ቀደምት ጽሑፎች
35—የመጀመሪያው የክርስቶስ ምጽአት
የሱስ ሰብዓዊውን ተፈጥሮ ወስዶና እራሱን እንደ ሰው ትሁት አድርጎ በሰይጣን ፈተና ሥቃይ ወደ ተቀበለበት ጊዜ ተወሰድኩ፡፡ EWAmh 104.1
የእርሱ ውልደት በዓለም ዘንድ ታላቅ ስፍራ አልተሰጠውም ነበር እርሱ በበረት ውስጥ ቢወለድና በእንስሳት መመገቢያ ግርግም ውስጥ ቢተኛ ም ነገር ግን የእርሱ ልደት ከማንኛውም የሰው ልጅ በላይ ክብር ተችሮት ነበር፡፡ የሰማይ መላእክት የየሱስን የመጀመሪያ ምጽhት ለእረኞች ሲያበስሩ ሳለ ምስክርነታቸው በእግዚአብሔር ብርሃንና ክብር የታጀበ ነበር፡፡ የሰማይ ሠራዊት በገናዎቻቸውን በመንካት እግዚአብሔርን አወደሱ፡፡ በሞቱ---ሰላምን፣ ደስታንና ዘላለማዊ ህይወትን ለሰዎች ለማምጣት ሲል የእግዚአብሔር ልጅ ወደ ወደቀው ዓለም ያደረገውን የመጀመሪያ ምጽአት በድል አድራጊነት አበሰሩ፡፡ እግዚአብሔር የልጁን የመጀመሪያ ምጽአት አከበ ረው፧ መላእክትም ኣመለኩት፡፡ ሲጠመቅ የእግዚአብሔር መላእክት በዙሪያው ነበሩ፡፡ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በመውረድ አበራበት፡፡ ሰዎች በእጅጉ ተደንቀውና ዓይኖቻ ቸውን ተክለው እየተመለከቱት ሳለ «በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው» የሚል የአብ ድምፅ ከሰማይ ተሰማ፡፡ EWAmh 104.2
አዳኙ ለመሆኑ ዮሐንስ የሚያውቅበት ምልክት በዮርዳኖስ ወንዝ በእጁ ለመጠመቅ የመጣው እርግጠኛ አልነበረም፡፡ ሆኖም የእግዚአብሔርን በግ እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት ነበር፡፡ ያ ምልክት ደግሞ በየሱስ ላይ ባ ረፈው ሰማያዊ ርግብና ዙሪያውን ባንጸባረቀው የእግዚአብሔር ክብር ተሰጥቶት ነበር ዮሐንስ እጁን ወደ የሱስ በማመላከት «እነሆ! የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ» በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ EWAmh 104.3
የሱስ ቃል የተገባው የዓለም አዳኝና መሲህ መሆኑን ዮሐንስ ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል፡፡ የእርሱ አገልግሎት እየተገባደደ ሲሄድ ደቀ መዛሙርቱ - ወደ የሱስ እንዲመለከቱና እንደ ታላቅ መምህር እርሱን እንዲከተሉ አስተምሯቸው ነበር የዮሐንስ ህይወት በሐዘን የተሞላና እራስን የመካድ ነበር፡፡ እርሱ የመጀመሪያውን የክርስቶስ ምጽአት ቢያበስርም ነገር ግን ተአምራቱን ለመመልከትና በእርሱ ለተገለጠው ኃይል ተጠቃሚ እንዲሆን ኣልተፈቀደለትም ነበር የሱስ ወደ መምህርነት ተግባሩ ባመራ ጊዜ ዮሐንስ መሞት እንደነበረበት አውቆ ነበር :: ከም ድረ በዳ ውጪ ድምጹ ይሰማ የነበረ አልፎ አልፎ ነበር ህይወቱን በብቸኝነት ይገፋ የነበረው ዮሐንስ ከአባቱ ቤተሰቦች ጋር ሳይቀላቀል ተልዕኮ ውን ከግብ ለማድረስ ትቶአቸው ሄደ፡፡ አያሌዎች የተጨናነቁትን ከተሞችና መንደሮች እየተዉ ድንቅ የሆኑትን የነቢዩን ቃላት ለማድመጥ ወደ ምድ ረበዳ ይጎርፉ ነበር፡፡ ዮሐንስ ሊመጣ የሚችለውን ውጤት ሳይፈራ ኃጢአትን ገሰጸ እንዲሁም መንገዱን ለእግዚአብሔር በግ አዘጋጀ፡፡ EWAmh 104.4
ሔሮድስ ጠንካራ የሆኑትንና ወደ እራሱ ያመላክቱ የነበሩትን የዮሐንስን ምስክርነቶች ሲሰማ የእርሱ ደቀ መዝሙር ለመሆን ምን ማድረ7 እንዳለበት ከውስጥ በመነጨፍላጎት ጠየቀ፡፡ ሔሮድስ ወንድሙ ገና በህይወት እያለ ሚስቱን ሊያገባት ማሰቡን ዮሐንስ ያውቅ ስለነበር ይህ አካሄድ ሕግን የተከተለ አለመሆኑን ነገረው፡፡ ሔሮድስ በዚህ ዙሪያ አንዳችም ዓይነት መስዋዕ ት ለመክፈል ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በመሆኑም የወንድሙን ሚስት ካገባት በኋላ በእርሷ ተጽእኖ አማካኝነት ዮሐንስ ተይዞ እንዲታሰር ተደረገ፡፡ እንዲህም ሆኖ ግን ሔሮድስ ያቀደው ዮሐንስን ለመልቀቅ ነበር፡፡ EWAmh 105.1
ዮሐንስ በእስር ላይ እንዳለ ስለ አስደናቂዎቹ የየሱስ ሥራዎች በደቀ መዛሙርቱ አማካኝነት ለመስማት ችሎ ነበር፡፡ እርሱ እነዚያን በጸጋ የተሞሉ ቃላት በጆሮው ለማድመጥ አልተቻለውም ነበር፡፡ ሆኖም ደቀ መዛሙርቱ ስለ ሰሙት ነገር አስፈላጊውን መረጃ በማቀበል አጽናኑት፡፡ ወዲያውኑ የሔሮድስ ሚስት ያስከተለችውን ተጽእኖ ተከትሎ ዮሐንስ እራሱን ተቆርጦ ተገደለ፡፡ የሱስን በትህት የተከተሉ፣ ከከናፍርቱ ይወጡ የነበሩትን አጽናኝ ቃላት ሲያደምጡ የነበሩና የሠራቸውን አስደናቂ ሥራዎች የመሰከሩ ደቀ መዛሙርት አብልጠው ስለከበሩና በህይወታቸው የላቀ ደስታ ስለነበራቸው ከመጥምቁ ዮሐንስ ይበልጡ ነበር፡፡ EWAmh 105.2
ዮሐንስ የመጀመሪያውን የየሱስ ምጽአት ለማወጅ በኤልያስ መንፈስና ኃይል መጣ፡፡ ወደ መጨረሻዎቹ ቀናት እንድመለከት ከተደረኩ በኋላ ስለ ቁጣው ቀንና ስለ የሱስ ዳግም ምጽአት ያውጁ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል መሄድ ያለባቸውን ዮሐንስ ወክሎአቸው እንደነበር ተመለከትኩ፡፡ EWAmh 105.3
የሱስ በዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ በዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ምድረበዳ ሄደ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ለዚያ ልዩና ብርቱ ፈተና አዘጋጅቶታል፡፡ እርሱ ለአርባ ቀናት ያህል በሰይጣን እየተፈተነ ቢቆይም ነገር ግን በእነዚያ ቀናት ውስጥ አንዳችም ነገር አልበላም:: በዙሪያው የነበረ ማንኛውም ነገር ሰብዓዊውን ተፈጥሮ ለውድቀት ከመጋበዝ ውጪ አንዳችም አስደሳች ነገር አልነበረውም፡፡ እርሱ በዚያ አታካች ምድ ረበዳ ከዱር አራዊትና ከዲያብሎስ ጋር ቆየ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ በጾምና በሥቃይ ገርጥቶና ከመጠን በላይ ከስቶ ነበር ሆኖም እርሱ የሚራመድበት iዳና ተለይቶ በመቀመጡ ይህንኑ የመጣበትን ሥራ የግዴታ ከግብ ማድረስ ነበረበት፡፡ EWAmh 105.4
ሰይጣን የእግዚአብሔርን ልጅ ሥቃይ እንደ ልዩ አጋጣሚ በመቁጠርና እራሱን እንደ ሰው ትሁት አድርጎ የቀረበውን የሱስ እንደሚያሸንፈው ተስፋ በማድረግ ልዩ ልዩ ፈተናዎችን በማምጣት ሊያደናግረው ዝግጅቱን አጠናቆ ነበር «የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እነዚህን ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ››፡፡ ሰይጣን እንዲህ በማለት የፈተነው የሱስ መለኮታዊ ኃይሉን ተጠቅሞ በትህትና መሲህ መሆኑን እንዲያረጋግጥ ለማድረግ ነበር «“ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል” EWAmh 106.1
ሰይጣን ጥል ለማንሳት ይሞክር የነበረው በየሱስ የእግዚአብሔር ልጅነት ዙሪያ ነበር፡፡ ወደ ደካማና በሥቃይ የተጎሳቆለ ሁናቴው በማመላከት ከየሱስ ይልቅ ሰይጣን የበረታ መሆኑን በትዕቢት አረጋገጠለት፡፡ ነገር ግን ከሰማይ የተነገሩት «በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው» የተሰኘ ት ቃላት የሱስን ከእነ ሥቃዩ አጽንተው ለማቆም ብቁ ነበሩ፡፡ ክርስቶስ ብርቱ ኃይል እንዳለው ወይም የዓለም አዳኝ ስለመሆኑ ሰይጣንን ለማሳመን ምንም ማድረግ እንደሌለበት ተመልክቼ ነበር፡፡ ሰይጣን በክርስቶስ ሥልጣን ስር ለመገዛት ፈቃደኛ ባለመሆን ከሰማይ ተቆርጦ ቀረ እንጂ ስለ እግዚአብሔር ልጅ ሥልጣንና ኃይል በቂ መረጃ ነበረው:፡፡ EWAmh 106.2
ሰይጣን ኃይሉን ለማሳየት ሲል የሱስን ተሸክሞ ወደ የሩሳሌም በመውሰድ በቤተመቅደሱ ጉልላት ላይ አቆመውና እራሱን ከዚያ ከፍተኛ ስፍራ ቁልቁል በመወርወር የእግዚአብሔር ልጅ ለመሆኑ ማረጋገጫ እንዲሰጥ ፈተነው፡፡ ሰይጣን ይህን ሲለው የሱስ የተባለውን እንዲፈጽም የሚያበረታቱ ቃላትን በመሰንዘር ነበር፡፡ «እንዲህ ተብሎ ተጽፎአልና እግርህ በድንጋይ እንዳይሰናከል በእጃቸው ያነሱህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተያዝልሃል» የሱስ ሲመልስለት «እንዲሁም በመጻሕፍት እግዚአብሔር አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ተጽፎአል” አለው፡፡ የሰይጣን ምኞት የሱስ በአባቱ ምህረት ላይ ተማምኖ ተልዕኮውን ከማጠናቀቁ አስቀድሞ ህይወቱን አደጋ ላይ እንዲጥል ማድረግ ነበር፡፡ ሰይጣን የደኅንነት እቅድ ይከሽፋል የሚል ተስፋ ቢኖረው ም ነገር ግን ይህ ዕቅድ በእጅጉ ጥልቅ በመሆኑ በሰይጣን ሊገረሰስ ወይም ሊበላሽ የማይችል ነበር፡፡ EWAmh 106.3
ክርስቶስ ለሁሉም ክርስቲያኖች ምሳሌ ነው:፡፡ ክርስቲያኖች ፈተና ሲደርስባቸው ወይም በመብቶቻቸው ላይ ተቃርኖ ሲገጥማቸው በትዕግሥት ሊያልፉ ይገባል፡፡ ጉዳዩ በቀጥታ እግዚአብሔር የሚከብርበት ካልሆነ በቀር አማኞች በጠላቶ ቻቸው ላይ ድል ይቀዳጁ ዘንድ ጌታ ኃይሉን እንዲያሳይ እርሱን የመጥራት መብት እዳላቸው ሊሰማቸው አይገባም: የሱስ ከቤተመቅደሱ አናት ላይ እራሱን ቢጥል ኖሮ በወቅቱ ከሰይጣንና ከእግዚአብሔር መላእክት በቀር ማንም ምስክር መሆን ስለማይችል ድርጊቱ አብ እንዲከብር አያደርገውም ነበር ደግሞም ለዚህ የከፋ ጠላት ኃይሉን ማሳየት ለጌታ ፈታኝ ሊሆን ይችል ነበር የሱስ ድል ሊያደርገው ለመጣው ለዚህ ፍጡር ኃይሉን ማሳየት አሳፋሪም በሆነ ነበር EWAmh 106.4
«ከዚያም ዲያብሎስ ወደ አንድ ከፍታ ቦታ አውጥቶት የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው፧ እንዲህም አለው የእነዚህ መንግሥታት ሥልጣንና ክብር ሁሉ ለእኔ ተሰጥቶአል እኔም ለምወደው ስለምሰጥ ለአንተእሰጥሃለሁ፧ ስለዚህ ብትስግድልኝ ይህ ሁሉ የአንተይሆናል: የሱስም መልሶ ለጌታ አምላክህ ስገድ እርሱን ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎhል አለው፡፡” EWAmh 107.1
ሰይጣን የምድርን ነገሥታት በየሱስ ፊት ያቀረባቸው በእጅጉ መስህብነት በነበረው ብርሃን ነበር የሱስ በዚያ ቦታ ላይ ቢሰግድለት ኖሮ ምድር የእኔ ግዛት ናት ማለቱን አምኖ በለቀቀለት ነበር የደኅንነት እቅድ ተግባራዊ መሆን ካለበትና የሱስ ሰብዓዊውን ፍጡር ለመዋጀት መሞት ካለበት የሰይጣን ኃይል የግዴታ እንደሚገደብ፣ በመጨረሻም ከእርሱ እንደሚወሰድና እንደሚጠፋ ያውቅ ነበር፡፡ በመሆኑም የሚቻል ከሆነ ይህ በእግዚአብሔር ልጅ የተጀመረ ዕቅድ የታለመው ዓላማ ላይ ሳይደርስ ማናከል የእርሱ የተጠና ዘዴ ነበር፡፡ ሰብዓዊውን ፍጡር የመዋጀቱ ዕቅድ ባይሳካ ኖሮ ሰይጣን የእኔ ነው የሚለውን ግዛት እንደያዘ ከመቅረቱ በተጨማሪ በሰማይ አምላክ ስፍራ እንደሚነግሥ አድርጎ እራሱን በሸነገለ ነበር EWAmh 107.2
የሱስ ኃይሉንና ክብሩን ሁሉ ትቶና ሰማይን ለቅቆ ወደ ምድር ሲመጣ ሰይጣን እራሱን ከፍ በማድረግ የእግዚአብሔር ልጅ በእርሱ ኃይል ሥር እንደሆነ አድርጎ አሰበ፡፡ በኤደን ለነበሩት ቅዱሳን ጥንዶች ያቀረበው ፈተና በቀላሉ ያሰበውን ያስገኘለት ሰይጣን አሁን ደግሞ በተለመደው ሰይጣናዊ አታላይነቱ በመጠቀም የእግዚአብሔርን ልጅ ሳይቀር ለመጣል ተስፋ አደ ረገ፡፡ ይህ እቅዱ ከተሳካለት ህይወቱንም ሆነ ግዛቱን ያድናል፡፡ እርሱ የሱስን በመፈተን ከአባቱ ፈቃድ እንዲያፈነግጥ ማድረግ ቢችል ዓላማው ይሰምራል፡፡ ነገር ግን የሱስ «ጌታ አምላክህን አትፈታተነው” በማለት ይህን ፈታኝ ገጸው:: እርሱ የሚሰግደው ለአባቱ ብቻ ነበር ምድር የራሴ ግዛት ናት የሚለው ሰይጣን ለየሱስ በተዘዋዋሪየምድር ነገሥታት ለአንተ ይገዙልህ ዘንድ ሥቃይ መቀበልም ሆነ መሞት አያስፈልግህም፧ ብቻ ለእኔ ስገድልኝ፧ የነድር ሐብትም ሆነ ንብረት የአንተ ይሆናሉ--እያለው ነበር፡፡ ነገር ግን የየሱስ አቋም ጽኑና የማያወላውል ነበር፡፡ እርሱ ህይወቱን መስዋዕ ት አድርጎ በመስጠት የሰይጣንን ግዛት በመዋጀቱ በሰማይና በምድር ያሉ ሁሉ እራሳቸውን ለእርሱ የሚያስገዙበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን አወቀ:: በመሆኑም ሥቃይ የተሞላውን ህይወትና አስፈሪውን ሞት መረጠ፡፡ በተመሳሳይ ስይጣን ከዚህ በኋላ የሱስንም ሆነ በክብሩ ውስጥ ያሉትን ቅዱሳን መበጥጡን ያቆም ዘንድ የሚጠፋበት ሞት በእጁ ይሰጠዋል፡፡ EWAmh 107.3