ቀደምት ጽሑፎች

6/73

5—እግዚአብሔር ለህዝቡ ያለው ፍቅር

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ያለውን የተለሳለሰ ታላቅ ፍቅርና መላእክት ክንፎቻቸውን ዘርግተው በቅዱሳኑ ዙሪያ ሲበሩ ተመልክቼአለሁ፡፡: እያንዳንዱ ቅዱስ አንድ ጠባቂ መላዕክ ነበረው፡፡ ቅዱሳኑ ተስፋ መቁረጥ ደርሶባቸው ወይም በአደጋ ላይ ሆነው ካነቡ እነርሱን የሚጠብቁ መላእክት መረጃውን ይዘው በፍጥነት ወደ ላይ የሚበሩ ሲሆንበከተማዋ የነበሩ መሳእክትም ዝማሬአቸውን ያቆማሉ፡፡ በዚህን ጊዜ የሱስ የሚያበረታታ፣ የሚጠብቅና ከጠባቡ መንገድ አፈትልከው እንዳይወጡ የሚንከባኩn ሌላ አጽናኝ መልአክ ይልካል፡፡ ነገር ግን ጥንቃቄ ለተሞላው ለእነዚህ የመላእክቱ ጥበቃ ግድ የማይላቸው ከሆነና በእነርሱ ህልዎት ምቾት በማጣት በተያያዙት የጥፋት ጎዳና የሚገፉበት ከሆነ መላእክተያዝናሉ የለቅሱማል፡፡ ይህን አሳዛኝ ዜና ወደ ላይ ይዘው ይወጣሉ፡፡ በከተማዋ ያሉ መላእክት ሁሉ ያነቡና ከፍ ባለ ድምጽ «አሜን» ይላሉ፡፡ ነገር ግን ቅዱሳኑ ዐይኖቻቸውን በተዘጋጀላቸው ሽልማት ላይ የሚያደርጉና እግዚአብሔርን በማመስገን ለእርሱ ክብር የሚሰጡ ከሆነ፡፡ በዚህን ጊዜ መላእክት የደስታ የምሥራች ይዘው ሽቅብ ወደ ከተማዋ ይተማሉ፡፡ ከዚያም በከተማዋ ያሉ መላእክት ወርቃማ በገናዎ ቻቸውን በመንካት «ሐሌሉያ” በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ይዘምራሉ፡፡ EWAmh 23.1

በቅዱሷ ከተማ ፍጹም የሆነ ሥርዓትና ውህደት አለ፡፡ ምድርን እንዲጎበኙ የሚላኩ መላእክት በሙሉ ከሰማያዊው ከተማ ሲወጡና ሲገቡ በራፍ ላይ ላሉት መላእክት የሚያሳዩትን ወርቃማ ካርድ ይይዛሉ፡፡ ሰማይ ግሩም ስፍራ ነው፡፡ በዚያ በመሆን ህይወቱን ለእኔ የሰጠኝንና ወደ እርሱ ባለክብር አምሳል የቀየረኝን ተወዳጁን የሱሴን ማየት እናፍቃለሁ፡፡ ምናለ የዚህን ብሩህ ዓለም ክብር የሚገልጽ ቋንቋ በመጣ! የአምላካችንን ከተማ በደስታ የሚሞሉትን ሕያው ምንጮች እጠማለሁ፡፡ EWAmh 23.2

ጌታ ሌሎች ዓለማትን ያየሁበትን ራይ ሰጥቶኛል፡፡: ከከተማዋ አንስቶ ብሩህና ባለ ግርማ እስከሆነው ስፍራ ድረስ የምበርባቸው ክንፎችና አብሮኝ የሚሆን መልአክ ተሰጥቶኝ ነበር በስፍራው የነበረው ሣር ብሩህ አረንጓዴ--የአዕዋፋቱም ዝማሬ እጅግ ጣፋጭ ነበር: በዚያ ምድር ይኖሩ የነበሩ ሕዝቦች ሁሉም ዓይነት መጠን ነበራቸው: ዝነኞች፣ ንሣዊና ተወዲጆችም ነበሩ:: የየሱስን አምሳል የተላበሱት እነዚህ ሕዝቦች--ቅዱስ የደስታ ጮራ የፈነጠቀበት የፊታቸው ገጽታ የነበራቸውን ነጻነትና የስፍራውን አስደሳችነት የሚገልጽ ነበር እነዚህ ሐዝቦች በምድር ካሉት በላቀ ተወዳጆች የሆኑበትን ምክንያት ይነግረኝ ዘንድ ከመካከላቸው አንዱን ጠየቅኩት እርሱም «እኛ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ፍጹም በሆነ መልኩ በመጠበቅ ከመኖር ውጪ በምድር እንዳሉት ባለመታዘዝ አልወደቅንም በማለት መለሰልኝ፡፡ ከዚያም በከተማው ሁለት ዛፎች የተመለከትኩ ሲሆን ከመካከላቸው አንደኛው የህይወትን ዛፍ ይመስል ነበር፡፡ የሁለቱም ዛፍ ፍሬዎች በእጅጉ የሚያምሩ ቢሆኑም ነገር ግን እነዚህ ነዋሪዎች የአንደኛውን ዛፍ ፍሬ አይበሉም ነበር፡፡ ምንም እንኳ ከሁለቱም ዛፎች ቀጥፈው የመብላት ኃይል ቢኖራቸውም ነገር ግን ከአንደኛው ዛፍ አንዳይበሉ ተከልክለው ነበር፡፡ ከዚያም አብሮኝ የነበረው መልአክ «በዚህ ስፍራ ካሉ ሕዝቦች መሃል አንዳቸውም እንኳ ከተከለከለው ፍሬ ቀምሰው አያውቁም፡፡ ቢበሉ ይወድቃሉ” በማለት ነገረኝ:፡፡ ከዚያም ሰባት ጨረቃዎች ወደ ነበሯት ምድር ተወሰድኩ በዚያ ስፍራ ከምድር ተለውጦ የተወሰደውን መልካሙን ሔኖክ ተመለከትኩ፡፡ ሔኖክ በቀኝ ክንዱ በግርማ የተሞላ ዘንባባ የያዘ ሲሆን በያንዳንዱ ቅጠል ላይ «ድል” የሚል ቃል ተጽፎበታል፡፡ በአናቱ አካባቢ ነጭና አንጸባራቂ የአበባ ጉንጉን--- በጉንጉኑ ላይ ደግሞ ቅጠሎች ነበሩ:፡፡ በእያንዳንዱ ቅጠል መካከል ላይ «ንጽህና” የሚል ተጽፎ ነበር ደግሞም በጉንጉኑ ዙሪያ ከከዋክብት ይልቅ የሚያንጸባርቁ የተለያዩ ቀለማት ያሏቸው ድንጋዮች የነበሩ ሲሆን እነርሱም በፊደሎቹ ላይ በማንጸባረቅ አጉልተዋቸው ነበር፡፡ በአናቱ ጀርባ በኩል ጉንጉኑን አቅፎ የያዘ እንደ ደጋን ዓይነት ነገር የነበረ ሲሆን በላዩ ላይ «ቅድስና” የሚል ጽሑፍ ነበረው፡፡ ከጉንጉኑ በላይ ከጸሐይ ይልቅ የሚያበራ ተወዳጅ ዘውድ ነበር ይህ ስፍራ ሔኖክ ከምድር በተወሰደ ጊዜ በቀጥታ የመጣበት እንደሆነ ጠየቅኩት፡፡ እርሱም ሲመልስልኝ «አይደለም፤ የኔ መኖሪያ ከተማዋ ናት ወደዚህ ስፍራ የመጣሁት ለጉብኝት ነው» አለኝ፡፡ እርሱ በዚህ ስፍራ አንደ ፍጹም መኖሪያው ይዘዋወር ነበር፡፡ ዳግመኛ በጽልመት ወደተዋጠው ምድር ተመልሶ የመምጣቱን ሃሳብ መቋቋም ባለመቻሌ በዚያ ስፍራ እንድቀር ይፈቅድልኝ ዘንድ አብሮኝ የነበረውን መልአክ ጠየቅኩት፡፡ እርሱም ሲመልስልኝ «ተመልሰሽ መሄድ ይኖርብሻል፡፡ ታማኝ ከሆነሽ ከ144ሺህዎቹ ጋር በመሆን ሁሉንም ዓለማት የመጎብኘትና የግዚአብሔርን እጆች ሥራ የመመልከት ዕድል ታገኛለሽ” አለኝ፡፡ EWAmh 23.3