ቀደምት ጽሑፎች

53/73

52—የቤተ ክርስቲያንና የዓለም ውህደት መፍጠር

ከዚህ በኋላ ሰይጣን ስላገኘው ውጤት ከመላእክቱ ጋር ይመክር እንደነበር ተመለከትኩ፡፡ በእርግጥ ሰይጣንና መላእክቱ አንዳንዶች ሞትን ፈርተው እውነትን ከመቀበል እንዲያፈነግጡ ቢያደርጓቸውም ነገር ግን ብዙ ዎች ፈሪና ድንጉጥ ሆነው ሳለ እውነትን በመቀበላቸው ብቻ የነበራቸው ፍርሃትና ድንጋጤ ከላያቸው መገፈፍ ችሎ ነበር፡፡ እነዚህ ወገኖች በወንድሞቻቸው ላይ ለደረሰው ሞት እማኝ በመሆን የራሳቸውን ጥንካሬና ትዕግሥት ሲመለከቱ፧ እንዲህ ያለውን ሥቃይ ያልፉ ዘንድ እግዚአብሔርና መላእክቱ እንደረዷቸው በማስተዋል ደፋርና ፍርሃት 0ልባ ሆኑ፡፡ ከእምነታቸውና ከህይወታቸው አንዱን እንዲመርጡ ሲጠየቁ፤ እምነታቸውን በትዕግሥትና በጽናት መጠበቃቸው ገዳዮቻቸውን ሳይቀር በፍርሃት እንዲርዱ ኣደረገ፡፡ ሰይጣንና መላእክቱ ነፍሳትን ለማጥፋት የሚያስችላቸው የላቀ ስኬታማ መንገድ እንደነበር ተመለከቱ፡፡ ምንም እንኳ ክርስቲያኖች ሥቃይ እንዲደርስባቸው ቢደረጉም ነገር ግን የነበራቸው ጽናትና ብሩህ ተስፋ ደካማው እንዲበረታ በማድረግ በዚያን ዘመን ሰዎችን ለማሰቃያ ጥቅም ላይ ይውል የነበረውን አሰቃቂ አሠራር በድፍረት እንዲጋፈጡ አስቻላቸው፡፡ በእነዚህ ሰዎች ዘንድ ይታይ የነበረው ታማኝነትና በላያቸው አርፎ የነበረው አምላካዊ ክብር ክርስቶስ በገዳዮቹ ፊት ይነበብበት ከነበረው ጻድቅ ገጽታ ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ብዙዎች እውነትን መያዛቸውን አምነው እንዲቀበሉ አድርጎ ነበር፡፡ EWAmh 163.1

ከዚህ በኋላ ሰይጣን ለስለስ ያለ አካሄድ መከተል እንዳለበት ወሰነ፡፡ ሰይጣን መጽሐፍ ቅዱሳዊውን አስተምህሮ ከባህል ጋር ቀላቅሎ በማቅረብ ሚሊዮኖችን ሥር በሰደ የተጣመመ ትምህርት ማሰናከል ቻለ፡፡ ሰይጣን ይከተል ከነበረው የጥላቻ አካሄድ በመታቀብ ቤተክርስቲያን ልዩ ልዩ ባህል፣ ወግና ልማዶችን ወደምትከተልበት ጎዳና መራት፡፡ ሰይጣን ቤተክርስቲያን ዓለማዊን ክብርና ዝና የምትቀዳጅበትን ሠራር ተከትላ እንድትጓዝ በማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ የነበራትን ድጋፍ እንድታጣ አደረጋት፡፡ ቤተክርስቲያን ቀጥተኛውን እውነት ከመናገር በመታቀብ ዓለማዊውን ደስታ ከሚወዱና ከዓለም ወዳጆች ጋር ግንባር በመፍጠሯ ቀስ በቀስ የነበራትን ኃይል እያጣች ሄደች:: EWAmh 163.2

በዚህን ወቅት ቤተክርስቲያን ቀደም ባሉት ጊዚያቶች ስደት ሲርስባት የነበረችው ዓይነት ከዓለም የተለየች አልነበረችም:፡፡ ያ አንጸባራቂ ወርቅ እንዴት ደበዘዘ! እንዴትስ ተቀየረ! ቤተክርስቲያን ምን ጊዜም የተለየና ቅዱስ የሆነውን ባህሪ ጠብቃ ከተጓዘች ለደቀ መዛሙርቱ ተሰጥቶ የነበረው መንፈስ ቅዱስ አብሯት እንደሚሆን ተመልክቻለሁ፡፡ ይህ ሲሆን በሽተኞች ይፈወሳሉ! አጋንንት ተገስጸው ይወጣሉ እንዲሁም ቤተክርስቲያን ኃያልና ጠላቶቿ የሚርበደበዱባት ትሆናለች:: EWAmh 164.1

የክርስቶስን ስም ይጠሩ የነበሩ ነገር ግን አግዚአብሔር የማያውቃቸውን አያሌዎችን ተመልክቼ ነበር፡፡ እርሱ በእነዚህ ሰዎች ደስታ አልነበረውም፡፡ እነዚህ ሕዝቦች እራሳቸውን ክርስቲያን አድርገው በመቁጠር የኃይማኖት መልክ ብቻ እንዲኖራቸው ማድረጉ የሰይጣን ዕቅድ ነበር በመሆኑም በየሱስ፣ በየሱስ ስቅለት እንዲሁም በትንሳኤው አንዲያምኑ የማድረግ ጉጉት ነበረው፡፡ ሰይጣንና መላእክቱም ቢሆኑ እነዚህን እውነታዎች ሙሉ ለሙሉ ያምናሉይንቀጠቀጣሉም፡፡ ነገር ግን ይህ እምነት ለመልካም ሥራ አነሳሽ መሆን እስካልቻለና ይህን እውነት እናምናለን የሚሉ ሁሉ ክርስቶስ ወደ ኖ ረው እራስን የመካድ ህይወት እንዲያመሩ እስካላደረገ ድረስ ሰይጣን ስጋት የለበትም፡፡ የአነዚህ ሰዎች ትኩረት ክርስቲያን ተብለው መጠራታቸው ላይ ብቻ በመሆኑ ልባቸው ሥጋዊ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሰይጣን ለፈለገው አገልግሎት በተሻለ እንዲጠቀምባው ያስችለዋል፡፡: እነዚህ ቅድስና የጎደለው ተፈጥሮ ያላቸውና ለአምላካዊው ፈቃድ የማይገዛ ክፉ ምኞት ባለቤቶች ግድፈቶቻቸውን በሙሉ በስመ ክርስትና ውስጥ ደብቀው ይኖራሉ፡፡ ይህ የእነርሱ ፍጽና የጎደለው ህይወት አማኝ የልሆነው ሰው በክርስቶስ ላይ ትችት እንዲሰነዝር በማድረግ ንጹህና ያልረከሰ እምነት ያላቸው ላይ ውርደትን ያመጣል፡፡ EWAmh 164.2

አገልጋዮች በሥጋ የሚመላለሱ ምሁራንን ስሜት ለመጠበቅ ሲሉ በሚያደርጉት መለሳለስ መልእክቶቻቸው ጥንካሬ አልነበራቸውም፡፡ አገልጋዮች ምሑራኑ ከቤተክርስቲያን እንዳይኮበልሉ በመስጋት የሱስንና መጽሐፍ ቅዱሳዊውን የሰላ እውነት ለመስበክ አልደፈሩም፡፡ ኃይማኖተኛ ናቸው የተባሉ ሰዎች በብዙዎች ዘንድ ይበልጥ የተከበሩ ተደርገው በመታየታቸው የየሱስ ክርስቶስ ኃይማኖት በዓለም ዐይን ታዋቂና የተከበረ ገጽታ እንዲይገ ተደረገ፡፡ የእርሱና የዓለም :ስተምህር እርስ በርስ ሰላም መፍጠር እንደማይችሉ በመሆናቸው እነዚህ ትምህርቶች ከክርስቶስ አስተምህሮዎች ጋር ሰፊ ልዩነት አላቸው፡፡ እርሱን ለመከተል የሚመርጡ ሁሉ ዓለምን ማውገዝ ነበረባቸው፡፡ በሰይጣንና መላእክቱ አማካኝነት የተጠነሰሱ አስደሳች ተረቶችን የኃይማኖት ሊቃውንትና ምሑራን ነን ባዮች ተቀብለው የኃይማኖታዊው አስተምህሮ አካል አደረጓቸው:: በዚህም አስተምህሮዎቹን ለመቀበል ዝግጁ የነበሩ ልቦች ይሁንታቸውን በማሳየት ግብዞችና በግልጽ ኃጢአት የሚያደርጉ ቤተክርስቲያንን እንዲቀላቀሉ ሆኑ፡፡ ቤተክርስቲያን እውነትን በንጽህና ብትሰብክ ኖሮ ይህ ዓይነቱ አስተምህሮ ጊዜ ሳይወስድ ባበቃለት ነበር፡፡ ሆኖም ክርስቶስን እንከተላለን በሚሉና በዓለም መሃል ልዩነት አልነበረም፡፡ የቤተክርስቲያን አባላትን ገጽታ የደበቀው የሐሰትሰሐሐሐሐሰሳ ጭምብል ቢነሳ ኖሮ ታማኝ አለመሆናቸው፣ ብልግናቸውና ብልሹነታቸው ተገለጾ ይታይ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ እነዚህን ሥራቸው የእርሱ መሆናቸውን የሚመሰክር ክርስቲያን ነን ባይ የአባታቸው የዲያብሎስን ልጆችን---የመጨረሻ ዐይናፋር የተባለው የእግዚአብሔር ልጅ በትክክለኛው ስማቸው ለመጥራት ባላመነታ ነበር፡፡ EWAmh 164.3

የሱስና መላው የሰማይ ሰራዊት ይህን ትዕይንት በመጸየፍ ቢመለከቱም፤ እግዚአብሔር ግን ቅዱስና አስፈላጊ ለሆነችው ቤተክርስቲያን መልእክት ነበ ረው፡፡ ቢቀበሉት በቤተክርስቲያን አጠቃላይ ተሐድሶ በማምጣት የግብዙንና ኃጢአተኛውን በደል የሚደመስስ ህያው የመነቃቃት ምስክር በመስጠት ቤተክርስቲያንን ዳግመኛ አጽንቶ ያቆማት ነበር፡፡ EWAmh 165.1