ቀደምት ጽሑፎች
6—የሰማያዊው ኃይላት መናወጥ
በወርሃ ታህሳስ 16/1848 ዓ.ም. ላይ ጌታ ሰማያዊው ኃይላት የተናወጡበትን ራእይ ሰጠኝ፡፡ ጌታ ሰማይ” ብሎ ሲናገር በማቴዎስ፣ በማርቆስና በሉቃስ ወንጌሎች ላይ የተጠቀሱትን ምልክቶች በመስጠት ሰማይ በማለት መናገሩ ሲሆን---‹ምድር» ሲል ይህችኑ ምድር መጥቀሱ አንደሆነ ተመልክቼአለሁ:: ስማያዊ ኃይላት ማለት ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ናቸው፡፡ እነርሱ በሰማያት ውስጥ ሆነው ይገዛሉ የምድር ኃይላት ደግሞ በምድር ላይ የሚገዙት ናቸው:: ሰማያዊው ኃይላት የሚናወጠ ት በእግዚአብሔር ድምጽ ሲሆን በዚህም---ጸሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት ስፍራዎ ቻቸውን ይስታሉ፡፡ የማያልፉ ቢሆንም ነገር ግን በእግዚአብሔር ድምጽ ይናወጣሉ፡፡ EWAmh 25.1
ጥቋቁርና ግዙፍ ደመናዎች በመምጣት እርስ በርሳቸው ተጋጩ ይህን ተከትሎ ከባቢው አየር ለሁለት ተሰንጥቆ ወደ ኋላ ተጠቅልሎ ተመለስ፡፡ ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ድምጽ በመጣበት በተሸነቆረው ቀዳዳ በኦሪየን ውስጥ ማየት ቻልን፡፡ ቅድስቲቱ ከተማ ወደ ምድር የምትወርደው በዚያ ሽንቁር በኩል ነው፡፡ በዚህን ወቅት የምድር ኃይላት መናወጣቸውንና እነዚያ ክስተቶች ሥርዓታቸውን ጠብቀው እየመጡ መሆኑን ተመለከትኩ፡፡ ጦርነትና የጦርነት ወሬ፣ ረኃብና ቸነፈር በመጀመሪያ የምድርን ኃይላት ማናወጣቸው የግድ ነው፡፡ ከዚያም የእግዚአብሔር ድምጽ ጸሐይን፣ ጨረቃንና ከዋክብትን እንዲሁም ይህን ምድር ያናውጣል፡፡ በአወሮፓ የነበረው የኃይላት መናወጥ አንዳንዶች እንደሚያስተምሩት የሰማያዊው ኃይላት መናወጥ ሳይሆን ነገር ግን በቁጣ የገነፈሉ መንግሥታት ነውጥ መሆኑን ተመልክቼአለሁ፡፡ EWAmh 25.2