ቀደምት ጽሑፎች

4/73

3—ተhታዮቹ ራዕዮች

በ1847 ዓ.ም. ላይ ወንድሞች በቶፕሻን ሜይን በሰንበት ተሰብስበው ሳለ ጌታ ተከታዩን ራእይ ሰጠኝ፡፡ EWAmh 17.1

በዚያን ወቅት ለየት ያለ የጸሎት መንፈስ ተሰምቶን ነበር፡፡ እየጸለይን በነበርንበት ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በላያችን ላይ ወረደ:፡፡ በእጅጉ ደስ ተሰኝተን ነበር፡፡ ወዲያውኑ ከምድራዊው ነገሮች ጋር ተለያይቼ በእግዚአብሔር ክብር ራእይ ተነጥቄ ተወሰድኩ:: መልአኩ ወደ እኔ እየበረረ ሲመጣ ተመለከትኩት፡፡ በፍጥነት ከምድር ላይ ተሸክሞ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደኝ፡፡ በዚያች ከተማ የገባሁባትን ቤተመቅደስ ተመለከትኩ፡፡ ወደ መጀመሪያው መጋረጃ ከመምጣቴ በፊት በአንድ በር ውስጥ አልፌ ነበር፡፡ ከዚያም መጋ ረጃው ተገለጠልኝና ወደ ቅዱሱ ክፍል ገባሁ፡፡ በዚህ ቦታ የዕጣን መሰዊያ፣ ሰባት መቅረዞች ያሉት መብራት እንዲሁም ሐብስቱ የተቀመጠበትን ጠረጴዛ ተመለከትኩ፡፡ የቅዱሱን ክብር ከተመለከትኩ በኋላ የሱስ ሁለተኛውን መጋረጃ በመግለጡ ወደ ቅድስተቅዱሳን አለፍኩ፡፡ EWAmh 17.2

በቅድስተቅዱሳኑ ክፍል ታቦት የተመለከትኩ ሲሆን ላዩና ጎኖቹ ንጹህ ወርቅ ነበሩ፡፡ በታቦቱ ዳርና ዳር ላይ ክንፎቻቸውን የዘረጉ ተወዳጅ ኪሩቤ ሎች ነበሩ፡፡ ፊታቸው ትይዩ ሲሆን ሁለቱም ወደ ታች ይመለከቱ ነበር በመላእክቱ መሃል ወርቃማ ጥና ነበር፡፡ መላእክቶቹ ከቆሙበት ከታቦቱ መሃል እግዚአብሔር ማደሪያ ዙፋን የሚመስል ከመጠን በላይ ብሩህና አንጸባራቂ ክብር ነበር: የሱስ ታቦቱ ጋር ቆሞ የነበረ ሲሆን የቅዱሳን ጸሎት ወደ እርሱ በመጣ ጊዜ በጥናው ላይ ያለው ዕጣን ይጨሳል፡፡ እርሰም ከዕጣኑ ጭስ ጋር ጸሎታቸውን ወደ አባቱ ይቀርባል፡፡ በታቦቱ ውስጥ ከወርቅ የተሠራ የመና ማሰሮ፣ያቆጠቆጠችው የአሮን በትር እንዲሁም እንደ መጽሐፍ ተዘግቶ የተቀመጠ የድንጋይ ጽላት ነበር፡፡ የሱስ ገለጣቸውና በእግዚአብሔር ጣት የተጻፉትን አሥርቱን ትእዛዛት ተመለከትኩ፡፡ በአንደኛው ገበታ አራቱ ትእዛዞች በሌላኛው ደግሞ ስድስቱ ትእዛዛት ነበሩ፡፡ በመጀመሪያው ገበታ ላይ የነበሩት አራቱ ትእዛዛት ከሌሎቹ ስድስት ይልቅ ፈክተው ይታዩ የነበረ ሲሆን ነገር ግን አራተኛው---የሰንበት ትእዛዝ ከሁሉም በላይ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ ሰንበት ተለይቶ የተቀመጠው ለእግዚአብሔር ቅዱስ ስም ክብር ለመስጠት እንደመሆኑ፤ የቅዱሱ ሰንበት ክብርና ቅድስና ዙሪያውን ሞልቶ ይታይ ነበር የሰንበት ሕግ በመስቀል ላይ እንዳልተቸነከረ ተመለከትኩ ይህ ሕግ ተቸንክሮ ቢሆን ኖሮ የቀሪዎቹም ዘጠኝ ሕጎች ዕጣ ፈንታ ተመሳሳይ በሆነና እኛም ሁሉንም ሆነ አራተኛውን ሕግ ለመጣስ ነጻነት ባገኘን ነበር እግዚአብሔር የሰንበትን ሕግ እንዳልለወጠውና ፈጽሞ ሊለውጠው እንደማይችል ተመለከትኩ፡፡ ነገር ግን ጳጳሳዊው ሥርዓት ከሰባተኛው ቀን ወደ ሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ለውጦት ነበር---ጊዜና ሕግን ይለውጣልና : EWAmh 17.3

እግዚአብሔር ሰንበትን ከሰባተኛው ቀን ወደ ሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ለውጦት ቢሆን ኖሮ አሁን በሰማያዊው መቅደስ ቅድስተቅዱሳን ውስጥ በድንጋይ ጽላቶቹ ላይ ተጽፎ የሚገኘው የሰንበት ትእዛዝ fሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን የእግዚአብሔር አምላክህ ሰንበት ነው የሚል በሆነ ነበር፡፡ ነገር ግን እኔ ያነበብኩት በእግዚአብሔር ጣቶች ተጽፈው በሲና ተራራ ለሙሴ ከተሰጡትን ጋር ተመሳሳይ የሆነውን ነው---«ሰባተኛው ቀን የእግዚአብሔር አምላክህ ሰንበት ነው»፡፡ ሰንበት ቅዱስ መሆኑንና የዚህ ቀን ቅድስና እውነተኛይቱን የእግዚአብሔር እስራኤልና የማያምኑትን እንደ ግድግዳ በመክፈል የሚቀጥል መሆኑን ተመልክቻለሁ:: በዚህም ሰንበት የእግዚአብሔርን ውድ ልጆች---የቅዱሳንን ልብ በአንድ ለማዋሃድ የሚቀርብ ታላቅ ጥያቄ ነው:፡፡ EWAmh 18.1

እግዚአብሔር ሰንበትን የማይመለከቱና የማይጠብቁ ልጆች እንደነበሩት ተመልክቼአለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች በሰንበት ላይ ያለውን ብርሃን አልተቃወሙም:: እንዲሁም በመከራው ጊዜ መጀመሪያ ላይ ሰንበትን ይበልጥ በሙ-ላት ለመስበክ ስንወጣና በይፋ ስንናገር በመንፈስ ቅዱስ ተሞልተን ነበር፡፡ ይህ ድርጊት የሰንበትን ውነት---ሐሰት ነው ብለው ማስተባበል ያልቻሉትን አብያተክርስቲያናትና የይስሙላ አድቬንቲስቶችን አስቆጣ፡፡ በዚህን ወቅት የእግዚአብሔር ምርጦች የያዝነውን እውነት በግልጽ በመመልከት ከያሉበት ወጥተው ከእኛ ጋር በስደት ውስጥ አለፉ፡፡ ሰይፍ፣ ረሃብ፣ ቸነፈርና ታላቅ ውዥንብር በምድሪቱ ላይ ተመልክቼ ነበር ርኩ ሳኑ በላያቸው ፍርድ ይዘን እንደመጣን አድርገው በማሰብ---ክፉው ጸንቶ እንዲኖር EWAmh 18.2

በሚል በእኛ ላይ ተነሱ-ከምድር ገጽም ሊያጠፉን መከሩ፡፡ በመከራው ወቅት ሁላችንም ከከተማዎችና ከመንደሮች እየወጣን ተሰደድን፡፡ ይህ የሆነው ኃጥአን ሰይፍ ይዘው በየቅዱሳን መኖሪያ ቤት እየገቡ አደና በማካሄዳቸው ነው:፡፡ ምንም እንኳ ኃጥአን ሊግደሉን ሰይፋቸውን ቢመዙም ነገር ግን ሰይፋቸው ልክ እንደ ገለባ ተልፈስፍሶና ተሰባብሮ ይወድቅ ነበር: ከዚያም ጌታ ያድነን ዘንድ ቀንና ሌሊት ጩኸታችንን ማሰማት ቀጠልን፡፡ኸታችንም በእግዚአብሔር ፊት ደረሰ፡፡ ጸሐይዋ ወጣች, ጨረቃዋ ጸንታ ቆመች፣ ጅረቶች መፍሰሳቸውን አቆሙ፣ ጥቋቁርና ግዙፍ ደመናዎች በመው ጣት እርስ በርሳቸው ተጋጩ፡፡ ሆኖም ሰማይና ምድርን ያናወጠ የእግዚአብሔር ድምፅ እንደ ብዙ የውሖች ድምፅ የመጣበት በክብር የተሞላና የተረጋጋ አንድ ግልጽ ስፍራ ነበር፡፡ ሰማዩ ክፍት---ዝግት ይላል---የተዘበራረቀ ዓይነት ክስተትም ይስተዋላል፡፡ ተራሮች በሚነፍሰው ነፋስ እንደ መቃ ይዋልላሉ፣ ቋጥኞችም ከላያቸው እየተናዱ ይወጣሉ፡፡ እንዲሁም ባሕሩ እሳት ላይ እንደተጣደ ድስት እየተንተከተከ ቋጥኞችን ወደ ደረቁ ምድር ይተፋ ነበር፡፡ የየሱስን መምጫ ቀኑንና ሰዓቱን እግዚአብሔር ሲናገርና ዘላለማዊውን ኪዳን ለሕዝቡ ሲሰጥ---ቃላቱ ወደ ምድር እየተንከባለሉ እየወረዱ ሳለአንድ ዐረፍተነገር ተናገረና ጸጥታ ሰፈነ፡፡ ጻድቃን በእስራኤል አምላክ ላይ ዐይኖቻቸውን ተክለው እንደ ታላቅ የነጎድጓድ ድምጽ ወደ ምድር እየተንከባለሉ ይወርዱ የነበሩትን ከያህዌ አፍ የሚወጡትን ቃላት ያደምጡ ነበር፡፡ ይህ ክስተት በታላቅ ክብርና ግርማ የተሞላ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር አንደበት በሚወጠት በእያንዳንዱ ዐረፍተነገር መጨረሻ ላይ---ቅዱሳኑ «ክብር ይሁን! ሐሌሉያ!” በማለት ይጮኹ ነበር፡፡ ገጽታቸው በምላካዊው ክብር ያበራ ነበር፡፡ ሙሴ ከሲና ተራራ ላይ ሲወርድ የነበረው ዓይነት የእግዚአብሔር ክብር ጸዳል በላያቸው ይስተዋል ነበር በእነዚህ ሕዝቦች ላይ ይታይ ከነበረው ክብር የተነሳ ኃጥአን ሊመለከቷቸው አልቻሉም የአግዚአብሔርን ሰንበት ቅዱስ አድርገው በጠበቁ ወገኖች ላይ ይወርድ የነበረውን ፍጻሜ የሌለውን በረከት ተከትሎ በአውሬውና በምስሉ ላይ ኃያል የድል ኸት አስተጋባ፡፡ EWAmh 19.1

ከዚያም ምድሪቱ የምታርፍበት ኢዮቤሊዩ ጀመረ: ፈሪሃ እግዚአብሔር የነበረው ባሪያ ታስሮ የነበረበትን ሰንሰለት በመበጣጠስ በድል አድራጊነት ሲነሳ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ድምፅ ቃላት ማስተዋል ያልቻለው ክፉው አሳዳሪው ግራ ተጋብቶና የሚያደርገው ጠፍቶት ተመልክቼአለሁ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ግዙፍ ነጭ ደመና እየተስፋፋ በመምጣት ከመቼውም ይልቅ ተወዳጅ ገጽታ መያዝ ጀመረ፡፡ በዚህ ደመና ላይ የሰው ልጅ ተቀምጦ ነበር: በመጀመሪያ የሱስን በደመናው ላይ አልተመለከትነውም ነበር፤ ነገር ግን ወደ ምድር እየቀረበ ሲመጣ ተወዳጅ ማንነቱን መመልከት ቻልን፡፡ ይህ ደመና በሰማይ ያለው የሰው ልጅ ምልክት ሆኖ ነበር የተገለጠው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ድምጽ ያንቀላፉ ቅዱሳንን ተጣራ፧ እነርሱም በክብር የተሞላውን የማይሞተውን አካል ለበሱ፡፡; በህይወት የነበሩት ጻድቃን ብቅጽበት በመለወጥ ተነጠቁና በደመና ሠረገላ ተገናኗቸው፡፡ ደመናው እጅግ ግርማ በተሞላው አኳኋን ሽቅብ ይወጣ ነበር፡፡ በሠረገላው ዳርና ዳር በኩል--ክንፎች፧ ከበታቹ ደግሞ መንኮራኩር ነበር፡፡ ሠረገላው ሽቅብ እየተሽከረከ ረ ሲወጣ መንኮራኩሮቹ «ቅዱስ» እያሉ ከፍ ያለ ድምጽ ያሰሙ ነበር፡፡ ክንፎቹም እንዲሁ በተንቀሳቀሱ ቁጥር «ቅዱስ» እያሉ ይጮኹ ነበር ደመናውን ዙሪያውን ከበው የነበሩ ቅዱሳን መላእክትም እንዲሁ «ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ---ጌታ አምላክ ገናና!» በማለት ይጮኹ ነበር፡፡ ደግሞም በደመናው ውስጥ የነበሩት ቅዱሳን «ክብር ይሁን! ሐሌሉያ!” በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ይኹ ነበር የሱስ የወርቃማዋን ከተማ በራፍ ወለል አድርጎ በመክፈት ወደ ውስጥ እየመራን ገባ፡፡ «የእግዚአብሔርን ትእዛዛት” በመጠበቃችንና «የህይወት ዛፍ ባለመብት” በመሆናችን እነሆ በዚህ ስፍራ የእንኳን ደኅና መጣችሁ አቀባበል ተደረገልን፡፡ EWAmh 20.1