ቀደምት ጽሑፎች
4—መታተም
ጥር 5/1849 ዓ.ም. በቅዱስ ሰንበት መጀመሪያ ላይ ከወንድም ቤልደን ቤተሰብ ጋር በሮኪ ሒ 1 ኮኔክቲከስ በጸሎት ተጠምደን በነበርንበት ወቅት መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ ወርዶ ነበር፡፡ በራእይ ተነጥቄ ወደ ሰማያዊው ቅድስተቅዱሳን በመወሰድ የሱስ ለእስራኤል የምልጃ አገልግሎት ሲፈጽም ተመለከትኩ፡፡ በዘርፋማው ልብሱ ግርጌ ላይ ደወልና የሮማን ፍሬ ነበር፡፡ ከዚያም እያንዳንዱ ጉዳይ ለደኅንነት ወይም ለጥፋት ተወስኖ እስኪያበቃ ድረስ የሱስ ቅድስተቅዱሳኑን ትቶ እንደማይወጣ ተመለከትኩ የሱስ ሥራውን እከሚጨርስ ድረስ የእግዚአብሔር ቁጣ አይወርድም፡፡: ከዚያ ግን ልብስ ተክኅኖውን ያወልቅና እራሱ የፍርድ ልብሱን ይለብሳል፡፡ ከዚያም የሱስ በአባቱና በሰዎች መሃል በመሆን አገልግሎት ይሰጥ ከነበረበት ስፍራ ይወጣል፡፡ ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር በዝምታ መቆየት ያበቃና የእርሱን እውነት በተቃወሙት ላይ ቁጣውን ያፈሳል፡፡ የመንግሥታት ቁጣ፣ የእግዚአብሔር ቁጣና የሞቱት የሚዳኙበት ጊዜ በየተራ የሚጡየተለያዩ መሆናቸውን ተመለከትኩ፡፡ ደግሞም ሚካኤል ለሕዝቡ ገና አልቆመም--ከዚያ በፊት ሆኖ የማያውቀው የመከራውም ጊዜ ገና አልጀመረም:: አሁን መንግሥታት በቁጣ ቢገነፍሉም ነገር ግን ሊቀ ካኅናችን ለሕዝቡ የሚቆመው የመቅደስ አልግሎቱን ሲያጠናቅቅ ነው:፡፡ ያን ጊዜ የበቀል ልብሱን ይለብሳል ሰባቱ የመጨረሻ መቅሰፍቶችም ይወርዳሉ፡፡ EWAmh 20.2
የየሱስ የመቅደሱ አገልግሎት እስኪፈጸም ድረስ አራቱ መላእክት አራቱን ነፋሳት እንደሚይዙትና ከዚያ በኋላ ግን ሰባቱ መቅሰፍቶች እንደሚወርዱ ተመለከትኩ፡፡ እነዚህ መቅሰፍቶች ኃጥአን በጻድቃን ላይ በቁጣ እንዲገነፍሉ ያደርጓቸዋል: እኛ በእነርሱ ላይ ፍርድ እንዳመጣንባቸው አድርገው በማሰብ ከምድር ገጽ ሊያጠፉን ቢችሉ መቅሰፍቶቹ እንደሚቀሩላቸው ይገምታሉ፡፡ ከዚያም ቅዱሳኑ ደኅንነት ያገኙ ዘንድ ቀንና ሌሊት እንዲያለቅሱ መንስኤ የሆናቸው---እነርሱን የመግደል አዋጅ ወጣ፡፡ ይህ የያዕቆብ የመከራ ወቅት ነበር፡፡ ከዚያም ቅዱሳኑ ሁሉ በከባድ ኃዘንና የሥቃይ መንፈስ ልቅሶአቸውን አስሙ---በእግዚአብሔርም ድምጽ ነጻ ወጡ፡፡ 144 ሺዎቹ ድል አድራጊ ሆኑ፡፡ ፊቶቻቸው በእግዚአብሔር ክብር አበራ፡፡: ከዚያም በከባድ ህመም ሲያነቡ የነበሩ ቡድኖችን እንድመለከት ተደርጌ የነበረ ሲሆን፤ እነዚህ ወገኖች በልብሶቻቸው ላይ ‹‹በሚዛን ተመዘንክ ቀለህም ተገኘህ» በሚል እጅግ ጎላ ተደርጎ ባህሪዎቻቸው ተጽፈው ነበር እነዚህ ቡድኖች እነማን እንደሆኑ ብጠይቅ መልአኩም «እነዚህ በአንድ ወቅት ሰንበትን ይጠብቁ የነበሩና ያቆሙ ናቸው” አለኝ፡፡ «በዳግም ምጽአትህ አምነናል፤ በኃይልም አስተምረናል” እያሉድምጻቸውን ከፍ አድርገው ሲጮኹ ሰማኋቸው፡፡ ደግሞም ይህን እየተናገሩ ዐይኖቻቸው በልብሶቻቸው ላይ ያርፉ---የተጻፈውንም ይመለከቱና ጮክ ብለው ያነቡ ነበር፡፡ እነዚህ ቡድኖች ጥልቅ ከሆኑት ውሖች ጠጥተው በመስከር፧ ሰንበትን በመርገጣቸውና ትሩፋኑን በመበከላቸው በሚዛን ተመዝነው እንደቀለሉ ተመልክቻለሁ:፡፡ EWAmh 21.1
ትዕይንቱን የሚያስጎበኘኝ መልአክ እንደገና ወደ ከተማዋ ይዞኝ በመሄድ አራት መላእክት ወደ ከተማው በራፍ እየበረሩ ሲሄዱ ተመለከትኩ፡፡ እነዚህ መላእክት በበሩ ላይ ለቆመው ለሌላው መልአክ ወርቅማ ካርድ እየሰጡት እያለ ሌላ አንድ መልአክ እጅግ ድንቅ ክብር ከሚስተዋልበት አቅጣጫ በፍጥነት እየበረረ በመምጣት ድምጹን ከፍ አድርጎ ለሌሎቹ መላእክት በመጮኽ በእጁ አንድ ነገር ወደ ላይና ወደታች አውለበለበላቸው፡፡ ላየሁት ነገር ማብራሪያ ይሰጠኝ ዘንድ አብሮኝ የነበረውን መልአክ ጠየቅኩት፡፡ እርሱም ከዚህ በኋላ ሌላ ልመለከት እንደማልችል በመንገር እነዚህን የያኋቸውን ነገሮች ትርጓሜ ከትንሽ ጊዜ በኋላ እንደሚነግረኝ አስታወቀኝ፡፡ EWAmh 21.2
ሰንበት ከሰዓት ላይ ከቤተክርስቲያን ከአባላቶቻችን አንድ ሰው በመታመሙ ይፈወስ ዘንድ ጸሎት እንዲደረግለት ተጠየቀ፡፡ እኛ ሁላችንም በአንድ ላይ በመሆን በሥራው እክል ገጥሞት ወደማያውቀው ሐኪም ጉዳዩን ይዘን ቀረብን:: ከዚያም የፈውስ ኃይል እየወረደና ህመምተኛው የተፈወሰ እያለ መንፈስ ወረደብኝና በራእይ ተነጥቄ ተወሰድኩ፡፡ EWAmh 22.1
በምድር ላይ የሚሠሩት ሥራ የነበራቸውን አራት መላእክት አየሁ መላእክቱ ተግባራቸውን ወደ ማገባደዱ ላይ ነበሩ፡፡ ልብሰ ተክኅኖውን ለብሶ የነበረው የሱስ በአዘኔታ 0ይን ወደ ትሩፋኑ መልከት አደረገና እጆቹን ወደላይ አነሳ ከዚያም ጥልቅ ርኅራኄ በሚሰማው ድምጽ «የእኔ ደም፣ አባት ሆይ፣ የእኔ ደም፣ የእኔ ደም፧ የኔ ደም» በማለት ጮኸ፡፡ ይህን ተከትሎ በነጭ ዙፋን ላይ ከተቀመጠው ከአግዚአብሔር አምላክ ብርቱ ብርሃን ሲመጣ አየሁ፡፡ ይህ ብርሃን ሙሉ ለሙሉ በየሱስ ላይ አብርቶ ነበር: ከዚያም ከየሱስ የተላከ አንድ መልአክ ተመለከትኩ፡፡ መልአኩ በምድር ላይ የሚሠሩት ሥራ ወደ ነበራቸው አራቱ መላእክት በፍጥነት በመገስገስ-የሆነ ነገር ወደላይና ወደ ታች እያውለበለበ በታላቅ ድምጽ «የእግዚአብሔር አገልጋዮች በግንባሮቻቸው ላይ ታትመው እስኪያበቁ ድረስ ያዘው፣ ያዘው፣ ያዘው፣ያዘው” እያለ ይገሰግስ ነበር EWAmh 22.2
የሰማሁትን ነገር ትርጓሜና አራቱ መላአክት ሊያደርጉ ያሉት ነገር ምን እንደሆነ አብሮኝ የነበረውን መልአክ ጠየቅኩት እርሱም ኃይላቱን የያዘው ግዚአብሔር መሆኑንና ምድር ላይ ለሚሆኑት ነገሮች ሁሉ ለመላእክቱ ሥልጣን እንደተሰጠ ነገረኝ: አራቱ መላእክት አራቱን ነፋሳት ለመያዝ ከእግዚአብሔር ኃይል የነበራቸው ሲሆን አሁን ግን ሊለቁት ነው:: የመላእክቱ እጆች እየላሉና ነፋሳቱ እየነፈሱ ሲሄዱ በምህረት የተሞሉት የየሱስ ዐይኖች ባልታተሙት ትሩፋን ላይ ነበሩ፡፡ ከዚያም የሱስ እጆቹን ወደ አባቱ በማንሳት ደሙን ለእነርሱ ማፍሰሱን በመግለጽ ልመናውን አቀረበ፡፡ ከዚያም ሌላ መልአክ በፍጥነት ወደ እነርሱ በመብረር የእግዚአብሔር አገልጋዮች በሕያው አምላክ ማኅተም በግንባሮቻቸው ላይ ታትመው እስኪያበቁ ድረስ ነፋሳቱን ይዘው እንዲቆዩ ይነግራቸው ዘንድ ታዘዘ፡፡: EWAmh 22.3