ቀደምት ጽሑፎች

54/73

53—ዊልያም ሚለር

እግዚአብሔር በግብርና ሥራ ይተዳደር ወደ ነበረው ዊልያም ሚለር መልአኩን ላከ:፡፡ ሚለር በወቅቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እምነት አልነበ ረውም፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔር ሕዝቦች በጽልመት በነበሩበት በዚያን ወቅት አእምሮውን በመክፈት ትንቢትን ያስተውል ዘንድ የእግዚአብሔር መላእክት ይህን የተመረጠ ሰው በተደጋጋሚ ጎብኝተውት ነበር፡፡ ተያያዥነት ያላቸው እውነቶች ለሚለር ከተሰጡት በኋላ አምላካዊውን ቃል በአግራሞት እስከተመለከተበት ጊዜ ድረስ እያንዳንዱ መልእክት ከሌላው ጋር የነበረውን ግንኘ ነት ተከትሎ መመርመር ጀመረ: ሚለር ፍጹም የሆነ ተያያዥነት ያለውን እውነት ተመለከተ፡፡ እንደ ተራ ጽሑፍ ተመልክቶት የነበረው መልእክት አሁን ግን ከእነ ውበቱና ግርማው ወለል ብሎ ታየው፡፡ ሚለር በነበረው ማስተዋል :ንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የተዘጋ ሆኖ ሲያገኘው፤ በሌላኛው ክፍል ተገልጾና ተብራርቶ መመልከት ቻለ፡፡ በዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ አንደኛው ክፍል ሌላውን እንደሚፈታ hስተዋለ፡፡ ይህን የተረዳው EWAmh 165.2

ሚልር የተቀደሰውን አምላካዊ ቃል በደስታና ከልብ በመነጨአክብሮት ተመለከተው ሚለር መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ትንቢት ተከትሎ ባደረገው ምርመራ ሰብዓዊው ፍጡር እየኖረ ያለው በምድር ታሪክ መዝጊያ ላይ ቢሆንም ነገር ግን ሰዎች ይህን አለማስተዋላቸውን ተመለከተ፡፡ ወደ አብያተክርስቲያናት ባደረገው ምልከታ ብልሹነት ሰፍኖባቸው አየ፡፡ ከየሱስ አግኝተውት የነበ ረውን ፍቅርና እንክብካቤ ለዓለም በማዋል ከላይ ከሚመጣው ክብር ፋንታ ምድራዊውን ክብርና ዝና ይሹ ነበርመዝገባቸውን በሰማይ በማኖር ፋንታ ምድራዊውን ባለጸግነት ያነፈንፉ ነበር፡፡ ሚለር ግብዝነትን፣ በጨለማ ውስጥ መመላለስንና ሞትን በየስፍራው መመልከት በመቻሉ መንፈሱ ታወከ፡፡ ኤ ልሳ በሬዎቹንና የእርሻ መሬቱን ትቶ ኤልያስን እንዲከተለው እግዚአብሔር እንደጠራው ሁሉ እርሱም እርሻውን ትቶ ይከተለው ዘንድ እግዚአብሔር ጥሪ አቀረበለት፡፡ ዊልያም ሚለር እየፈራና እየተባ አስደናቂውን የእግዚአብሔር መንግሥት ምስጢር ለሕዝቡ በመግለጥ ትንቢቶቹን እየተከተለ አድማጮቹን ወደ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት አመጣቸው፡፡ በእያንዳንዱ ጥረቱ ብርታት እያገኘ መምጣት ጀመረ፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ የመጀመሪያውን የየሱስ ምጽአት በይፋ በማስተጋባት ጎዳናውን እንደጠረገ ሁሉ ዊልያም ሚለርና ተከታዮቹም እንዲሁ የእግዚአብሔርን ልጅ ዳግም ምጽአት አስተጋቡ፡፡ EWAmh 166.1

ወደ ደቀ መዛሙርቱ ጊዜያት ተወስጄ ተወዳጁ ዮሐንስ ያከናውነው ዘንድ እግዚአብሔር የሚሻው የተለየ ሥራ እንደነበር ተመለከትኩ፡፡ ሰይጣን ይህን ሥራ ለማሰናከል ቆርጦ ተነስቶ ስለነበር አገልጋዮቹ ዮሐንስን እንዲያጠፉት ቢመራቸውም ነገር ግን አግዚብሔር መልአኩን ልኮ በሚያስደንቅ ሁኔታ ታደገው፡፡ ዮሐንስን በማዳን ለተገለጠው ታላቅ አምላካዊ ኃይል ምስክር የሆኑ ሁሉ በተመለከቱት ነገር በመደነቅ እግዚአብሔር አብሮት እንዳለና ስለ የሱስ የሰጠው ምስክርነት ትክክለኛ መሆኑን አመኑ፡፡ እርሱን ለማጥፋት ተመኝተው የነበሩ ዳግመኛ ህይወቱን ለማጥፋት ሙከራ ለማድረግ ፍርሃት አድሮባቸው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ዮሐንስ ለየሱስ ስቃይ ይቀበል ዘንድ ተፈቅዶ ነበር፡፡ ተወዳጁ ደቀ መዝሙር በጠላቶቹ የሐሰት ክስ ከቀበረበበት በኋላ ሰው ወደ ማይኖርበት አንድ ደሴት በግዞት ተወሰደ፡፡ ጌታ መልአኩን ልኮ እስከ መጨረሻ እውን የሚሆኑ ምድራዊ ስተቶችንና የቤተክርስቲያንን ሁናቴ ገለጸለት፡፡ በዚህ በተሰጠው ራእይ በቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሰውን ውድቀት እንዲሁም ቤተክርስቲያን እግዚአብሔርን የሚያስደስት አቋም ብትይዝ በመጨረሻ አሸናፊ እንደምትሆን ገልጾለታል፡፡ EWAmh 166.2

ከሰማይ የተላከው መልአክ ወደ ዮሐንስ የመጣው በታላቅ ክብር ሲሆን፤ የፊቱ ገጽታ አስደናቂውን አምላካዊ ክብር ያንጸባርቅ ነበር፡፡ መልአኩ በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ታሪክ እውን የሚሆኑ ጥልቅና አስደናቂ ትዕ ይንቶችን እንዲሁም ክርስቲያን ተከታዮች የሚያልፉባቸውን አስፈሪ ውዝግቦችን ገለጸለት፡፡ ዮሐንስ ክርስቲያኖች በhባድ ፈተና ውስጥ አልፈውና ልብሶቻቸውን አንጽተው በመጨረሻ አሸናፊዎች ሆነው በእግዚአብሔር መንግሥት ወራሾች መሆናቸውን ተመልክቶአል፡፡ መልአኩ የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን በመጨረሻ አሸናፊ እንደምትሆን ለዮሐንስ ሲገልጽለት ገጽታው በደስታ ብዛት ፈክቶ ነበር፡፡ ሐዋርያው ቤተክርስቲያን በስተመጨረሻ ነጻ መውጣቷን ሲመለከት በዚህ በክብር የተሞላ ትዕይንት በመደሰት ጥልቅ በመሆነ አክብሮትና ፍርሃት ለመልአኩ ለመስገድ በእግሩ ስር ወደቀ፡፡ ሰማያዊው መልአክ ግን በፍጥነት ዮሐንስን በማንሳት ለስለስ ብሎ እንዲህ ሲል ገሰጸው «ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ የየሱስ ምስክር የትንቢት መንፈስ ነውና፡፡” ከዚያም መልአኩ ሰማያዊውን ከተማ ከእነሙሉ ክብሩና ውበቱ አሳየው፡፡ ዮሐንስ በተመለከተው ነገር አብልጦ በመደመሙ መልአኩ እንደገጸው በመዘንጋት ዳግመኛ ሊሰግድለት በእሩ ስር ወደቀ፡፡ መልአኩም እንዲህ ሲል ዳግመኛ ገሰጸው «ተው! ይህን አታድርግ! እኔ hአንተና ከወንድሞችህ ከነቢያት እንዲሁም የዚህን መጽሐፍ ቃል ከሚጠብቁት ሁሉ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ፡፡” EWAmh 167.1

ሰባኪዎችም ሆኑ ሕዝቡ የራእይን መጽሐፍ ምስጢራዊና ከሌሎቹ ቅዱሳት መጻሕፍተይልቅ አስፈላጊነቱ እምብዛም ያልሆነ አድርገው ተመልክተውታል፡፡ ነገር ግን ይህ መጽሐፍ በመጨረሻዎቹ ቀናት የሚኖሩትን የእግዚአብሔር ታማኞች የሚመራ፣ የያዙትን እውነተኛ አቋም የሚያ ረጋግጥላቸውና ተግባራቸውን የሚያመላክታቸው-እንደ ልዩ ጥቅም የተሰጠ መገለጥ መሆኑን ተመልክቼ ነበር፡፡ የዊልያም ሚለር አእምሮ ወደ ትንቢቶቹ እንዲያነጣጥር በማድረግ እግዚአብሔር በራእይ መጽሐፍ ዙሪያ ታላቅ ብርሃን ሰጠው፡፡ EWAmh 167.2

የዳንኤል ራእዮች, መስተዋል ከቻሉ ሕዝቡ የዮሐንስን ራእይ በተሻለ መ ረዳት ይችላል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ትክክለኛው ጊዜ ሲደርስ እርሱ የመረጠውን አገልጋዩን በመንካት ግልጽ ሆኖ በተቀመጠና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ትንቢቶቹን በመክፈ የዳንኤልን፣ የዮሐንስንና የሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን ውህደት በመግለጽ ሕዝቡ ለሰው ልጅ ዳግም ምጽአት የሚዘጋጅበትን ቅዱስና አስፈሪ ማስጠንቀቂያዎችን አሳየው፡፡ እርሱን በሰሙት ሰዎች አእምሮ ውስጥ ጥልቅና ጽኑ መነካት በመከሰቱ አገልጋዮች፣ ሕዝቡ፣ ኃጢአተኞች እንዲሁም በክህደት ውስጥ የነበሩ ፊታቸውን ወደ ጌታ በመመለስ ለፍርዱ ቀን ዝግጅት ማድረግ ፈለጉ፡፡ EWAmh 167.3

ዊልያም ሚለር የተሰጠውን ተዕእኮ ከግብ ያደርስ ዘንድ የአግዚአብሔር መላእክት ከጎኑ ነበሩ፡፡ ጽኑና ፍርሃት የማያውቀው፣ ላመነበት ቀናኢ የነበ ረው ሚለር በክፋትና ቅዝቃዜ ተሞልቶ ለነበረው ምድር የተሰጠውን መልእክት በይፋ አስተጋባ፡፡ ምንም እንኳ ሚለር በዓለምና ክርስቲያን ነን በሚሉ ሰዎች ተቃውሞ ቢደርስበት እንዲሁም ሰይጣንና መላእክቱ ሥቃይ ቢያመጡበትም እርሱ ግን እንዲናገር ግብዣ በተደረገለት ቦታ ሁሉ ዘላለማዊውን ወንጌል ለሕዝቡ መስበኩን አላቋረጠም ነበር «እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርም ስጡት ምክንያቱም የፍርዱ ሰዓት ደርሶአል»፡፡ EWAmh 168.1