ቀደምት ጽሑፎች
7—የተከፈተውና የተዘጋው በር
ወርሃ መጋቢት 24/1849 ዓ.ም:፡፡ ዕለቱ ሰንበት እንደመሆኑ ከወንድሞች ጋር በቶፕሻም ሜይን ጣፋጭና አስደሳች ፕሮግራም ነበረን፡፡ መንፈስ ቅዱስ በላያችን ወርዶ ነበር እኔም በመንፈስ ወደ ሕያው አምላክ ከተማ ተወሰድኩ፡፡ ከዚያም የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና የየሱስ ክርስቶስ ምስክር ከተዘጋው በር ጋር ተለያይቶ ሊቀመጥ እንደማይችል ተመለከትኩ፡፡ የእግዚአብሔር ትእዛዛት ከነሙሉ አስፈላጊነታቸው የሚያበሩበትና የእግዚአብሔር ሕዝቦች በሰንበት እውነት ዙሪያ የሚፈተኑበት ጊዜ አስርቱን ትእዛዛት የያዘው ታቦቱ ያለበት የቅድስተቅዱሳኑ ሰማያዊ ቤተመቅደስ ክፍል በተከፈተበት ወቅት እንደነበር ተመልክቼአለሁ፡፡ ይህ በር በቅዱሱ የመቅደሱ ክፍል የየሱስ የምልጃ አገልግሎት ፍጻሜ እስካገኘበት 1844 ዓ.ም ድረስ አልተከፈተም ነበር፡፡ ከዚያም የሱስ የቅዱሱን ስፍራ በራፍ በመዝጋት የቅድስተቅዱሳኑን ክፍል ከፍቶ በታቦቱ አጠገብ ወዳለው አሁን ወደሚገኝበትና የእስራኤል እምነት ወደሚደርስበት ሁለተኛው መጋረጃ አልፎ ገባ፡፡ EWAmh 26.1
የሱስ የቅዱሱን ክፍል በራፍ ዘግቶት እንደነበር ተመለከትኩ፡፡ ይህን በር ማንም ሊከፍተው አይችልም ነበር፡፡ ከዚያም የቅድስተቅዱሳኑን ክፍል ከፍቶ ገባ ይህንንም በር እንዲሁ ማንም ሊዘጋው አይችልም ነበር (ራእ. 3፡፡78)፡፡ የሱስ ታቦቱ ወደ ሚገኝበት የቅድስተቅዱሳኑ ክፍል እንደመግባቱ ትእዛዛቱ ለእግዚአብሔር ሕዝቦች ያንጸባርቁ ነበር.ሰንበት ጥያቄ ዙሪያም እንዲፈተኑ ሆኑ፡፡ EWAmh 26.2
አሁን በሰንበት ዙሪያ ያለው ፈተና የየሱስ የቅዱሱ ክፍል የምልጃ አገልግሎት ፍጻሜ አግኝቶ ወደ ሁለተኛው መጋረጃ አልፎ እስከሚገባ ድረስ ሊመጣ እንደማይችል ተመልክቼ ነበር፡፡ በመሆኑም እውነተኛውን ሰንበት ያልጠበቁ---በሰባተኛው ወር 1844 ዓ.ም. ላይ የቅድስተቅዱሳኑ በራፍ ከመከፈቱ አስቀድሞ በእኩለ ሌሊቱ ጩኸት ማብቂያ ላይ ያንቀላፉ ክርስቲያኖች እነሆ አሁን ተስፋ ኖሮአቸው ያርፋሉ፡፡ ነገር ግን ያ በር ከተከፈተአንስቶ እኛ ያለን የሰንበት ብርሃንም ሆነ ፈተና አልነበራቸውም፡፡: በዚህ ርዕሰ ነጥብ ዙሪያ ሰይጣን አንዳንድ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች እየፈተነ እንደነበር ተመልክቼአለሁ፡፡ አያሌ መልካም ክርስቲያኖች ሰንበትን ሳይጠብቁ በእምነታቸው ድልን ተጎናጽው በማንቀላፋታቸው ሰንበት አሁን ለእኛ ፈተና የመሆኑን ነገር እነዚህ ሕዝቦች እየተጠራጠሩ ነበር፡፡ EWAmh 26.3
የወቅታዊው እውነተጠላቶች---የሱስ የዘጋውን የቅዱሱን ስፍራ በር ለመክፈትና እርሱ በ1844 ዓ.ም. ላይ የከፈተውን በያህዌ ጣት የተጻፉት አስርቱ ትእዛዛት የሚገኙበትን የቅድስተቅዱሳኑን በር መዝጋት እየሞከሩ ነው፡፡ EWAmh 27.1
በዚህ የመታተም ወቅት የእግዚአብሔር ሕዝቦች ከጊዜያችን እውነት እንዲርቁና እንዲዋልሉ ለማድረግ ሰይጣን እያንዳንዱን መሣሪያ በመጠቀም ላይ ይገኛል፡፡ ከሚመጣው የመከራ ወቅት ለመጠበቅ ሲል እግዚአብሔር ሕዝቡን ለማልበስ ያዘጋጀውን መሸፈኛ ተመልክቼ ነበር፡፡ ደግሞም በእውነት ላይ ውሳኔዋን ያደረገችና ንጹህ ልብ ያላት እያንዳንዷ ነፍስ ኃያል በሆነው አምላክ ተሸፍና ነበር EWAmh 27.2
ይህን ያውቅ የነበረው ሰይጣን የብዙዎች አእምሮ በዚህ እውነት ላይ እንዳይጸና በማድረግ የተቻለውን ያህል በሙሉ ኃይሉ እየሠራ ነበር፡፡ በኒው ዮርክ እና በሌሎች ስፍራዎች የተስተዋለው ስውር የቤተክርስቲያንን ደጃፍ የማንኳኳት ደባ የመነጨው ከስይጣን ኃይል መሆኑን ተመልክቻለሁ:፡፡ በሌ ሎች ዘንድ ከፍ ያለ ተቀባይነትን ለማግኘት ያስችላቸው ዘንድ እነዚያን የተታለሉትን እሹሩሩ እያሉ በማባበልና የሚቻልም ከሆነ የእግዚአብሔርን ሕዝቦች አእምሮ በመሳብ የመንፈስ ቀዱስን አስተምህሮና ኃይል እንዲጠራጠሩ የማድረጉ እንዲህ ያለት ኃይማኖታዊውን ካባ በመደረብ የሚፈጸሙ ተግባራት ወደፊት ይበልጥ እየተለመዱ ይሄዳሉ፡፡ EWAmh 27.3
ሰይጣን በወኪሎቹ አማካኝነት በብዙ መንገዶች ሲሠራ ተመልክቼአለሁ፡፡: እርሱ እውነትን በተቃወሙ አገልጋዮች አማካኝነት በሥራ ላይ የነበረ ሲሆን እነዚህ አገልጋዮች በሠሯቸው ስህተቶች ላይ ኩነኔ ሊያስከትሉባቸው የሚችሉ ሌሎች ከፍተኛ ሐሰቶች ተሰጥተዋቸዋል እነርሱ እየሰበኩ ወይም እየጸለዩ ሳለ አንዳንዶች ተዘርግተው ይወድቁ ነበር፡፡ ይህ ይሆን የነበረው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሳይሆን ነገር ግን በእነዚህ ወኪሎቹ ላይ እፍ ባለባቸው በሰይጣን ኃይል አማካኝነት ነው:፡፡ ደግሞም ከእነርሱ ወደ ሕዝቡ ይዛመታል: ለዚህ ዘመን የተሰጠውን ወቅታዊ እውነት የማይቀበሉ አንዳንድ አስመሳይ አድቬንቲስቶች ሲሰብኩ፣ ሲጸልዩ ወይም ንግግር ሲያደርጉ ደጋፊዎች ለማግኘት ሲሉ በስመመን ላይ መሆንን ይጠቀማሉ፡፡ ሕዝቡም መንፈስ ቅዱስ ነው ብሎ ስለሚያስብ በዚህ ዓይነቱ ተጽእኖ ደስ ይሰኛል፡፡ ነገር ግን ይለማመዱት ዘንድ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ኃይል እንደሆነ አድርገው በማመን እነዚህን ነገሮች የተጠቀሙ አንዳንዶች ዛሬም በጨለማና በዲያብሎስ ስህተት ውስጥ አሉ፡፡ እግዚአብሔርን በራሳቸው በመወሰን የእርሱን ኃይል እንደ ምናምንቴ ቆጥረውታልና፡፡ EWAmh 27.4
የሰይጣን ወኪሎች በሰይጣናዊው ተጽእኖ ስር በመጣል ሊያስቷቸውና ከእውነት ፈቀቅ ሊያደርጓቸው ያልቻሏቸውን ቅዱሳን እነዚህ ሰዎች ያውኩ ነበር፡፡ እግዚአብሔር የገለጠልኝን ይህን የሰይጣንን ማታለያ ዘዴ ሁሉም መመልከት ቢችሉና ከዚህ ቢጠበቁ ምንኛ ግሩም ነው፡፡ አሁን-በዚህ በመታተም ወቅት ሰይጣን እነዚህን መንገዶች በመከተል የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ሊያጠፋ፣ ሊያስትና ከእርሱ ሊያርቅ በሥራ ላይ መሆኑን ተመልክቼአለሁ: ለወቅታዊው እውነት በጽናት ያልቆሙ አንዳንዶችን ተመልክቼ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በእውነት ላይ አለመተhላቸውን ተከትሎ ጉልበቶቻቸው ይብረhረኩ እግሮቻቸውም ይዳልጡ ነበር፡፡ ይህ መደነቃቀፋቸው የኃያሉ አምላክ ከለላ አንዳይሸፍናቸው መንስዔ ነበር፡፡ EWAmh 28.1
የመታተም ጊዜ አስኪያልፍ፣ የእግዚአብሔር ሕዝቦች በእርሱ ከለላ ተሸፍነው ከሚነደው አምላካዊ ቁጣ ያለ መጠለያ ከመቅረታቸው በፊትና የመጨረሻዎቹ ሰባት መቅሰፍቶች ከመውረዳቸው ቀደም ባሉት ጊዜያት፤ ሰይጣን እነርሱን ባሉበት ይዞ ለማስቀረት የማይፈነቅለው ድንጋይ አልነበ ረም፡፡ እግዚአብሔር አምላካዊውን ሽፋን በሕዝቡ ላይ ማድረግ ጀምሮአል፡፡ ደግሞም ሁሉም እንዲገደሉ ትእዛዝ በሚወጣበት ዕለት እንደ ጋሻ ይሸፍናቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ለሕዝቡ በኃይል የሚሠራ ሲሆን ሰይጣንም እንዲሁ ይሠራ ዘንድ ይፈቀድለታል: EWAmh 28.2
ምስጢራዊ ምልክቶች፣ አስገራሚ ትዕይንቶችና የሐሰት ተሐድሶዎች እየጨመሩና እየተስፋፉ እንደሚሄዱ ተመልክቻለሁ: እኔ በራእይ እንዳያቸው የተደረጉ ተሐድሶዎች ከስህተት ጅማሮ ወደ እውነት የመጡ አልነበሩም:፡፡ አብሮኝ የነበረው መልአክ በኃጢአተኛው ላይ የሚደርሰውን ሥቃይ እንድመለከት ጋበዘኝ፡፡ ነገር ግን የደኅነታቸው ጊዜ አልፎ ስለነበር ብመለከትም መረዳት አልቻልኩም ነበር -- EWAmh 28.3
[የእነዚህ መልእክቶች ጸሐፊ በዚህ ወቅት የመላው ኃጢአተኞች የደኅንነት ጊዜ የማለፉን ኃይማኖታዊ አስተምህሮ አላስተዋለችም ነበር እነዚህ ነገሮች እየተጻፉ በነበሩበት ወቅትእርሷ እስከ መጨረሻው ትሠራው የነበረውንኛለኃጢአተኞች ደኅንነት እየሠራች ነበር፡፡ ለእርሷ በተሰጣት መሰረት ጉዳዩን ያስተዋለችበት መልእክት በተከታዮቹ አንቀጾች የቀረቡ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የታተሙት በ1854 ዓ.ም---ሁለተኛው ዕትም ደግሞ 1888 ዓ.ም. ላይ ነበር:: «እዚህ ላይ የተጠቀሱት ‘ሐሰተኛ ተሐድሶዎች ሙሉ ለሙሉ እየጎሉ የሚሄዱ ነበሩ፡፡ ይህ ምልክታ በተለይ የሚያጠነጥነው የአድቬንቲስትን ኃይማኖታዊ አስተምህሮ እውነትን ሰምተው ብርኑን በተቃወሙት ዙሪያ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች ለጠንካራ ማታለያ ተላልፈው ተሰጥተዋል፡፡ ሆኖም ይህ ከላይ በቀረበው አንቀጽ የተጠቀሰውን በኃጢአተኛው ላይ የሚደርሰውን ሥቃይ አያካትትም፡፡ የአድቬንቲስትን መልእክት በመቃወም ለሰይጣን ማታለያ ተላልፈው በመሰጠታቸው የደኅንነት ጊዜአቸው ማለፉ’---የዳግም ምጽአቱን ኃይማኖታዊ አስተምህሮ ካልሰሙና ካልተቃወሙ ጋር ዝምድና የለውም፡፡» EWAmh 28.4
«አእምሮአችንን ካሳመነንና ልቦቻችንን ከነካን እውነት ቀስ በቀስ እያፈገፈጉ መሄድ አስፈሪ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔር በምህረቱ የሚልክልንን ማስጠንቀቂያዎች ንጽህና በጎደለው መልኩ ልንቃወም አንችልም:: በኖህ ዘመን መልእክት ከሰማይ ወደ ምድር ተልኮ የነበረ ሲሆን በወቅቱ የሰዎች ደኅንነት መተማመን አድርጎ የነበረው በእነርሱ መቀበል ወይም አለመቀበል ላይ ነበር፡፡ በመሆኑም እነዚህ ሕዝቦች ማስጠንቀቂያውን በመቃወማቸው የእግዚአብሔር መንፈስ ከኃጢአተኛው ዘር ተለየ በውሃ ጥፋትም ወደሙ በአብርሃም ዘመን ኃጢአተኞች ሆነው በተገኙት የሶዶም ነዋሪዎች ላይ ምኅ ረት መውረድ በማቆሙ ከሎጥና ሚስቱ እንዲሁም ከሁለት ሴቶች ልጆቹ በቀር ሌሎቹ ከሰማይ በተላከ እሳት ተበልተው ጠፉ፡፡ በክርስቶስ ዳግም ምጽአትም እንዲሁ ይሆናል፡፡ የሰው ልጅ ልበ ደንዳና ለነበሩት አይሁዳውያን ‘ቤታችሁ የተፈታ ሆኖ ይቀራል’ ነበር ያላቸው፡፡ ወደ ምድር የመጨረሻዎቹ ቀናት በመመልከት ሊያድናቸው የሚችለውን የእውነት ፍቅር ስላልተቀበሉት’ ሕዝቦች ያው ዘላለማዊ ኃይል ሲናገር እነዚያ እውነትን ያላመኑና ጻድቅ ባልሆነው ነገር ደስታ የነበራቸው ሁሉ ይኮነኑ ዘንድ ሐሰትን እንዲያምኑ እግዚአብሔር ጠንካራ ማሳሳቻ ይስድባቸዋል:’ እነዚህ ሐዝቦች የእርሱን ቃል አስተምህሮ ሲቃወሙ ሳለ እግዚአብሔር መንፈሱን ከእነርሱ በማንሳት በዚያ ባፈቀሩት ነገር ይታለi ዘንድ ይተዋቸዋል] EWAmh 29.1