የልጅ አመራር

64/85

ምዕራፍ 62—ለመኖር መመገብ

እግዚአብሔር ዝንባሌዎችን እና የምግብ አምሮቶችን ሰጥቷል— ተፈጥሮአዊ ዝንባሌያችን እና የምግብ አምሮታችን ... በመለኮት የተሰጡ ሲሆን ለሰው ሲሰጡ ንፁህና ቅዱስ ነበሩ፡፡ አዕምሮ የምግብ ፍላጎትን እንዲገዛ እና ለደስታችን መገልገል እንዲችሉ የእግዚአብሔር ዕቅድ ነበር። በተቀደሰ አዕምሮ ደንብ እና ቁጥጥር ሥር ሲሆኑ ቅድስና ለጌታ ይሆናሉ፡፡ 721 CGAmh 358.1

መለኮትን የሚያሳስብ ርዕሰ ጉዳይ— የእስራኤላውያን ትምህርት ሁሉንም የሕይወት ልማዶቻቸውን ያካተተ ነበር፡፡ ደህንነታቸውን የሚመለከቱ ነገሮች ሁሉ መለኮትን የሚያሳስብ ጉዳይ እና በመለኮታዊ ሕግ ክልል ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ ምግባቸውን በማቅረብ ረገድ እንኳን፣ እግዚአብሔር የላቀውን መልካም ነገር ተመኝቶላቸዋል፡፡ በምድረ በዳ የመገባቸው መና፣ አካላዊ፣ አእምሯዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጥንካሬን የማጎልበት ተፈጥሮ ነበረው…፡፡ ምንም እንኳን በምድረ በዳ ኑሯቸው ከባድ ችግሮች ቢኖሩም እንኳ በጎሳዎቻቸው ሁሉ ውስጥ አንድ ደካማ ሰው አልነበረም፡፡ 722 CGAmh 358.2

ከምንመገበው ምግብ የተገነባው ነው— ሰውነታችን የተገነባው ከምንመገበው ምግብ ነው። በሰውነት ሕብረ ሕዋሳት ውስጥ የማያቋርጥ መሰባበር አለ፤ የእያንዳንዱ አካል እንቅስቃሴ ሁሉ ተወጋጅን ያጠቃልላል፣ እናም ይህ ተወጋጅ የሚተካው በምግቦቻችን ነው። እያንዳንዱ የሰውነት አካል የድርሻውን ምግብ ይፈልጋል፡፡ አንጎል የድርሻውን ማግኘት አለበት፤ አጥንቶች፣ ጡንቻዎች እና ነርቮች የራሳቸውን ይፈልጋሉ፡፡ ምግብን ወደ ደም የሚቀይር እና ይህን ደም የሚጠቀሙ የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን ለመገንባት የሚያስችላቸው አስደናቂ ሂደት ነው፤ ነገር ግን ይህ ሂደት በተከታታይ እየተከናወነ ለእያንዳንዱን ነርቭ፣ ጡንቻ እና ህብረ ህዋሳት ህይወትን እና ጥንካሬን ይሰጣል፡፡723 CGAmh 358.3

በትክክለኛው የሕፃን ምግብን በመመገብ ጀምሩ— ልጆች የአመጋገብ ሥርዓትን እንዲያስተካክሉ የማሠልጠን አስፈላጊነት በጭራሽ ከግምት በላይ ነው። ትናንሾቹ ልጆች ለመብላት ሳይሆን ለመኖር እንደሚመገቡ መማር አለባቸው፡፡ ስልጠናው በእናቱ እቅፍ ውስጥ ባለው ህፃን መጀመር አለበት፡፡ ህፃኑ ምግብን በመደበኛ የጊዜ ክፍተቶች ብቻ ሊሰጠው ይገባል፣ ዕድሜውም እየጨመረ ሲሄድ ድግግሞሹ መቀነስ አለበት። እርሱ ሊፈጨው የማይችለው ጣፋጮች ወይም በዕድሜ የገፉ ሰዎች ምግብ ሊሰጠው አይገባም፡፡ ጨቅላ ሕፃናትን በመመገብ ረገድ የሚደረግ እንክብካቤ እና መደበኛነት ጤናን በማሳደግ የረጉ እንዲሁኑ እና ተወዳጅ ባህሪይ እንዲኖራቸው ማድረግ ብቻ ሳይሆን ካደጉ በኋላ በረከት ለሚሆንላቸው ልማዶች መሠረት ይጥላል፡፡ 724 CGAmh 359.1

ምርጫዎችን እና የምግብ ፍላጎትን ማሰልጠን— ልጆች ከጨቅላነታቸው እንደወጡ፣ ጣዕማቸውን እና የምግብ ፍላጎታቸውን በማሰልጠን ረገድ አሁንም ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት። ብዙውን ጊዜ ጤናን ከግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ የመረጡትን ነገር እና በመረጡበት ጊዜ እንዲመገቡ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ ጤናማ ባልሆኑ ጥሩ ምግቦች ላይ የሚባክነው ጉልበት እና ገንዘብ ወጣቶች በሕይወት ውስጥ ትልቁ ነገር እና እጅግ ከፍተኛ ደስታን የሚያመጣው የምግብ ፍላጎትን ማጣጣም ነው ብለው እንዲያስቡ ይመራቸዋል፡፡ የዚህ ስልጠና ውጤት ሆዳምነት ነው፣ ከዚያም በሽታ ይመጣል ...፡፡ CGAmh 359.2

ወላጆች የልጆቻቸውን የምግብ ፍላጎት ማሠልጠን አለባቸው እንዲሁም ለጤና ጎጂ የሆኑ ምግቦች እንዲጠቀሙ መፍቀድ የለባቸውም፡፡ 725 CGAmh 359.3

ምግብ መንፈሳዊ፣ አእምሯዊና አካላዊ ኃይሎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል— ጤና እና የደስታ ስሜቶችን መስዋዕት በማድረግ የልጆቻቸውን ፍላጎት የሚያረኩ እናቶች በቅለው ፍሬ የሚያፈሩ የክፋት ዘሮችን እየዘሩ ናቸው፡፡ እንዳሻቸው መሆን በትናንሽ ልጆች ውስጥ ያድጋል፣ አእምሯዊም ሆነ አካላዊ ብርታቶች መስዋዕት ይደረጋሉ። ይህን ስራ የሚሰሩ እናቶች የዘሩትን ዘር በምሬት ያጭዳሉ፡፡ ልጆቻቸው በህብረተሰብ ውስጥ ወይም በቤት ውስጥ ክቡር እና ጠቃሚ ሚና ለመወጣት በአእምሮ እና በባህሪይ ብቃት የሌላቸው ሆነው ሲያድጉ ይመለከታሉ፡፡ መንፈሳዊም ሆነ አእምሯዊና አካላዊ ኃይሎች ጤናማ ባልሆነ ምግብ ተጽዕኖ ሥር ጉዳት ይደርስባቸዋል። ሕሊና ይደነዝዝ እና ለመልካም ነገር ያለው ተጋላጭነት ይጎዳል። 726 CGAmh 359.4

ምርጥ ምግቦችን ምረጡ—ምርጥ ምግቦች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ለሰው ምግብ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር የነበረውን የመጀመሪያ እቅድን ማጥናት አለብን፡፡ ሰውን የፈጠረው እና ፍላጎቱንም የሚረዳ እርሱ ለአዳም ምግብን መረጠ...፡፡ ፈጣሪያችን የመረጠልን ምግብ ጥራጥሬዎች፣ ፍራፍሬዎች፣ የቅባት እህሎች እና አትክልቶችን ያጠቃልላል፡፡ 727 CGAmh 360.1

ቀላል ባለ፣ በሚጥም መንገድ ማዘጋጀት— እግዚአብሔር ያልተዛባ የሰው ልጅ የምግብ ፍላጎት እንዲረካ የተትረፈረፈ መንገድ አዘጋጅቷል፡፡ የምድርን ምርቶች በፊቱ አትረፍርፏል— ይህም ለጣዕም የሚጣፍጡ እና ለአካል ለስርዓት ጠቃሚ የሆኑ ብዙ የተትረፈረፈ ምግብ ነው። ደግ የሆነው የሰማዩ አባታችን እነዚህንበነፃ ብሉ ይላል፡፡ ከማንኛውም ዓይነት ቅመማ ቅመም እና ቅባት ነጻ የሆነ በቀላል መንገድ የተዘጋጁ ፍራፍሬዎች፣ ጥራጥሬዎች እና አትክልቶች ከወተት ወይም ከክሬም ጋር ሲሰራ እጅግ ጤናማ አመጋገብ ነው፡፡ በአነቃቂዎች ምግብ የልተሰራ ምግብ እነዚህ ሰውነትን ይመግባሉ፣ የጽናት ኃይል እና የአዕምሮ ብርታትን ይሰጣሉ፡፡8 CGAmh 360.2

የምግብ አምሮት አስተማማኝ መመሪያ አይደለም— ሰውነትን ለመገንባት የሚያስፈልጉትን ንጥረ ነገሮች በተሻለ ሁኔታ የሚያቀርቡ ምግቦች መመረጥ አለባቸው። በዚህ ምርጫ ረገድ የምግብ አምሮት አስተማማኝ መመሪያ አይደለም፡፡ በተሳሳተ የአመጋገብ ልምዶች አማካኝነት የምግብ ፍላጎት ፈሩን ለቋል፡፡ እርሱ ብዙውን ጊዜ ጤናን የሚጎዳ እና ከብርታት ይልቅ ድክመትን የሚያስከትል ምግብን ይፈልጋል...፡፡ በሁሉም ቦታ ተስፋፍቶ የሚገኝ በሽታ እና ስቃይ በአመዛኙ በአመጋገብ ስህተቶች ሳቢያ የመጣ ነው፡፡728 CGAmh 360.3

ያልተገራ የምግብ ፍላጎት የሚከተሉ ልጆች— በመኪኖች ስጓዝ ሳለሁ ወላጆች የልጆቻቸው የምግብ ፍላጎት ደካማ እንደሆነ እና ስጋ እና ኬክ ከላገኙ በስተቀር መብላት እንደማይችሉ ሲናገሩ እሰማለሁ። የእኩለ ቀን ምግብ በሚበላበት ጊዜ ለእነዚህ ሕፃናት የሚቀርበውን የምግብ ጥራት ተመልክቻለሁ፡፡ ይህም ሥስ የስንዴ ዳቦ፣ በቁንዶ በርበሬ የተሸፈነ ቁራጭ የአሳማ ሥጋ፣ ቁራጭ የቅጠላ ቅጠል ኮምጣጤ፣ ኬክ እና ለረጅም ጊዜ ተጠብቆ የቆየ ምግብ ነበር፡፡ የእነዚህ ሕፃናት የገረጣ፣ ፈዛዛ ፊት ጨጓራ እየደረሰበት ያለውን በደል በግልጽ ያመለክታል፡፡ ከእነዚህ ልጆች መካከል ሁለቱ የሌላ ቤተሰብ ልጆች ከምግባቸው ጋር አይብ ሲመገቡ ተመልክተው አግባብነት የሌለውን መሻታቸውን የምታረካ እናታቸው ውዶቿ ምግባቸውን ሳይጨርሱ ይቀራሉ በሚል ፍራቻ ትንሽ አይብ ለምና ለልጆቿ እንክትሰጣቸው ድረስ በፊታቸው ላለው ምግብ ፍላጎታቸው ጠፋ፡፡ ይህችም እናት “ልጆቼ ይህን ወይም ያን እጅግ በጣም ይወዳሉ፣ እኔም የሚፈልጉትን እንዲያገኙ አደርጋቸዋለሁ፤ ምክንያቱም የአካል ሥርዓት ለሚፈልገውን ዓይነት ምግብ አምሮት ይኖረዋል” ስትል ሐሰብ ትሰጥ ነበር፡፡ CGAmh 361.1

የምግብ ፍላጎት በፍጹም ባይዛባ ኖሮ ይህ ትክክል ሊሆን ይችል ነበር፡፡ የተለመደ እና የተበላሸ የምግብ ፍላጎት አለ፡፡ የምግብ አምሮታቸው እስኪዛባ እና ሸክላ፣ ቀላጭ እርሳሶችን፣ የተቃጠለ ቡና፣ የሻይ አተላ፣ ቀረፋ፣ ቅርንፉድ እና ቅመማ ቅመም ለመብላት እስኪጓጉ ድረስ—ልጆቻቸው በሕይወታቸው በሙሉ ጤናማ ያልሆነ እና የሚያነቃቃ ምግብ እንዲመገቡ ያስተማሯቸው ወላጆች— የአካል ሥርዓት ለሚፈልገውን ዓይነት ምግብ አምሮት ይኖረዋል ብለው ለመናገር መብት የላቸውም፡፡ የምግብ አምሮት እስኪዛባ ድረስ በተሳሰተ መንገድ ተገርቷል፡፡ በቀላሉ ለጉዳት መጋለጥ የሚችለው ስሜቱ እስኪጠፋ ድረስ የጨጓራ ሥስ የአካል ክፍሎች እንዲነቃቁ እና እንዲቃጠሉ ተደርገዋል፡፡ የተጎዳው ጨጓራ በጣም በሚያነቃቁ ንጥረ ነገሮች ካልተበረታታ በስተቀር የተሰጠውን ሥራ አይሠራም፡፡ እነዚህ ልጆች ከጨቅላነታቸው ጀምሮ በጣም በቀላል መንገድ ተዘጋጅተው፣ በተቻለ መጠን የተፈጥሮ ንጥረ ነገሮቻቸውን ጠብቀው፣ የስጋ ምግቦችን፣ ቅባቶችን እና ማናቸውንም ቅመሞችን በማስወገድ ጤናማ ምግብን ብቻ እንዲወስዱ ቢሰለጥኑ ኖሮ ጣዕማቸውና የምግብ ፍላጎታቸው ባልተበላሸ ነበር፡፡ በተፈጥሮው ሁኔታ ከአካል ስርዓት ፍላጎቶች ጋር በተሻለ ሁኔታ የተጣጣመውን ምግብ በከፍተኛ ደረጃ ሊያመለክት ይችል ነበር፡፡” 729 CGAmh 361.2

ስለሥጋ ምግብስ ምን ማለት እንችላለን?— በምግብ ረገድ ሁሉም ሰው መከተል ያለበትን የተወሰነ መስመር ለይተን አናወጣም፤ ነገር ግን ብዙ ጥራጥሬዎች፣ እና የቅባት እህሎች ባሉባቸው ሀገሮች ውስጥ የሥጋ ምግብ ለእግዚአብሔር ህዝብ ትክክለኛ ምግብ አይደለም እንላለን፡፡ የሥጋ ምግብ ተፈጥሮ የእንስሳነት፣ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ለእያንዳንዱ ሰው ሊሰማቸው የሚገባውን ፍቅር እና ርህራሄ የማስወገድ እና ወራዳ ፍላጎቶች በከፍተኛ ኃይሎች ላይ ቁጥጥር እንዲኖራቸው የማድረግ ዝንባሌ እንዳለው መመሪያ ተሰጥቶኛል፡፡ የስጋ ምግብ ጤናማ ቢሆን ሆኖ ቢሆን እንኳ አሁን ደህንነቱ የተጠበቀ አይደለም፡፡ 730 CGAmh 362.1

የሥጋ ምግቦችን መወገድ ያለባቸው ምክንያቶች— ሥጋ የሚመገቡ ሰዎች ጥራጥሬና አትክልትን በሁለተኛ ደረጃ በመመገብ ላይ ናቸው፤ ምክንያቱም እንስሳው እድገት የሚሰጠውን ምግብ ከእነዚህ ነገሮች ይወስዳል፡፡ በጥራጥሬዎችና በአትክልቶች ውስጥ የነበረው ሕይወት በተመጋቢው ውስጥ ያልፋል፡፡ እኛ ይህን የምወስደው የእንስሳውን ሥጋ በመመገብ ነው፡፡ እኛ እንድንጠቀምበት እግዚአብሔር የሰጠንን ምግብ በመመገብ ቀጥታ ማግኘቱ እንዴት የተሻለ ነው! CGAmh 362.2

ሥጋ በጭራሽ ምርጥ ምግብ ሆኖ አያውቅም፤ በእንስሳት ላይ ያለው በሽታ በጣም በፍጥነት እየጨመረ ስለመጣ አሁን እርሱን መጠቀሙ የባሰ በእጥፍ ተቃውሞ የሚደርስበት መሆን አለበት፡፡ የሥጋ ምግቦችን የሚጠቀሙ ሰዎች ምን እየተመገቡ እንደሆነ አያውቁም፡፡ ብዙውን ጊዜ እንስሳቱ በሕይወት ሳለ ማየት ቢችሉ እና የሚመገቡትን የስጋ ጥራት ቢያውቁ በጥላቻ ፊታቸውን ያዞሩ ነበር፡፡ ሰዎች በሳንባ ነቀርሳ እና በካንሰር ጀርሞች የተሞላ ሥጋን ያለማቋረጥ እየተመገቡ ነው፡፡ የሳንባ ነቀርሳ ፣ ካንሰር እና ሌሎች ገዳይ በሽታዎች በዚህ መንገድ ይተላለፋሉ።12 CGAmh 362.3

ውጤቶቹ በቅጽበት አይመጣም— የሥጋ ምግብ ውጤቶች ወዲያውኑ ሊከሰት አይችልም፣ ነገር ግን ይህ ሥጋ ምንም ጉዳት እንደሌለው የሚያሳይ ማስረጃ አይደለም። ደማቸውን የመረዘው እና ለመከራ ያበቃቸው የሚመገቡት ሥጋ መሆኑን የሚያምኑት ጥቂቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች እውነተኛውን መንስኤ ራሳቸውም ሆኑ ሌሎች ሳይጠረጣሩ ሙሉ በሙሉ ሥጋ በመመጋባቸው ሳቢያ በበሽታዎች ይሞታሉ፡፡ 731 CGAmh 363.1

ወደ መጀመሪያው ጤናማ ምግብ መመለስ— ሁሉም የሥጋ ምግብን ለማስወገድ ማቀድ ያለበት ጊዜ አይደለምን? የሰማያዊ መላእክት ወዳጅነት እንዲኖራቸው ንፁህ፣ የጠሩ እና ቅዱሳን ለመሆን የሚፈልጉ ሰዎች እንዴት በነፍስና በሥጋ ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትለውን ማንኛውንም ነገር እንደ ምግብ መጠቀምን ይቀጥላሉ? ሥጋን እንደ ቅንጦት ለመብላት የእግዚአብሔርን ፍጡራን ሕይወት እንዴት ሊያጠፉ ይችላሉ? ይልቁን በመጀመሪያ ለሰው ወደ ተሰጠው ጤናማና ጣፋጭ ምግብ ይመለሱ፡፡ 732 CGAmh 363.2

የክርስቶስን ምጽዓት የሚጠባበቁ ሰዎች አካሄድ— የጌታን መምጣት ከሚጠባበቁ ሰዎች መካከል የስጋ ምግብ በመጨረሻ ይወገዳል፣ ሥጋ የምግባቸው አንድ አካል መሆኑ ያበቃል፡፡ መቼም ይህንን በዓላማችን ይዘን ወደ እርሱ ለመድረስ ያለማቋረጥ ለመስራት መጣር አለብን። ስጋ በመብላት እግዚአብሔር ለእኛ በመስጠቱ ከተደሰተበት ብርሃን ጋር በስምምነት እየሄድን ነን ብዬ ማሰብ አልችልም፡፡ 733 CGAmh 363.3

ወደ እግዚአብሔር ንድፍ ተመለሱ— እንደገና እና ደጋግሜ እግዚአብሔር ህዝቦቹን ወደ ቀደመው ንድፍ እንደሚመልሳቸው፣ ማለትም የሞቱ እንስሳት ሥጋ ላይ ተደግፎ በሕይወት መቆየት እንደሌለባቸው ተመልክቻለሁ፡፡ እርሱ የተሻለ መንገድ ሰዎችን እንድናስተምር ይፈልጋል ...፡፡ ሥጋ ከተወገደ፣ የምግብ አምሮት በዚያ አቅጣጫ ካልተማረ፣ ፍራፍሬ እና ጥራጥሬ መውደድ የሚበረታታ ከሆነ፣ ሳይቆይ እግዚአብሔር በመጀመሪያ ይሆን ዘንድ እንደ ነደፈው ይሆናል፡፡ ምንም አይነት ሥጋ በሕዝቡ ዘንድ ጥቅም ላይ አይውልም፡፡16 CGAmh 363.4

የአመጋገብ ለውጥን በተመለከተ የተሰጠ መመሪያ— የጡንቻ ጥንካሬ የእንስሳትን ምግብ በመጠቀም ላይ የተመሠረተ ነው ብሎ ማሰብ ስህተት ነው። እርሱን ሳንጠቀም የአካል ስርዓት ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ሊቀርቡ ይችላሉ፣ የበለጠ ጥሩ ጤንነትን ማጣጣም ይቻላል። ጥራጥሬዎች፣ ፍራፍሬዎች፣ ለውዞች እና አትክልቶች ጥሩ ደም ለመፍጠር አስፈላጊ የሆኑ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ሁሉ ይዘዋል፡፡ እነዚህ ንጥረ ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ወይም ሙሉ በሙሉ በስጋ አመጋገብ ሊበረከት አይችልም። ሥጋን መጠቀሙ ለጤና እና ለጥንካሬ አስፈላጊ ቢሆን ኖሮ የእንስሳት ምግብ መጀመሪያ ለሰው በተመረጠው ምግብ ውስጥ ይካተት ነበር፡፡ CGAmh 364.1

የሥጋ ምግብን መጠቀም ሲቋረጥ ብዙውን ጊዜ የድካም ስሜት፣ የጉልበት ማጣት ይኖራል፡፡ ብዙዎች ይህን የሥጋ ምግብ አስፈላጊ መሆኑን እንደ ማስረጃ ያቀርባሉ፤ ነገር ግን እንደዚህ አይነቶቹ ምግቦች አነቃቂ በመሆናቸው፣ ደምን ስለሚያሞቁ እና ነርቮችን ስለሚያነቃቁ እና ይህ የሆነው ሰውነት እነዚህ በማጣቱ ነው፡፡ አንዳንዶች ሰካራም መጠጦቻቸውን ለመተው እንደሚቸገሩ ሁሉ ሥጋ መብላትን ለመተው ይቸገራሉ፣ ነገር ግን በለውጡ የተሻሉ ይሆናሉ፡፡ CGAmh 364.2

የሥጋ ምግብ በሚወገድበት ጊዜ ቦታው በተለያዩ ጥራጥሬዎች፣ ለውዞች፣ አትክልቶች እና ፍራፍሬዎች መተካት አለበት፡፡ ይህ አስፈላጊ የሚሆነው በተለይም ደካማ ለሆኑት ወይም በተከታታይ የጉልበት ሥራ ለሚሰሩ ሰዎች ነው፡፡ 734 CGAmh 364.3

በደንብ የተዘጋጁ ተተኪዎች ጠቃሚ ናቸው— በተለይም ስጋ ዋና የምግብ ዝርዝር በማይሆንበት ሁኔታ ጥሩ የምግብ አሰራር አስፈላጊ መስፈርት ነው፡፡ የስጋን ቦታ ለመተካት አንድ ነገር መዘጋጀት አለበት፣ እንዲሁም ሰው ስጋን እንዳይመኝ፣ እነዚህ የስጋ ምትኮች በደንብ መዘጋጀት አለባቸው።18 CGAmh 364.4

ከሥጋ ምግብ ወደ የተጎሳቆለ አመጋገብ ለውጥ ያደረጉ ቤተሰቦችን አውቃለሁ፡፡ ምግባቸው በሚያስጠላ ሁኔታ ከመዘጋጀቱ የተነሳ ጨጓራ ይጸየፈው ነበር፣ እናም እንደነዚህ ያሉ ሰዎች የጤና ተሃድሶ ከእነርሱ ጋር እንደማይስማማ፤ በአካላዊ ጥንካሬ እየቀነሱ እንደነበረ ነግረውኛል፡፡ አንዳንዶች ምግባቸውን ቀለል ለማድረግ በሚያደርጉት ጥረት ስኬታማ ያልነበሩበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው፡፡ አመጋገባቸው በድህነት የተጠቃ ነበር፡፡ ምግብ ያለ ምንም ጥረት ይዘጋጃል፣ ዘወትርም ተመሳሳይነት ያለው ይሆናል። CGAmh 365.1

በአንድ የምግብ ክፍለ ጊዜ ብዙ ዓይነት ምግብ መኖር የለበትም፣ ነገር ግን ሁሉም የምግብ ክፍለ ጊዜ ለውጥ ሳይኖር አንድ ዓይነት ምግቦችን ማካተት የለባቸውም፡፡ ምግብ ቀለል ባለ መንገድ፣ ሆኖም ግን የምግብ ፍላጎትን ከሚያነሳሳ ጥሩ ስሜት መዘጋጀት አለበት። 735 CGAmh 365.2

ከተፈጥሮ ውጭ የሆነውን የምግብ ፍላጎት ማሸነፍ— ቅመማ ቅመም የበዛበት፣ በጣም አነቃቂ የሆነ ምግብ የለመዱ ሰዎች ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ጣዕም አላቸው፣ በመሆኑም በአንድ ጊዜ ቅመም የሌለበት እና ቀላል የሆነ ምግብ አያረካቸውም። ጣዕም ተፈጥሯዊ እስኪሆን እና ጨጓራ ከደረሰበት በደል ለማገገም ጊዜ ይወስዳል፡፡ ነገር ግን ጤናማ ምግብን በመጠቀም ጽናትን የሚያሳዩ ሰዎች፣ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ደስ የሚል ሆኖ ያገኙታል፡፡ ብስክስክ እና ጣፋጭ ጣዕሞቹ አድናቆት ያገኛሉ፣ እና ጤናማ ባልሆኑ ጣፋጮች ከሚሰረው ይበልጥ በደስታ ይበላል። እንዲሁም ጨጓራ፣ ጤናማ በሆነ ሁኔታ፣ ትኩሳትም ሆነ መጨናነቅ በጭራሽ ሳይደርስበት፣ ተግባሩን በቀላሉ ማከናወን ይችላል፡፡ 736 CGAmh 365.3

ጤናማ አመጋገብ መስዋእትነት አይደለም— ልጆች የምግብ ፍላጎትን እንዲቆጣጠሩ እና ጤንነትን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እንዲመገቡ መማር ቢገባቸውም ከሚጎዷቸው ነገሮች ብቻ እራሳቸውን እየካዱ እንደሆነ ግልፅ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡ ለተሻለ ነገር የሚጎዱ ነገሮችን ይተዋሉ፡፡ የምግብ ገበታ እግዚአብሔር በቸርነቱ በለገሳቸው መልካም ነገሮች ሲሞላ ማራኪ እና የሚስብ ይሁን፡፡ 737 CGAmh 365.4

ወቅቱን ፣ የአየር ንብረትን፣ የሥራ ሁኔታን ከግንዛቤ ውስጥ አስገቡ— ሁሉም ጤናማ የሆኑ ምግቦች በማናቸውም ሁኔታዎች ሁሉ ከፍላጎቶቻችን ጋር የሚስማሙ አይደሉም፡፡ በምግብ ምርጫ ረገድ ጥንቃቄ መደረግ አለበት፡፡ አመጋገባችን ከወቅቱ፣ ከምንኖርበት አካባቢ አየር ሁኔታ እና ከምንሰራው የሥራ ሁኔታ ጋር የተጣጠመ መሆን አለበት፡፡ ከአንድ ወቅት ወይም ከአንድ የአየር ንብረት ጋር የሚጣጣሙ አንዳንድ ምግቦች ለሌላው ተስማሚ አይደሉም፡፡ ስለዚህ በተለያዩ የሥራ ሁኔታዎች ላይ ላሉት ሰዎች እጅግ የሚስማሙ የተለያዩ ምግቦች አሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ በከባድ የጉልበት ሥራ ላይ ለተሠማሩ ሰዎች ሊጠቀም የሚችል ምግብ ያለ እንቅስቃሴ ሥራቸውን ለሚሰሩ ወይም ከባድ የአእምሮ ትግበራ ላላቸው ሰዎች ተገቢ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ብዙ የተለያዩ ጤናማ ምግቦችን ሰጥቶናል፣ በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው ልምድ እና ትክክለኛ የሕሊና ውሳኔዎች ከራሱ ፍላጎቶች ጋር እንደሚስማማ የሚያረጋግጥለትን መምረጥ አለበት። 738 CGAmh 366.1

ምግብን በብልህነት እና በክህሎት አዘጋጁ— የምግብ ፍላጎትን ለማሟላት ብቻ መመገብ ስህተት ነው፣ ነገር ግን የምግብ ጥራት ወይም የአሰራር ሁኔታን በተመለከተ ግድየለሽነት መታየት የለበትም። የሚበላው ምግብ ማራኪ ካልሆነ ሰውነት በደንብ አይገነባም። ምግብ በጥንቃቄ መመረጥ እና በእውቀት እና በችሎታ መዘጋጀት አለበት። 739 CGAmh 366.2

“ማንኛውንም ነገር ማንሳት እንችላለን፡፡” — በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ ለጎብኝዎች ታላቅ ዝግጅት ይደረጋል፡፡ ለገበታ ሲባል ብዙ የተለያዩ ምግቦች ይዘጋጃሉ፡፡ ይህ ምግብ እንደነዚህ ዓይነቶቹን ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን የተለያዩ ምግቦችን ላልተለማመዱ ሰዎች ፈታኝ ነው ...፡፡ CGAmh 366.3

እነዚህን ከመጠን በላይ ዝግጅቶች ለጎብኝዎች የሚያደርጉ አንዳንድ ሰዎችን አውቃለሁኝ፡፡ በገዛ ቤተሰቦቻቸው ውስጥ መደበኛነትን አይጠብቁም፡፡ ምግቦቹ የሚዘጋጁት ለሚስቱት እና ለእናት ምቾት ተስማሚ እንዲሆን ተደርጎ ነው፡፡ የባል እና የልጆች ደስታ አልተጠናም፡፡ ምንም እንኳን እንደዚህ አይነት ድግስ ለጎብኝዎች የሚደረግ ቢሆንም፣ አንድ ነገር “ለእኛ ብቻ” እንደሚጠቅም ተደርጎ መታሰብ አለበት፡፡ ግድግዳው ጋር ያለው የምግብ ገበታ ላይ ማራኪ እንዲሆን ምንም ጥረት ሳይደረግ የተቀመጠ ቀዝቃዛ ምግብ ብዙ ጊዜ ይታያል፡፡ “ለእኛ ብቻ” ይላሉ፡፡ “አንዱን ነገር ማንሳት እንችላለን፡፡” 740 CGAmh 366.4

የመመገቢያ ሰዓቱን አስደሳች የማህበራዊ ጊዜ አድርጉት— የምግብ ሰዓት የማህበራዊ ግንኙነት እና የመዝናኛ ወቅት መሆን አለበት፡፡ ሸክም ሊሆኑ ወይም ሊያበሳጩ የሚችሉ ነገሮች ሁሉ መወገድ አለባቸው፡፡ በበጎውን ሁሉ ሰጪ በሆነው ላይ መተማመን፣ ቸርነት እና አመስጋኝነት ይታይ፣ እንዲሁም ንግግር አስደሳች ይሁን፣ ሳያዝል ከፍ ከፍ የሚያደርግ ደስ የሚል የሃሳብ ፍሰት ይኑር። 741 CGAmh 367.1

የምግብ ገበታ ወላጆች በሚከተሉት አንዳንድ ምክንያታዊ ያልሆኑ አካሄዶች ጭቅጭቅ በልጆች ላይ እንዲታይ የሚፈለግበት ቦታ አይደለም፡፡ መላው ቤተሰብ እግዚአብሔርን የሚወዱ እና የሚታዘዙ በእግዚአብሔር መንግሥት የበጉን የሰርግ እራት እንደሚመገቡ እና ኢየሱስ ራሱ እንደሚያገለግላቸው በማስታወስ በደስታ፣ በምስጋና መመገብ አለባቸው።742 CGAmh 367.2

በአመጋገብ ረገድ ሊጠበቅ የሚገባ መደበኛነት— በአመጋገብ ረገድ ሊጠበቅ የሚገባ መደበኛነትን ማጣት ጤናን እና ደስታን ለመጉዳት የምግብ መፍጫ አካላትን ጤናማ ቃና ያጠፋሉ። 743 CGAmh 367.3

በምንም መልኩ የምግብ ክፍለ ጊዜያት መደበኛነታቸውን ያጡ መሆን የለባቸውም፡፡ እራት ከተለመደው ጊዜ ከአንድ ሰዓት ወይም ከሁለት ሰዓት በፊት ቢበላ ጨጓራ ሌላ ሸክም ለመሸከም ዝግጁ አይደለም፤ ምክንያቱም ቀድሞ የተበላውን ምግብ ስላላስወገደ ለአዲሱ ሥራ ለሕይወት አስፈላጊ የሆነ ኃይል አይኖረውም። በመሆኑም የአካል ሥርዓት ከመጠን በላይ በሥራ ይጠመዳል። CGAmh 367.4

ከሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም ወይም የተወሰነ ሥራ ለመፈጸም ተብሎ የምግብ ሰዓት በአንድ ወይም በሁለት ሰዓታት ሊዘገይ አይገባውም። ጨጓራ መመገብ በለመደበት ጊዜ ነው ምግብ የሚጠይቀው፡፡ ያ ጊዜ ከዘገየ የአካል ስርዓት ጥንካሬ እየቀነሰ በመጨረሻም የምግብ ፍላጎቱ ሙሉ በሙሉ እስኪጠፋ ድረስ በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይደርሳል፡፡ ከዚያ በኋላ ምግብ ከተወሰደ ጨጓራ በአግባቡ ሊያስተናግደው አይችልም፡፡ ምግብ ወደ ጥሩ ደም ሊለወጥ አይችልም፡፡ ሁሉም ሰዎች በመደበኛው ሰዓት የሚመገቡ ከሆነ በምግብ መካከል ምንም የማይቀምሱ ከሆነ ለመመገብ ዝግጁ ይሆናሉ እናም ለጥረታቸው ዋጋቸውን የሚከፍለውን በመመገብ ደስተኞች ይሆናሉ፡፡ 744 CGAmh 368.1

ልጆችን መቼ፣ እንዴት እና ምን መመገብ እንዳለባቸው አስተምሯቸው— ልጆች በአጠቃላይ መቼ፣ እንዴት፣ እና ምን መመገብ እንዳለባቸው አስፈላጊ ስለ መሆኑ አይማሩም፡፡ እነርሱ የምግብ አምሮታቸውን በነፃነት እንዳሻቸው እንዲያደርጉ፣ በማንኛውም ሰዓት እንዲመገቡ፣ ዓይኖቻቸውን ከፈተነም ፍራፍሬ እንዲመገቡ ይረዳሉ፤ እንዲሁም ይሄ፣ ከቂጣ፣ ኬክ፣ ዳቦ፣ ቅቤ እና ሁል ጊዜ በሚባል መልኩ በሚበላ ጣፋጭ ሥጋ ጋር ሲሆን ከርሳም እና የምግብ መፈጨት ችግር ያለባቸው ያደርጋቸዋል፡፡ ምግብን የሚፈጩ አካላት ልክ ያለማቋረጥ እንደሚሰራ ወፍጮ ይዝላሉ፣ ከመጠን በላይ እየሰራ ያለውን ጨጓራ ለመርዳት ከአእምሮ አስፈላጊ ኃይል ይመጣል፣ በዚህም መንገድ የአእምሮ ኃይሎች ይደክማሉ፡፡ ከተፈጥሮ ውጭ የሆነ ማነቃቂያ እና የሕይወት ኃይሎች መዛል ብስጩ፣ አንድ ነገር ሲከለከሉ ትዕግስ የለሾች፣ ግትር እና ቁጡዎች ያደርጋቸዋል፡፡ ከወላጆቻቸው እይታ ውጭ ሲሆኑ ብዙም ሊታመኑ አይችሉም፡፡ በብዙ ሁኔታዎች ሥነ ምግባራዊ ኃይሎች የሞቱ ይመስላሉ፣ በመሆኑም የኃጢአትን ኃፍረት እና አስከፊ ባህሪ እንዲሰማቸው እነርሱን ማንቃት ከባድ ይሆናል፤ እነርሱ ወደ ሕገ-ወጥነት ልማዶች፣ ወደ ማታለል እና ብዙውን ጊዜ ወደ ግልጽ ውሸቶች በቀላሉ ይንሸራተታሉ፡፡ CGAmh 368.2

ወላጆች እነዚህን ነገሮች በልጆቻቸው ላይ በማየታቸው ያዝናሉ፣ ነገር ግን ክፋትን ያመጣው የራሳቸው መጥፎ አስተዳደር መሆኑን አይገነዘቡም፡፡ እነርሱ የልጆቻቸውን ፍላጎቶች እና ምኞቶችን የመገደብ አስፈላጊነትን አልተመለከቱም፣ በመሆኑም ከዕድሜያቸው ጋር አድገዋል፣ ተጠናክረዋልም፡፡ እናቶች አካልና አእምሮን የመጉዳት ዝንባሌ ያላቸውን ምግቦች በገዛ እጃቸው በማዘጋጀት በልጆቻቸው ፊት ያቀርባሉ፡፡ 745 CGAmh 369.1

በምግብ ክፍለ ጊዜ መካከል በጭራሽ አትመገቡ— ጨጓራ ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት ማግኘት አለበት፡፡ ያለማቋረጥ እንዲሰራ መደረግ የለበትም፡፡ ይህ አላግባብ ጥቅም ላይ የዋለ እና ብዙ በደል የተፈጸመበት አካል ትንሽ የጸጥታ እና የእረፍት ጊዜ ይሰጠው ...፡፡ CGAmh 369.2

መደበኛው ምግብ ከተበላ በኋላ ጨጓራ ለአምስት ሰዓታት እንዲያርፍ ሊደረግ ይገባል፡፡ እስከሚቀጥለው የምግብ ክፍለ ጊዜ ድረስ አንድ የምግብ ቅንጣት ጨጓራ ውስጥ መግባት የለበትም፡፡ በዚህ የጊዜ ክፍተት ውስጥ ጨጓራ ሥራውን ያከናውንና ከዚያ ተጨማሪ ምግብ መቀበል በሚያስችለው ሁኔታ ላይ ይሆናል፡፡ 746 CGAmh 369.3

እናቶች (ልጆቻቸው) በምግብ መካከል እንዲመገቡ በመፍቀድ ትልቅ ስህተት ይፈጽማሉ፡፡ በዚህ ተግባር ጨጓራ ይቃወሳል፣ ለወደፊት መከራም መሠረት ይጣላል፡፡ ቁጡ መሆናቸው እስከ አሁንም ድረስ ባልተፈጨ ጤናማ ባልሆነ ምግብ ሳቢያ የተከሰተ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እናት ጉዳዩን ለማመዛዘን እና ጎጂ አያያዟን ለማስተካከል ጊዜ ማጥፋት እንዳለባት አይሰማትም፡፡ ወይም እርሷ ትዕግሥት አልባ ጭንቀታቸውን ማረጋጋት አትችልም፡፡ ችግር ላይ ያሉ ትናንሽ ልጆችን ዝም ለማሰኘት አንድ ኬክ ወይም ሌላ የቅምጥልና ምግብ ትሰጣቸዋለች፣ ነገር ግን ይህ ክፋቱን ያባብሳል...፡፡ CGAmh 369.4

እናቶች ብዙውን ጊዜ ጥቂት የማመዛዘን ችሎታቸውን ቢጠቀሙ ኖሮ ችግሩ በአመዛኙ በአመጋገብ ስህተቶች የተፈጠረ መሆኑን ማየት ሲችሉ ስለ ልጆቻቸው ደካማ ጤንነት ቅሬታ በማሰማት ሐኪም ያማክራሉ። 747 CGAmh 369.5

“እራትን” ዘግይተው የመመገብ ክፉ ልማድ— ሌላው አስከፊ ልማድ ልክ ከእንቅልፍ በፊት መመገብ ነው። መደበኞቹ ምግቦች ተወስደው ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን የዝለት ስሜት ስለሚፈጠር ተጨማሪ ምግብ ይወሰዳል፡፡ ይህን የስህተት ተግባር በማፈጸም ልማድ ይፈጠር እና ብዙውን ጊዜ እጅግ የበረታ ስለሚሆን ያለ ምግብ መተኛት አይቻልም ተብሎ ይታሰባል፡፡ ዘግይቶ እራት በመመገብ ሳቢያ የምግብ መፈጨት ሂደት በእንቅልፍ ሰዓቶች ውስጥ ይቀጥላል፡፡ ነገር ግን ጨጓራ ያለማቋረጥ የሚሠራ ቢሆንም ሥራው በትክክል አይከናወንም፡፡ እንቅልፍ ብዙውን ጊዜ ደስ በማያሰኙ ሕልሞች ይረበሻል፣ ጠዋት ላይ ሰውየው ያልታደሰ፣ ለቁርስም ብዙም ፍላጎት የሌለው ይሆናል፡፡ ለማረፍ በምንተኛበት ጊዜ ጨጓራ እንዲሁም ሌሎች የሰውነት አካላት እረፍትን ያጣጥሙ ዘንድ ጨጓራ ሥራውን በሙሉ ሰርቶ መፈፀም አለበት፡፡ ሥራቸውን ሳይንቀሳቀሱ የሚያከናውኑ ሰዎች ከረፈደ በኋላ የሚበሉ እራቶች በተለይም ጎጂዎች ናቸው፡፡ በእነርሱ ዘንድ የተፈጠረው መረበሽ ብዙውን ጊዜ በሞት የሚያበቃ የበሽታ ጅማሮ ነው፡፡ 748 CGAmh 370.1

ቁርስ አስፈላጊ ስለ መሆኑ የተመከረች እናተ— ልድሽ ቁጡ ባሕርይ ስላላት አመጋገቧ በጥንቃቄ ሊታይ ይገባል። ተገቢ ምግብ ሳይኖረው የምግብ አምሮቷን ብቻ የሚያረካ ምግብ እንድትመርጥ ሊፈቀድላት አይገባም...፡፡ ቁርስዋን ሳትበላ ከቤት ወደ ትምህርት ቤት እንድትሄድ በጭራሽ አትፍቀጂላት፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ለዝንባሌዎችሽ ሙሉ ኃላፊነት ለመስጠት አትሞክሪ፡፡ እራስሽን ሙሉ በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጥጥር ስር አድርጊ፣ እርሱም ምኞሽን ሁሉ ከእርሱ መስፈርቶች ጋር እንዲጣጣም ይረዳሻል። 749 CGAmh 370.2

አነስተኛ ቁርስ መመገብ የህብረተሰቡ ልማድ እና ስርዓት ነው፡፡ ነገር ግን ጨጓራ የሚያዝበት የተሻለ መንገድ ይህ አይደለም፡፡ በቁርስ ሰዓት ከቀኑ ከሁለተኛው ወይም ከሦስተኛው ምግብ ጊዜ የበለጠ ምግብን ለመፍጨት ጨጓራ በተሻለ ሁኔታ ላይ ይሆናል፡፡ አነስተኛ ቁርስ እና ብዙ እራት የመመገብ ልማድ የተሳሳተ ነው፡፡ ቁርሳችሁን የዕለቱ ትልቅ የምግብ ጊዜያችሁ አድርጉ፡፡ 750 CGAmh 370.3

የተትረፈረፈ ምርጥ ምግቦችን አቅርቡ— ልጆች እና ወጣቶች በምንም አይነት ሁኔታ ከሚፈለገው መጠን በታች መመገብ የለባቸውም፤ የተትረፈረፈ ጤናማ ምግብ ሊኖራቸው ይገባል፣ ነገር ግን ይህ ማለት ቅመማ ቅመም የበዛባቸውን ኬኮች እና ፓስቲዎች ከፊት ለፊታቸው መቅረብ አለበት ማለት አይደለም፡፡ በጣም ጥሩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ምርጥ ምግብ ሊኖራቸው ይገባል፣ ምክንያቱም እነዚህ በአእምሮ እና በሥነ-ምግባር ኃይሎች ሁኔታ ላይ ጠቃሚ ተጽዕኖ አላቸው፡፡ ተገቢ እና ጤናማ አመጋገብ ጤናማ የምግብ መፍጨት ከሚገኝባቸው መንገዶች አንዱ ይሆናል፡፡ 751 CGAmh 371.1

ተገቢ በሆነ መጠን ይህንን ተመገቡ— ወላጆች ብዙውን ጊዜ ለልጆቻቸው ከመጠን በላይ የሆነ ምግብ በመስጠት ስህተት ይሰራሉ፡፡ በዚህ መንገድ የተያዙ ልጆች የምግብ መፈጨት ችግር ይዘው ያድጋሉ፡፡ ጥሩ ምግብን እንኳን በመጠኑ መጠቀሙ አስፈላጊ ነው። ወላጆች፣ መብላት የሚገባቸውን መጠን ከልጆቻችሁ በፊት አኑሩ፡፡ የሚሰማቸውን ያህል ይመገቡ ዘንድ ለእነርሱ አትተው...፡፡ ወላጆች፣ ይህ ነጥብ ካልተጠበቀ በስተቀር ልጆቻችሁ የደነዘ ግንዛቤ ይኖራቸዋል፡፡ ትምህርት ቤት ሊከታተሉ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን የሚገባቸውን ያህል መማር አይችሉም፤ ምክንያቱም ወደ አንጎል መሄድ ያለበት ጥንካሬ ጨጓራ የተጫነበትን ተጨማሪ ምግብን በመንከባከብ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ለልጆች የሚሰጠው እጅግ ብዙ ምግብ ጠንካራ ከመሆን ይልቅ ደካማ እንደሚያደርጋቸው ወላጆች መማር አለባቸው፡፡752 CGAmh 371.2

ውሳኔ መስጣት ያለባቸው ወላጆች እንጂ ልጆች አይደሉም— የምግብ አምሮትን እንዲክዱ፣ እግዚአብሔር ለሚሰጣቸው ቅመማ ቅመም ያልበዛበት እና ቀላል ምግብ አመስጋኝ እንዲሆኑ አስተምሯቸው። ምን መብላት እንዳለበቸው እነርሱ እንዲወስኑ መፍቀድ ሳይሆን ለእነርሱ የሚበጀውን እናንተ መወሰን አለባችሁ፡፡ ልጆቻችሁ ከተበላሸው የምግብ አምሮታቸው ጋር ስለማይጣጠም ጥሩ ጤናማ ምግብ ላይ እንዲያጉረመርሙ እና ቅሬታ እንዲያቀርቡ መፍቀድ ኃጢአት ነው፡፡ 753 CGAmh 371.3

ልጅ ልጅ ስለሆነ ብቻ፣ የራሱን መንገድ እንዲመርጥ እና መምራት እንዳለበት እንዲሰማው አትፍቀዱለት። እርሱ ስለወደዳቸው ብቻ የማይጠቅሙት የምግብ አይነቶችን እንዲመርጥ ሊፈቀድለት አይገባም፡፡ የወላጆች ተሞክሮ በልጁ ሕይወት ላይ የመቆጣጠር ኃይል ሊኖረው ይገባል፡፡ 754 CGAmh 372.1

ምክንያታዊ ከሆነ የልጁን ምርጫ አክብሩ— ህይወታችን በአእምሮ ወይም በአካል ቁጥጥር ስር እንደሚሆን መወሰን በየግላችን በእኛ ላይ የሚያርፍ ኃላፊነት ነው። ወጣቱ ሕይወቱን የሚቀርፅበትን ምርጫ እያንዳንዱ ለራሱ ማድረግ አለበት፤ ደግሞም እርሱን የሚገጥሙትን ኃይሎች፣ ባህሪይውን እና ዕጣ ፈንታውን የሚቀርጹ ተጽዕኖዎችን ይረዳ ዘንድ ምንም ጫና ሊያርፍበት አይገባም፡፡ 755 CGAmh 372.2

በልጆችና ወጣቶች ትምህርት ላይ በዓለም የመለኪያ ደረጃ የተፈጠሩ የአመጋገብ፣ የመጠጥ እና የአለባበስ ልምዶች ከጤና እና ከህይወት ህጎች ጋር የማይስማሙ እና በምክንያታዊነት እና በአዕምሮ ቁጥጥር ስር ሊውሉ እንደሚገባ መማር አለባቸው፡፡ የምግብ ፍላጎት እና የልምድ ጥንካሬ ምክንያታዊነትን እንዲያሸንፉ ሊፈቀድላቸው አይገባም፡፡ ይህንን ዓለማ ለማሳካት ወጣቱ በአመጋገብና በመጠጥ ከእንስሳት እርካታ የበለጠ ዓላማና ተነሳሽነት ሊኖረው ይገባል፡፡ 756 CGAmh 372.3

የተዛባ የምግብ ፍላጎት አድመሰ-ሰፊዎቹ ውጤቶች—አንዳንዶች ለእግዚአብሔር ክብር የመብላት እና የመጠጣት አስፈላጊነት አይሰማቸውም፡፡ የምግብ አምሮትን ልቅ ማድረግ ሁሉንም የሕይወት ግንኙነቶቻቸውን ይነካል፡፡ ይህ በቤተሰብ፣ በቤተክርስቲያን፣ በጸሎት ስብሰባ እና በልጆቻቸው ምግባር ላይ ይታያል፡፡ እርሱም የሕይወታቸው እርግማን ነው፡፡ ይህም ለእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ያለውን እውነት እንዳይረዱ ያደርጋቸዋል፡፡ 757 CGAmh 372.4

የግለሰብ ግዴታ የሆነው ጤናማ ኑሮ— የምንበላው እና የምንጠጣው በሕይወታችን እና በባህሪያችን ላይ ወሳኝ ተጽዕኖ ያሳድራል፣ በመሆኑም ክርስቲያኖች የአመጋገብ እና የመጠጥ ልምዳቸውን ከተፈጥሮ ህጎች ጋር እንዲስማሙ ማድረግ አለባቸው፡፡ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ለእግዚአብሔር ያለንን ግዴታዎች ማስተዋል አለብን፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ በፈቃደኝነት አላዋቂ መሆን ኃጢአት በመሆኑ ለጤና ህጎች መታዘዝ በጥልቀት ጥናት ሊደረግበት የሚገባ ጉዳይ መሆን አለበት፡፡ እያንዳንዳቸው የጤናማ የአኗኗር ህጎችን የማስፈፀም ግላዊ ግዴታ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ 758 CGAmh 372.5