የልጅ አመራር
ምዕራፍ 63—በሁሉ ነገር መሻትን መግዛት
መሻትን አለመግዛት አብዛኛውን የሕይወት ሕመሞች ያስከትላል— በሕይወት ውስጥ ከሚከሰቱት በሽታዎች መካከል ትልቁ ድርሻ መሻትን አለመግዛት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያወድማል፡፡ መሻትን አለመግዛት አስካሪ መጠጦች ላይ ብቻ ወስነን አናወራም፣ ነገር ግን ማንኛውንም ጎጂ የምግብ ፍላጎት ወይም አምሮትን በማካተት ሰፋ ያለ ትርጉም እንሰጠዋለን፡፡ 759 CGAmh 374.1
መሻትን ባለመግዛት አንዳንዶች ግማሽ፣ ሌሎቹ ደግሞ ሁለት ሦስተኛ የሚሆኑት አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ሥነ ምግባራዊ ኃይሎቻቸውን መሥዋዕት አድርገው ለጠላት መጫወቻዎች ይሆናሉ፡፡ 760 CGAmh 374.2
ከመጠን በላይ ልቅ መሆን ኃጢአት ነው— በአመጋገብ፣ በመጠጥ፣ በእንቅልፍ ወይም በማየት ልቅ መሆን ኃጢአት ነው። የሁሉም የሰውነት እና የአእምሮ ኃይሎች ጤናማ ተግባር በትብብር መሥራት ደስታን ያስከትላል፤ እንዲሁም ይበልጥ ኃይሎች የከበሩ እና ንጹህ ሲሆኑ ደስታም እንዲሁ ይበልጥንፁህ እና ያልተበከለ ይሆናል። 761 CGAmh 374.3
መሻትን መግዛት የኃይማኖታዊ ሕይወት መርሆ ነው— በዚህ ምድራዊ ሕይወት ውስጥ በሁሉ ነገሮች መሻትን መግዛት መስተማር እና መተግበር አለበት። በአመጋገብ፣ በመጠጣት፣ በእንቅልፍ እና በአለባበስ መሻትን መግዛት ከሃይማኖታዊ የሕይወት ታላላቅ መርሆዎች አንዱ ነው፡፡ ወደ ነፍስ መቅደስ የገባ እውነት አካል እንዴት መያዝ እንዳለበት ምሪት ይሰጣል፡፡ የሰብአዊ ሰው ወኪል ጤናን የሚመለከት ምንም ነገር በግዴለሽነት መታየት የለበትም፡፡ ዘላለማዊ ደህንነታችን በዚህ ምድር ሕይወት ላይ በጊዜአችን፣ በጥንካሬያችን እና በተፅኖአችን በተጠቀምበት የሚወሰን ይሆናል፡፡ 762 CGAmh 374.4
እዚህ የአንድ ጊዜ የሕይወት ውል ብቻ ተሰጥቶናል፤ እናም እያንዳንዱ ሰው መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ፣ የላቀ ትርፍ ማስገኘት እችል ዘንድ ሕይወቴን እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል እችላለሁ? የሚል መሆን ያለበት፡፡ 763 CGAmh 375.1
ለእግዚአብሔር እና ለሌሎች ለባልንጀሮቻችን ያለን የመጀመሪያ ግዴታችን ራስን ማጎልበት ነው፡፡ አቅማችን የፈቀደውን ያህል ከፍተኛውን በጎ ነገር ማከናወን እንድንችል ፈጣሪ የሰጠን እያንዳንዱ ችሎታ ወደ ላቀ የፍጽምና ደረጃ ማደግ አለበት፡፡ በመሆኑም ያ ጊዜ አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነትን በመመስረት እና ጠብቆ በማቆየት መልካም ተግባር ላይ መዋል አለበት፡፡ ከመጠን በላይ በመሥራት ወይም ማንኛውንም ሕያው ማሽንን አላግባብ በመጠቀም አንድ የአእምሮ ወይም የአካል ሥራ እንዲቀጭጭ ወይም ጎዶሎ በማድረግ የሚደርሰውን ጉዳት መቀበል አንችልም፡፡ በእርግጥ ይህንን ስናደርግ በውጤቱ ተጠቂዎች ልንሆን ይገባል፡፡ 764 CGAmh 375.2
አስደናቂ ኃይል አለው— መሻትን መግዛትን እና በሁሉም ነገር መደበኛነትን መጠበቅ አስደናቂ ኃይል አለው። የሕይወትን ጎዳና የተስተካከለ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያደርገውን መልካም እና የመንፈስ እርካታ ባህሪይን ለማሳደግ ከሁኔታዎች ወይም ከተፈጥሮ ስጦታዎች የበለጠ ይሰራል። በተመሳሳይ ጊዜ በዚህ መንገድ የሚገኝ ራስን የመቆጣጠር ኃይል እያንዳንዱን ሰው ከሚጠብቁ ጥብቅ ግዴታዎች እና ገሃዶች ጋር በተሳካ ሁኔታ ተጋድሎ ለማድረግ ከሚያስፈልጉ በጣም ጠቃሚ ከሚባሉ መሳሪያዎች መካከል አንዱ ሆኖ ይገኛል፡፡ 765 CGAmh 375.3
አስተሳሰብን ለማጥራት የሚረዳ ድጋፍ— ኃላፊነት ያለባቸው ሰዎች በየቀኑ ከፍተኛ ጠቀሜታ ባላቸው ውጤቶች ላይ መወሰን ያለባቸው ውሳኔዎች አሏቸው። ብዙውን ጊዜ በፍጥነት ማሰብ ይጠበቅባቸዋል፣ በመሆኑም ይህ በተሳካ ሁኔታ ሊከናወን የሚችለው ጥብቅ መሻትን መግዛትን በሚለማመዱ ሰዎች ብቻ ላይ ነው፡፡ አዕምሮ የሚጠነክረው በአካላዊ እና አእምሯዊ ኃይሎች ትክክለኛ አያያዝ ስር ነው። ውጥረቱ በጣም ከፍተኛ ባይሆን ኖሮ፣ ከእያንዳንዱ ተግባር ላይ በመጠመድ አዲስ ኃይል ይመጣል። 766 CGAmh 375.4
ራስን የመግዛት ልማዶች እጅግ ብዙ ወሮታዎችን ያስገኛሉ— በማደግ ላይ ያለው ትውልድ የምግብ ፍላጎትን ለመፈተን በተሰሉት ማታለያዎች ተከብቧል፡፡ በተለይም በትላልቅ ከተሞቻችን ውስጥ እያንዳንዱ አይነት ልቅነት ቀላል እና የሚጋብዝ እንዲሆን ተደርጓል፡፡ እነዚያ እንደ ዳንኤል ራሳቸውን ከማርከስ አሻፈረኝ የሚሉ ራስን የመግዛት ልማዳቸውን ወሮታ ያገኛሉ፡፡ በትላልቅ አካላዊ ጥንካሬአቸው እና በላቀ የመጽናት ኃይላቸው ድንገተኛ ሁኔታ ሲከሰት ከተቀማጭ ወጪ የሚያደርጉበት ባንክ አላቸው፡፡ CGAmh 376.1
ትክክለኛ የአካል ልማዶች የአእምሮን የበላይነት ያሳድጋሉ፡፡ የአዕምሯዊ ኃይል፣ አካላዊ ጥንካሬ እና ረጅም ዕድሜ በማይለወጡ ህጎች ላይ የተወሰነ ነው፡፡ ይህን ጉዳይ በተመለከተ እንደ አጋጣሚ የመከሰት እና ምንም ዕድል የሚባል ነገር የለም፡፡ የተፈጥሮ አምላክ የተፈጥሮ ሕጎችን በመጣስ ከሚመጡባቸው መዘዞች ሰዎችን ለማዳን ጣልቃ አይገባም፡፡ 767 CGAmh 376.2
ፍጹም ጤንነት ለማግኘት በሁሉም ራሳችን ግዙ— ጤናን ለመጠበቅ በሁሉም ነገር ራስን መግዛት አስፈላጊ ነው…። ንፅህና እና ቅድስና የሚወዱ እርሱ ለእነርሱ ያዘጋጃቸውን መልካም ነገሮች በማስተዋል እንዴት እንደሚጠቀሙበት ማወቅ ይችሉ ዘንድ እና በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ራስን መግዛትን በመለማመድ በእውነት እንዲቀደሱ የሰማዩ አባታችን በረከሰ የምግብ አምሮት ሳቢያ ከሚመጡ ክፋቶች እንድንጠበቅ የጤና ተሃድሶ ብርሃንን ልኮልናል።10 CGAmh 376.3
ራስን መግዛት ቅድስናን ይቀድማል— የእግዚአብሔር ሰዎች በሁሉም ነገር ራስን የመግዛትን ትርጉም መማር አለባቸው ...፡፡ ልቅነት ሁሉ ከሕይወታቸው መቆረጥ አለበት። የእውነተኛ መቀደስን እና ከክርስቶስ ፈቃድ ጋር የመስማማትን እውነተኛ ትርጉም በትክክል ከመረዳታቸው በፊት፣ ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር በተሳሳተ ልምዶች እና ተግባራት ላይ የበላይነትን ማግኘት አለባቸው፡፡11 CGAmh 376.4
በጥናት ላይ— በጥናት ላይ ራስን አለመግዛት የስካር ዝርያ ነው፤ እናም በዚህ ረገድ ልቅ የሚሆኑ ሁሉ፣ እንደ ሰካራም፣ ከደህና ጎዳናዎች እየራቁ ይሰናከላሉ፣ በጨለማም ይወድቃሉ፡፡ ጌታ የእያንዳንዱ ተማሪ ዐይን በእግዚአብሔር ክብር ላይ ብቻ መሆን እንዳለበት እንዲያስብ ይፈልጋል፡፡ ተማሪው የሳይንስን የተቻለውን ያህል እውቀት ሁሉ ለማግኘት በመፈለግ አካላዊ እና አእምሯዊ ኃይሎችን ማሟጠጥ እና ማባከን የለበትም፣ ነገር ግን የጽድቅን መንገድ በመፈልግ ረገድ ነፍሳትን ለመርዳት ጌታ በሾመው ሥራ ውስጥ ለመሳተፍ የኃይሎቹን ሁሉ አፍላነት እና ብርታት መጠበቅ አለበት፡፡ 768 CGAmh 377.1
በሥራ ላይ— በሥራችን ላይ ራስን መግዛትን መለማመድ አለብን፡፡ ከመጠን በላይ ሥራ የምንሠራበት ቦታ ላይ እራሳችንን ማድረግ ግዴታችን አይደለም፡፡ አንዳንዶች አንዳንድ ጊዜ ይህ አስፈላጊ በሚሆንበት ቦታ ሊቀመጡ ይችላሉ፣ ግን ደንብ ሳይሆን በተለየ ሁኔታ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ በሁሉም ነገር ልከኝነትን መለማመድ አለብን፡፡ የእኛን ድርሻ በመወጣት ጌታን የምናከብር ከሆነ እርሱ በበኩሉ ጤናችንን ይጠብቃል፡፡ ሁሉንም ብልቶቻችንን በማስተዋል ቁጥጥር ልናደርግበት ይገባል፡፡ በአመጋገብ፣ በመጠጥ፣ በአለባበስ፣ በጉልበት እና በሁሉም ነገር ልከኝነትን በመለማመድ ማንም ሐኪም ለእኛ ማድረግ የማይችለውን ለራሳችን ማድረግ እንችላለን፡፡13 CGAmh 377.2
እንደ ደንቡ፣ የቀኑ ሥራ እስከ ማታ ማራዘም የለበትም...፡፡ ይህንን የሚያደርጉ ጉልበታቸው ስለሚዝል፣ እና በነርቭ ስሜት መነሳሳት ስለሚሰሩ ብዙውን ጊዜ ከሚያገኙት የበለጠ ብዙ እንደሚያጡ ተረድቻለሁ፡፡ ወዲያውኑ ምንም ጉዳት እንደሚደርስባቸው ላይገነዘቡ ይችላሉ፣ ግን በእርግጥ አካላቸውን እያፈረሱ ነው፡፡ 769 CGAmh 377.3
በተወሰነ ጊዜ ውስጥ እጅግ ብዙ ስራዎችን ለመፈፀም ከፍተኛ ጥረት የሚያደርጉ እና ሕሊና ማረፍ እንዳለባቸው ሲፈረድባቸው ቀጥለው የሚሰሩ ሰዎች በጭራሽ አትራፊዎች አይደሉም፡፡ እነርሱ እየኖሩ ያሉት በተውሶ ጉልበት ነው፡፡ ለመጻኢ ጊዜ የሚያስፈልጋቸውን የሕይወት ኃይል እያጠፉ ነው፡፡ እናም በግዴለሽነት የተጠቀሙበት ጉልበት በሚፈለግበት ጊዜ ስለሚታጣ ይቸገራሉ፡፡ አካላዊ ጥንካሬው ጠፍቷል፣ የአእምሮ ኃይሎች አቅመ ቢስ ሆኗል፡፡ ኪሳራ እንዳጋጠማቸው ይገነዘባሉ፣ ነገር ግን ምን እንደሆነ አያውቁም፡፡ እርሱን የሚያስፈልጉበት ጊዜ ደርሷል፣ ነገር ግን አካላዊ ሀብቶቻቸው ተሟጠዋል፡፡ የጤና ህጎችን የሚጥስ ማንኛውም ሰው በአንድ ወቅት በከፍተኛ ወይም በተወሰነ ደረጃ ደረጃ ተጎጂ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር በሕይወታችን በተለያዩ ጊዜያት አስፈላጊ የሆኑትን አካላዊ ኃይል ሰጥቶናል፡፡ በተከታታይ ከመጠን በላይ በመስራት በግዴለሽነት ይህንን ኃይል ካሟጠጥን፣ የሆነ ጊዜ ላይ ከሳሪዎች እንሆናለን። 770 CGAmh 377.4
በአለባበስ ረገድ— በሁሉም ረገድ አለባበስ ጤናማ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር “ከሁሉ በላይ” በአካል እና በነፍስ ጤንነት “ጤነኞች” እንድንሆን ይፈልጋል። እንዲሁም ለነፍስም ሆነ ለሥጋ ጤንነት ከእርሱ ጋር አብረን ሠራተኞች መሆን አለብን፡፡ ሁለቱም በጤናማ አለባበስ ይበረታታሉ፡፡ CGAmh 378.1
አለባበስ የተፈጥሮ ቀላል ያለ ዘይቤ ጸጋ፣ ውበት፣ ተገቢነት ሊኖረው ይገባል፡፡ ክርስቶስ ስለ ሕይወት ኩራት አስጠንቅቆናል እንጂ ስለ ፀጋው እና ስለ ተፈጥሮአዊ ውበት ጋር አይደለም፡፡ 771 CGAmh 378.2
በአመመገብ ረገድ— እውነተኛ መሻትን መግዛት ጎጂ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እና ጤናማ የሆነውን በአግባቡ እንድንጠቀም ያስተምረናል፡፡ የአመጋገብ ልምዶቻቸው ከጤንነታቸው፣ ከባህሪያቸው፣ በዚህ ዓለም ካላቸው ፋይዳ ሳጪነታቸው እና ከዘላለማዊ ዕጣ ፈንታቸው ጋር ምን ያህል እንደሚዛመዱ የሚገነዘቡ ጥቂቶች ናቸው፡፡ የምግብ ፍላጎት ለሥነ ምግባራዊ እና ለአዕምሯዊ ኃይሎች መገዛት አለበት፡፡ አእምሮ ለአካል ሳይሆን አካል ለአእምሮ አገልጋይ መሆን አለበት፡፡ 772 CGAmh 378.3
እነዚያ መሻትን ባለመግዛት እና ያለ ሳያስተውሉ የሚመገቡ እና የሚሰሩ ሰዎች፣ ሳያስተውሉ የሚናገሩ እና የሚሰሩ ናቸው፡፡ መሻትን ላለመግዛት የአልኮል መጠጦችን መጠጣት አስፈላጊ አይደለም፡፡ በአመጋገብ መሻትን ያለመግዛት ኃጢአት— እጅግ ብዙ ጊዜ ደጋገሞ መመገብ፣ ቅመማ ቅመም የበዛበትን እጅግ ብዙ ጤናማ ያልሆነ ምግብን መመገብ— የምግብ መፍጫ አካላትን ጤናማ ተግባር ያወድማል፣ አንጎል ላይ ተጽዕኖ የማጣል እንዲሁም ፍርድን ያዛባል፣ ምክንያታዊ፣ የተረጋጋ፣ ጤናማ አስተሳሰብ እና ተግባርን ይከላከላል። 773 CGAmh 379.1
ከመጠን በላይ ላለመመገብ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ— ከአሥሩ እጅ በዘጠኙ እጅግ ጥቂት ከመመገብ ይልቅ ከመጠን በላይ መመገቡ ከፍተኛ አደጋ አለው...፡፡ ያለ ምንም በሽታ የሚሰቃዩ ብዙ ሕመምተኞች አሉ፡፡ የሕመማቸው መንስኤ የምግብ አምሮት ልቅነት ነው፡፡ ምግቡ ጤናማ ከሆነ የፈለጉትን ያህል መመገብ እንዳለባቸው ያስባሉ፡፡ ይህ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ ኃይላቸው የተዳከሙ ሰዎች መጠነኛ እና እንዲያውም ውስን የሆነ ምግብ መመገብ አለባቸው፡፡ ከዚያ የአካል ስርዓት በቀላሉ እና በጥሩ ሁኔታ ስራውን ሊያከናውን ይችላል፣ ከብዙ ስቃይም ይተርፋሉ።774 CGAmh 379.2
በአንዳች መሻትን ባለመግዛት ድርጊት እግዚአብሔርን አትካዱ— እኛ በዋጋ ተገዝተናል፤ ስለዚህ የእርሱ በሆኑት በሰውነታችን እና በመንፈሳችን እግዚአብሔርን ማክበር አለብን። በአንድም መሻትን ባለመግዛት ድርጊት እርሱን መካድ የለብንም፣ ምክንያቱም አንድያ የእግዚአብሔር ልጅ ከሥፍር በላይ ወጭ፣ በሕይወቱ መስዋእትነት ጭምር ገዝቶናል። እርሱ ለእኛ የሞተው ለክፉ ልምዶች ባሪያዎች እንድንሆን ሳይሆን፣ ነገር ግን ባለን ኃይል ሁሉ እርሱን የምናገለግል የእግዚአብሔር ወንዶችና ሴቶች ልጆች እንሆን ዘንድ ነው፡፡ 775 CGAmh 379.3
በዚህ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር ስለ መቆማቸው የማያቋርጥ ግንዛቤ ያላቸው ሰዎች የምግብ ፍላጎትን የሚያስደስት ነገር ግን የምግብ መፍጫ አካላትን በሚጎዳ ምግብ ጨጓራቸው ውስጥ አያኖሩም፡፡ ተገቢ ያልሆነ የአመጋገብ፣ የመጠጥ ወይም የአለባበስ ልምዶችን በመለማመድ የእግዚአብሔርን ንብረት አያበላሹም። ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር ለመስራት ይህንን ማድረግ እንዳለባቸው በመገንዘብ ለሰብአዊ ሰው ማሽን ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ እርሱ ጤናማ፣ ደስተኛ እና ጠቃሚ እንዲሆኑ ይፈልጋል። ነገር ግን ይህን ይሆኑ ዘንድ ፈቃዳቸውን ከፈቃዱ ጎን ማድረግ አለባቸው፡፡776 CGAmh 379.4
በእያንዳንዱ የቤት ሕይወት ዝርዝር ውስጥ መሻትን መግዛትን መተግበር— የወላጆች ምሳሌ መሻትን የመግዛት ትምህርት ይሆን ዘንድ፤ ራስን መካድን እና ራስን መቆጣጠርን ልጆችን ለማስተማር እና ከህፃንነት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ በእነርሱ ላይ ተፈፃሚ ይሆን ዘንድ ለማድረግ፤መሻትን የመግዛት መርሆዎች በሁሉም የቤት ሕይወት ዝርዝሮች ውስጥ እንዲተገበር እንመክራለን፡፡ 777 CGAmh 380.1
በቤተሰብ ክበብ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ ክርስቲያናዊ መሻትን መግዛትን ከፍ ባለ መድረክ ላይ ማድረግ አለብን፡፡ እርሱ ህያው፣ የሚሰራ አካል፣ ልምዶችን፣ ዝንባሌዎችን እና ባህሪያትን የሚያድስ መሆን አለበት፡፡23 CGAmh 380.2