ቀደምት ጽሑፎች
54—የመጀመሪያው መልአክ መልእክት
እግዚአብሔር በ1843 ዓ.ም. እወጃ እንደሚያደርግ ተመልክቻለሁ፡፡ ሕዝቡ እውነትን ለመከተል ወይም በተቃራኒው ለመቆም ውሳኔውን እንዲያደርግ በማነሳሳት ወደ ሚፈተኍበት ነጥብ ማምጣት የእርሱ ዕቅድ ነበር አገልጋዮች በትንቢታዊ ቀናቶቹ ዙሪያ የተደረሰው አቋም ትክክል መሆኑን አምነው ተቀብለው የነበረ ሲሆን ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ክብራቸውን፣ ደሞዛቸውንና ቤተክርስቲያናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ትተው መልእክቱን ለማሰራጨት ከስፍራ ወደ ስፍራ መጓዝ ጀመሩ፡፡ ሰማያዊው መልእክት በእነዚህ ጥቂት አዳዲስ የክርስቶስ አገልጋዮች ልብ ውስጥ ቦታ ማግኘት ሲጀምር ሥራው ሰባኪ ባልሆኑ በብዙዎች ትከሻ ላይ አረፈ:፡፡ አንዳንዶች መልእክቱን ለማስተዋወቅ እርሻዎቻቸውን ሲተዉ ሌሌች ደግሞ ከንግድ ሥራዎቻቸውና ድርጅቶቻቸው ተጠርተው ነበር፡፡ በተጨማሪ አንዳንድ ባለሙያዎች ሙያቸውን ተተው ዝነኛ ባልሆነው የመጀመሪያውን መልአክ መልእክት የማሰራጨቱ ሥራ ላይ ተጠምደው ነበር:: EWAmh 168.2
አገልጋዮች የነበሯቸውን የወገንተኝነት አመለካከቶችና ,ሜቶች በማስወገድ በየሱስ ምጽአት ዙሪያ ቃሉን ለማወጅ ህብረት ፈጠሩ፡፡ መልእክቱ በተሰጠበት በማንኛውም ስፍራ የዎችን ልብ ይነካ ነበር፡፡ ኃጢአተኞች ንስሐ ገቡ፣ አነቡ፣ ለኃጢአታቸው ይቅርታ ያገኙም ዘንድ ጸለዩ፡፡ ታማኝነት የጎደለው ህይወት ይመሩ የነበሩ ከዚህ በኋላ ባለው ህይወታቸው ለመካስ ጽኑ ጉጉት አሳዩ፡፡ ወላጆች የልጆቻቸው ጉዳይ አሳሰባቸው፡፡ መልእክቱን የተቀበሉ የመልእክቱ ብርቱነትና ክብደት ስለተሰማቸው ልባቸው ወዳልተነካው ጓደኞቻቸውና ዘመዶቻቸው በማምራት ለሰው ልጅ ዳግም ምጽአት ይዘጋጁ ዘንድ አግባቧቸው---አስጠነቀቋቸው:: እንዲህ ያለው ነፍስን የሚያጠራ ሥራ ሰዎች ለዓለማዊው ነገር የነበራቸውን ፍቅር አስወግደው ከዚያ ቀደም ተለማምደውት የማያውቁትን ቅድስናን እንዲለማመዱ መራቸው፡፡ EWAmh 169.1
በዊልያም ሚለር የቀረቡትን መልእክቶች በሺህዎች የሚቆጠሩ ተቀበሏቸው፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች መልእክቱን ለማዳረስ በኤልያስ መንፈስና ኃይል እያደጉ ሄዱ ብርቱ የሆነውን ይህን መልእክት የሰበኩ የየሱስን ጎዳና እንደጠረገው እንደ ዮሐንስ---ሰዎች መልካም ፍሬ ያፈሩ ዘንድ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ ያለበለዚያ ግን ምሳር የዛፎችን ስር ለመቁረጥ መዘጋጀቱን ለመናገር ተገፋፉ፡፡ ምስክርነታቸው ቤተክርስቲያን በኃይል ተነሳስታ ወደ ሥራ እንድትገባ ተጽእኖ የሚያሳድርና እውነተኛውን ባህሪያችውን በትክክል እንዲያሳይ ሆኖ የተቀመረ ነበር፡፡ ሰዎች ከሚመጣው ቁጣ እንዲያመልጡ የተሰጠው ይህ ብርቱ ማስጠንቀቂያ በተሰማ ጊዜ ከየአብያተክርስቲያናቱ ጋር ሕብረት የነበራቸው ብዙዎች ይህን ፈዋሽ መልእክት ተቀበሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ከእግዚአብሔር ቤት መሰናከላቸውን በመመልከት አምርረው በማልቀስና በእግዚአብሔር ፊት ታማኝ አድርገው በላያቸው ባረፈ ጊዜ «እግዚአብሔርን የፍርዱ ሰዓት ደርሶአል” እያሉ አብረው ንስሐ በመግባት እራሳቸውን አቆሙ፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ፍሩ ክብርም ስጡት ምክንያቱም ያስተጋቡ ጀመር፡፡ EWAmh 169.2
የክርስቶስን መምጫ ቀን ቁርጥ አድርጎ የሚያስቀምጠው መልእክት ከምስባክ (ፑልፒት) ላይ አገልጋዩ አንስቶ ቁልቁል ደፋሩ ኃጢአተኛ ድረስ በየአቅጣጫው ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የመምጫውን «ቀኑን ወይም ሰዓቱን» አታውቁም የተሰኘው ጥቅስ ከግብዙ አገልጋይ እስከ ከደፋሩ ፌዘኛ ሲነገር ይደመጥ ነበር፡፡ ከእነዚህ ሰዎች ውስጥ አንዳቸውም ቢሆኑ ትንቢቶቹንና ምልክቶቹን ተከትለው ምጽአቱ በደጅ መሆኑን በማስተዋል የክርስቶስን መምጫ ቀን ቆርጠው ካስቀመጡት ወገኖች ሊማሩም ሆነ ሊታረሙ ፈቃደኞች የሆኑ አልነበሩም፡፡ ክርስቶስን እንወደዋለን ይሉ የነበሩ አያሌ የመንጋ ጠባቂዎች ስለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት መልእክትበመሰጠቱ ተቃውሞ እንደሌላቸው ነገር ግን የእነርሱ ተቃውሞ በዚህ ቀን ይመለሳል ብሎ ቀኑን ወስኖ ማስቀመጡ ላይ መሆኑን ሲናገሩ ይደመጡ ነበር፡፡ ሁሉን የሚያዩትና የሚመረምሩት አምላካዊው ዐይኖች ልቦቻቸውን ያነቡ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች የሱስን ወደ ልቦቻቸው አቅርበው አልወደዱትም፡፡ በእርሱ ተለይቶ በተቀመጠው ትሁት ጎዳና ላይ እየተራመዱ ስላልነበር ክርስቲያናዊ ያልሆነው ህይወታቸው ፈተናውን ተቋቁሞ መቆም እንደማይችል ያውቁ ነበር፡፡ እነዚህ የሐሰት እረኞች የእግዚአብሔር ሥራ በሚሠራበት ጎዳና ላይ ቆመው ነበር፡፡ የሰዎችን ልብ ሊያሳምን በሚችል ኃይል የተነገረው እውነት ሕዝቡን ማነሳሳት በመቻሉ «እድን ዘንድ ምን ላድርግ?” በማለት እንደ እስር ቤት ጠባቂው መጠየቅ ጀመሩ፡፡ ነገር ግን እረኞቹ በእውነትና በሕዝቡ መሃል በመግባት ሕዝቡ ከእውነት እንዲያፈነግጥ የሚያደርግ ለስላሳ መልእክት መስጠት ጀመሩ፡፡ በዚህም ከሰይጣንና መላእክቱ ጋር አንድነት በመፍጠር ሰላም በሌለበት ሁናቴ «ሰላም ነው፣ ሰላም ነው» እያሉ ጮኹ፡፡ ነገር ግን የገዛ ምቾቶቻቸውን ይወዱ የነበሩና ከእግዚአብሔር ጋር በነበራቸው ርቀት ደስተኞች የነበሩ ከሥጋዊው ማንነታቸው መንቃት አይችሉም. ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት በሁሉም ላይ ምልክት በማድረጋቸው ያልተቀደሱት እረኞች ልብስ በነፍሳት ደም ተበክሎ እንደ ነበር ተመልክቻለሁ፡፡ EWAmh 169.3
ይህን የሚያድን መልእክት ለራሳቸው የማይቀበሉ አገልጋዮች ሊቀበሉ ይችሉ የነበሩትን ያሰናክሉ ነበር፡፡ በመሆኑም የነፍሳቱ ደም በላያቸው ነው፡፡ ሰባኪዎችና ሕዝቡ ይህን ከሰማይ የመጣ መልእክት፣ ዊልያም ሚለርንና በሥራው ከእርሱ ጋር አንድ የሆኑትን ለመቃወም ግንባር ፈጠሩ፡፡ የሚለርን ተጽእኖ ለመጉዳት በማሰብ የሐሰት ወሬዎች እንዲሶራጩ ተደረገ፡፡ ሚለር ስለት ያለውን እውነት በማቅረብ የአድማጮቹን ልብ በመንካት አምላካዊው ድጋፍና ምሪት እንዳለው በይፋ ከተናገረ በኋላ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ ገጠመው፡፡ የነበረበትን የስብሰባ ስፍራ ለቅቆ እንደወጣ ህይወቱን ለመቅጠፍ አድፍጠው ቢጠባበቁትም ነገር ግን የእርሱ ሥራ ገና ባለመጠናቀቁ የእግዚአብሔር መላእክት ይጠብቁት ዘንድ ተላኩ:: በቁጣ ከነደደውም ሐዝብ ታደጉት፡፡ EWAmh 170.1
ለአምላካዊው ነገር እራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ መልእክቱን በደስታ ተቀበሉት፡፡ እነዚህ ሰዎች መልእክቱ ከእግዚአብሔር መምጣቱንና በትክክለኛ ው ጊዜ መሰጠቱን አውቀው ነበር፡፡ የዚህን ሰማያዊ መልእክት ውጤት በጥልቅ ፍላጎት ይመለከቱ የነበሩ መላእክት አብያተክርስቲያናቱ ላለመቀበል ተቃውሞአቸውን ባሳዩ ጊዜ በሐዘኔታ ከየሱስ ጋር መከሩ፡፡ የሱስ ፊቱን ከቤተክርስቲያናቱ በማዞር መላእክቱ ምስክርነቱን ያልተቃወሙትን የከበሩ ነፍሳት በታማኝነት ይመለከቷቸው ዘንድ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ወቅት የመጀመሪያ መስăከ መስăከት ሌላ ብርሃን ሊያንጸባርቅላቸው በሂት ላይ ነበር፡፡ EWAmh 170.2
ክርስቲያን ነን የሚሉ ሁሉ የአዳኛቸውን መገለጥ ለማየት እስከወደዱና በዚህ ምድር ላይ አንዳችም ከእርሱ ጋር ሊወዳደር የሚችል እንደሌለ ከተሰማቸው የዳግም ምጽቱ ፍንጭ ከመጠን ያለፈ ደስታ በፈጠረላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ስለ ጌታ ዳግም ምጽአት በሰሙ ጊዜ ያሳዩት ጥላቻ እርሱን አለመውደዳቸውን የሚገልጥ ነበር፡፡ EWAmh 171.1
የእግዚአብሔር ሕዝቦች በታላቅ ተስፋ የጌታቸውን ምጽአት ይጠባበቁ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ እግዚአብሔር ግን ሊፈትናቸው በማሰብ ይህን አደ ረገ፡፡ የጌታን ምጽአት ይጠባበቁ የነበሩ ትንቢታዊ ጊዜያቶቹን ሲያሰሉ የሠሩትን ስህተት እግዚአብሔር በእጁ ሸፍኖት ስለነበር ስህተቱን አልደ ረሱበትም፡፡ በተጨማሪ ይህን ተወስኖ የተቀመጠ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት የሚቃወሙ የሥነ መለኮት ምሑራንም እንዲሁ ስህተቱን መመልከት ተስኗቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ያ ጌታ ይገለጥበታል የተባለው ዕለት እንደማንኛ ውም ቀን ሲያልፍ አዳኛቸውን በታላቅ ተስፋ ይጠባበቁ የነበሩ ሁሉ ከፍተኛ ኃዘንና ተስፋ መቁረጥ ሲደርስባቸው ነገር ግን መልእክቱን በፍርሃት በመያዝ የየሱስን መገለጥ ያልወደዱ በዳግምምጽአቱ እውን አለመሆን ደስ ተሰኙ፡፡ የእነርሱ እምነት በልባቸው ላይ አንዳችም ተጽእኖ ያላሳደረና ህይወታቸውን ያላጠራ ነበር፡፡ ተስፋ የተደረገው ዕለት ያለ ክርስቶስ ዳግም ምጽአት ማለፉ የእነዚህን ልቦች ማንነት ለማሳየት በሚገባ የተቀመረ ነበር፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች የጌታቸውን መገለጥ በወደዱት፣ ባዘኑትና ተስፋ በቆረጡት ላይ ለማፌዝና ለመሳለቅ ቀዳሚዎቹ ነበሩ፡፡ በፈተና ሰዓት ወደ ኀ ላ የሚያፈገፍጉትን ለይቶ ለማስቀመጥ አምላካዊው ጥበብ በሕዝቡ ላይ ፈተና እንደሚያመጣ ተመልክቻለሁ፡፡ EWAmh 171.2
እርሱን እንደ ነፍሳቸው በማፍቀር በሚፍለቀለቅ ደስታ ሊያዩት የናፈቁትን ሁሉ የሱስና መላው የሰማይ ሰራዊት በታላቅ ርኅራኄና ፍቅር ይመለከቷቸው ነበር፡፡ ለፈተናው ጊዜ አጽንተው ያቆሟቸው ዘንድ መላእክት በላያቸው ይስፉ ነበር፡፡ ከሰማይ የተላከላቸውን ብርሃን ለመቀበል ቸል ብለው በነበሩ ላይ እግዚአብሔር በመቆጣቱ በጨለማ ውስጥ ተተዉ፡፡ ነገር ግን ጌታቸው ለምን እንዳልመጣ ሊገባቸው ያልቻለ ታማኝና ተስፋ የቆረጡ ሕዝቦች በጽልመት ውስጥ ባለመተዋቸው ዳግመኛ ትንቢታዊውን ስሌት ለማጥናት ወደ መጽሐፍ ቅዱሶቻቸው አመሩ፡፡ በዚህን ወቅት የጌታ እጅ ከቁጥሮቹ ላይ ተነስቶ ስለነበር ስህተቱ መስተዋል ቻለ፡፡ ትንቢታዊ ጊዜያቶቹ 1844 ላይ መድረሳቸውና የትንቢታዊ ጊዜያቶቹ ማብቂያ 1843 ላይ መሆኑን ያመላከቱት ተመሳሳይ መረጃዎች 1844 ላይ ፍጻሜ እንደሚያገኙ አረጋግጠውላቸው ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር ቃል ላይ ያንጸባረቀው ብርሃን ይዘውት በነበረው አቋም ላይ በማብራቱ መዘግየቱን ደረሱበት---«የሚገይ ቢመስልም (ራእዩ) ጠብቀው»፡፡ ስሌት የተሰላው እውነተኛዎቹን ተጠባባቂ ዎች ለማሳየት እንደመሆኑ ለክርስቶስ ዳግም ምጽአት ከነበራቸው ፍቅር አኳያ የራእዩን መዘግየት ማስተዋል ተሳናቸው: አብዛኞቹ ላይ ደርሶ ከነበ ረው የከፋ ተስፋ መቁረጥ አኳያ 1843 ላይ ተስተውሎ የነበረው ዓይነት የእምነት ጣራ ላይ እንደማይደርሱ ተመልክቼ ነበር፡፡ EWAmh 171.3
መልእክቱን የማይቀበሉ ወደፊት መልእክቱን የሚሆነውን አስቀድመው እንደሚያውቁ በማሰብ የስህተት ትንቢት ያሉትን መልእክት ባለመቀበል በደ ረሱት ውሳኔ ደስ በመሰኘታቸው ሰይጣንና መላእክቱ በእነርሱ ላይ ድል አገኘ :: እነዚህ ከሰማያዊው መልእክት ውጪ እየኖሩ የነበሩ ሰዎች እግዚአብሔር እያቀረበላቸው የነበረውን መልእክት በመቃወም ከሰይጣንና መላእክቱ ጋር ግንባር ፈጥረው የእግዚአብሔርን ሕዝቦች ግራ እያጋቡ እንደነበር በውል አልተገነዘቡም EWAmh 172.1
የዚህ መልእክት አማኞች በቤተክርስቲያን ጭቆና ደርሶባቸው ነበር፡፡ መልእክቱን የማይቀበሉ የልባቸውን ፈቃድ እንዳይፈጽሙ ፍርሃት ቢገታቸውም ነገር ግን የጊዜው ማለፍ እውነተኛውን ስሜታቸውን ገልጾት ነበር: አማኞቹ ጌታቸውን በ1844 ላይ የተጠባበቁበትን ምክንያት በማቅረብ ስህተቶቻቸውን ግልጽ አድርገው አስቀመጡ፡፡ ይህን ተከትሎ ተቃዋሚዎቻ ቸው በቀረበላቸው ጠንካራ ማሳመኛ ነጥቦች ላይ አንዳችም ክርክር ማንሳት ቢሳናቸውም ነገር ግን በአማኞቹ ይቀርቡ የነበሩ ማናቸውም ዓይነት መረጃ ዎችም. ሆነ ምስክርነቶች በቤተክርስቲያን እንዳይደመጡ ውሳኔ ላይ በመድ ረሳቸው ሌሎች እነዚህን ተጨባጭ መንስኤዎች መስማት አልቻሉም ነበር፡፡ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ብርሃን ለሌሎች ለመግለጽ የደፈሩ ከየቤተክርስቲያናቱ ቢታገዱም ነገር ግን የሱስ አብሯቸው ስለነበር በፊቱ ብርሃን ደስተኞች ነበሩ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች የሁለተኛውን መልአክ መልእክት ለመቀበል ተዘጋጅተው ነበር፡፡: EWAmh 172.2