ቀደምት ጽሑፎች
34—የደኅንነት ዕቅድ
የሰው መጥፋት እንደታወቀ ሰማይ በሃዘን ተሞላ፡፡ እግዚአብሔር የፈጠራት ዓለም ዕጣ ፈንታ---ሥቃይ ህመምና ሞት ሆነ፡፡ ምድር ሟች በሆኑ ፍጡራን ተሞላች፡፡ ጥፋተኛው ከበደሉ ማምለጫ መንገድ አልነበ ረውም፡፡ መላው የአዳም ቤተሰብ መሞት ነበረበት፡፡ በተወዳጁ የሱስ በገጽታ ላይ ሐዘንና ርኅራኄ አጥልቶ ተመለከትኩ፡፡ ወዲያውኑ አብን ወደ ከበበው ሊገለጽ የማይቻል ብርሃን ሲቀርብ ተመለከትኩት፡፡ የሱስ ከአባቱ ጋር በቅርበት እየተነጋገረ መሆኑን መልአኩ ነገረኝ:፡፡ የሰስ ከአባቱ ዘንድ ሲወጣ በመላእክቱ ዘንድ ይታይ የነበረው ጉጉትና ጭንቀት ብርቱ ነበር ሦስት ጊዜ ያህል ሊገለጽ በማይችል ከአብ ዘንድ በሚመነጭ ብርሃ, ውስጥ ተዘግቶበት የነበረ ሲሆን---በሦስተኛው ጊዜ ከአብ ዘንድ ሲወጣ የወልድ አምሳል መታየት የሚችል ነበር፡፡ የተረጋጋ ገጽታ የተላበሰ፣ ከማንኛውም ጭንቀትና ጥርጣሬ ነጻ የሆነና ደግነቱና አፍቃሪነቱ ቃላት ሊገልጹት ከሚችሉት በላይ አንጸባራቂ ነበሩ፡፡ ከዚያም ለጠፋው ሰው ማምለጫ መንገድ መዘጋጀቱን ለመላእክቱ ሠራዊት ይፋ አደረገ፡፡ ሰብዓዊው ፍጡር ይቅርታ ያገኝ ዘንድ እርሱ የእነርሱን የሞትን ፍርድ በመውሰድ ሕጉን ታዝዞ በደሙ በሚከፍለው የኃጢአት መቀጮ ሰው ዳግመኛ ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ በመፍጠር ወደ ውቧ ኤደን ገነት ተመልሶ ከህይወት ዛፍ ፍሬ ይበላ ዘንድ አብን ሲለምን እንደነበርና ይህ እውን መሆን እንደቻለ ለመላእክቱ አበሰራቸው:: EWAmh 100.1
ይህ አዛዣቸው ሁኔታውን ሳይሸፋፍንና አንዳችም ነገር ሳይደብቃቸው የደኅንነትን ዕቅድ በፊታቸው በማስቀመጡ በመጀመሪያ ላይ መላእክቱ ሐሴ ት ማድረግ አልቻሉም ነበር፡፡ የሱስ በአባቱ ቁጣና ጥፋተኛ ሆኖ በተገኘው ሰብዓዊ ፍጡር መሃል በመቆም ክፋትና ውርደት እንደሚደርስበት ፧ አብዛኞቹ ሲጠሉትና ሲቃወሙት ጥቂቶች ብቻ እንደ እግዚአብሔር ልጅ እንደሚቀበሉት ነግሯቸው ነበር፡፡ እርሱ ክብሩን ሁሉ በሰማይ ትቶ ትሁት ሰው ሆኖ ወደ ምድር ይመጣል፡፡ በሰዎች ላይ ወከባ የሚያደርሱ የተለያዩ ፈተናዎችን በመቋቋም የሚታወቀው---እርሱ በፈተና ያሉትን እንደሚረዳ ያውቃል በመጨረሻ የእርሱ የማስተማር ተልዕኮ ክንውን ካገኘ በኋላ በሰዎች እጅ በመሰጠት ሰይጣንና ወኪሎቹ ክፉ ሰዎችን በማነሳሳት የሚያደርሱበትን እያንዳንዱን ግፍና ሥቃይ በመቀበል እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ በሰማይና በምድር በሃል ተሰቅሎ ጭካኔ የተሞላው ሞት እንዲቀበል ይደረጋል፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ በመስቀል ላይ የሚደርስበት ህማም በእጅጉ አስፈሪ ከመሆኑ የተነሳ መላእክት እንኳ ፊታቸውን ከመሸፈን ውጪ ትዕ ይነቱን ለመመልከት ይቸገራሉ፡፡ በእርሱ ላይ የሚደርሰው ሥቃይ ከአካላዊው ጋር ፈጽሞ ሊስተካከል የማይችል አእምሮአዊ ህማም ነው፡፡ የመላው ዓለም ኃጢአት ክብደት በሙሉ በእርሱ ላይ ያርፋል፡፡ የሱስ እንደሚሞትና በሦስተኛው ቀን ተነስቶ ለበደለኛው ሰው ሊማልድ ወደ አባቱ ዘንድ እንደሚያርግ ነግሯቸዋል፡፡ EWAmh 101.1
መላእክቱ ህይወታቸውን በመስጠት ግንባራቸውን መሬት ላይ ደፍተው በፊቱ ተዘረሩ፡፡ የመላእክ ህይወት ዕዳውን መክፈል እንደማይችል በመንገር የሱስ በመሞቱ ብዙዎችን እንደሚያድንና የእርሱ ህይወት ብቻ የኃጢአትን መቀጮ ለመክፈል በአብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው ነገራቸው፡፡ በተጨማሪ እነዚህ መላእክት በተለያዩ ጊዜያት አብረውት በመሆን እርሱን የማበረታታት ድርሻ እንደሚኖራቸው አሳወቃቸው፡፡ እርሱ የወደቀውን ስብዓዊ ተፈጥሮ ሲወስድ የሚኖረው በብርታት ከእነርሱ ጋር መስተካከል እንኳ እንደማይችል በመግለጽ ለሚደርስበት ውርደትና ከፍተኛ ሥቃይ እነርሱ ምስክር እንደሚሆኑ hወሳቸው፡፡ ደግሞም ይህን የሚደርስበትን ሥቃይና በሰዎች መጠላት ሲመለከቱ ጥልቅ በሆነ ስሜት በመነካት ለእርሱ ካላቸው ፍቅር የተነሳ ከእነዚያ ገዳዮች እጅ ሊያድኑት አጥብቀው ቢመኙም ነገር ግን በእርሱ ላይ ሲደርስ የሚመለከቱትን ማንኛውንም ነገር ለመግታት ጣልቃ መግባት የለባቸውም፡፡ ሆኖም በእርሱ ትሣሳዔ ላይ የሚጫወቱት ሚና ይኖራቸዋል፡፡ ይህ የዘላለም ደኅንነት እቅድ ወጥቶአል አባቱም ይህንኑ እቅድ ተቀብሎአል: EWAmh 101.2
የሱስ ቅድስና በተሞላው ኃዘን መላእክቱን በማጽናናትና በማበረታታት በስተመጨረሻ እነዚያ እርሱ የሚዋጃቸው ከእርሱ ጋር እንደሚሆኑ፣ በሞቱ የብዙዎችን ዕዳ በመክፈል በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን እንደሚያጠፋው ነገራቸው፡፡ ደግሞም አባቱ ከሰማይ በታች ያለውን ግዛትና ታላቅነት በሙሉ ይሰጠዋል ከዘላለም እስከ ዘላለምም ይገዛል፡፡ ሰይጣንና ኃጢአተኞች ከዚህ በኋላ ሰማይን ወይም ንጹህዋን ምድር ፈጽሞ በሞቱ---በኃጢአት የወደቀው ሰብዓዊ ፍጡር ከእግዚአብሔር ጋር እርቅ በመፍጠር የሰማያዊው ደስታ ባለቤት ይሆን ዘንድ አባቱ የተቀበለውንና ደስ የተሰኘበትን ይህን እቅድ የሰማይ ሠራዊትም እንዲሁ ይቀበሉት ዘንድ አቀረበላቸው፡፡ EWAmh 102.1
አያውኩም-ይጠፋሉ፡፡ የሱስ ዳግመኛ ንሰራርቶ ሰማይ ቃላት ሊገልጹት በማይችል ደስታ ተሞላ፡፡ የሰማይ ሠራዊትም ከፍተኛ ፍቅርና ክብር የተሞላው የምስጋና ዜማ አዜሙ:፡፡ እግዚአብሔር ከታላቅ ምኅረቱና ትህትናው የተነሳ ውድና ተፈቃሪ ልጁ ለዐመጸኛው ዘር ይሞት ዘንድ በመስጠቱ መላእክት በገናዎቻቸውን በመንካት ከቀድሞው የላቀ ዝማሬ አሰሙ፡፡ ህይወቱን ለሌሎች ይሰጥ ዘንድ ከአባቱ እቅፍ ወጥቶ ብርቱ ሥቃይ፣ መከራና እንግልት የበዛበት እራስን የመካድ ህይወት በመኖር አሳፋሪውን ሞት ለመሞት ለመረጠው የሱስ ምስጋናና ፍቅር የተሞላ ክብር ተቸረው:: EWAmh 102.2
መልአኩ እንዲህ አለ «አብ የተወደደውን ልጁን ያለ ምንም ትግል የሰጠ ይመስልሻል? በጭራሽ! ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ሰብዓዊ ፍጡር ይጥፋ ወይስ ለመተላለፋቸው ይሞትላቸው ዘንድ አብ የሚወደውን ልጁን ይስጥ? በሚለው ዙሪያ ብርቱ ትግል ነበር መላእክት ለሰው ልጅ ደኀንነት ከፍተኛ ፍላጎት በማሳየት የእነርሱ ክብርና ህይወት ለሚጠፋው የሰው ልጅ ደኅንነት ማምጣት የሚችል ከሆነ ከመካከላቸው ይህን ለማድረግ ፈቃደኞች የሆኑ ነበሩ፡፡ ሆኖም የእነርሱ መስዋዕትን የሚፈይደው አንዳችም ነገር አይኖርም፡፡ የሰብዓዊው ፍጡር መተላለፍ እጅግ ግዙፍ ስለነበር የመላእክ ህይት ዕ ዳውን መክፈል አይችልም፡፡ ከእግዚአብሔር ልጅ ሞትና ምልጃ በቀር የጠፋውን ሰው ተስፋ ከመቁረጥ፣ ከሃዘንና ሥቃይ በማዳን ዕዳውን መክፈል የሚችል የለም” EWAmh 102.3
ነገር ግን ለመላእክት የተመደበላቸው የሥራ ድርሻ የነበረ ሲሆን ይኸውም ወደ ሰማይ እየወጡና እየወረዱ የእግዚአብሔር ልጅ በምድር ላይ ለሚኖረው ሥቃይ የተሞላው ህይወት እርሱን ማበረታታትና ማጽናት እንዲሁም ከማንኛውም የክፉ መላእክትና ያለማቋረጥ በሰይጣን ከሚሰነዘር ጽልመት መጠበቅ ነበር፡፡ የጠፉትን ለማዳን ሕጉን መለወጥ ለእግዚአብሔር የማይቻል መሆኑን ተመለከትኩ፡፡ በዚህ የተነሳ ለሰብዓዊው ፍጡር መተላለፍ ተወዳጁ ልጁ ይሰቃይ ዘንድ ፈቀደ፡፡ EWAmh 103.1
ሰይጣን ሰብዓዊውን ፍጡር እንዲወድቅ በማድረግ የእግዚአብሔር ልጅ ከነበረበት የከበረ ስፍራ ማውረድ በመቻሉ እርሱና መላእክቱ ዳግመኛ ደስ ተሰኙ:፡፡ የሱስ የወደቀውን ሰብዓዊ ተፈጥሮ ይዞ ወደ ምድር ሲመጣ ድል አድርጎት የደኅንነትን እቅድ ስኬት እንደሚያጨናግፍ ለመላእክቶቹ ነገራቸው:: EWAmh 103.2
ሰይጣን በአንድ ወቅት ደስተኛና የከበረ መልአክ እንደነበር እንድመለከት ተደረኩ፡፡ ከዚያም አሁን ያለበትን ሁናቴ አየሁ: እርሱ አሁንም ከፍ ያለ ግርማ ይታይበታል፡፡ የወደቀ መልአክ እንደመሆኑ አቋሙ ላይ አሁንም ላቅ ያለ ማንነት ይስተዋልበታል፡፡ ነገር ግን ገጽታው ላይ ጭንቀት፣ ሽብር® ደስተኛ አለመሆን፣ ጥላቻ፣ ተንኮል ማታለልና እያንዳንዱ ክፋት የተሞላው ማንነትን ተላብሶ ይታያል:: በተለይ ተመልክቼው የነበረና በአንድ ወቅት በእጅጉ የከበረው ወጣ ያለ ግንባሩ አሁን ግን ከዓይኖቹ ጀምሮ ወደ ውስጥ መሰብሰብ ጀምሮአል፡፡ እራሱን ለረጅም ዘመን በክፋት በማጉበጡ እያንዳንዱ መልካምና የከበረ የነበረ ነገር መርከሱን ተመለከትኩ፡፡ ዓይኖቹ በጥልቀት የሚመለከቱ---አታላይ፣ አጭበርባሪና ተንኮለኛ ነበሩ:፡፡ አቋሙ ግዙፍ የነበረ ሲሆን ነገር ግን የእጆቹና የፊቱ ሥጋ ልልና የተንጠለጠለ ዓይነት ነበር፡፡ ወደ እርሱ ስመለከት አገጩ በግራ እጁ ላይ አርፎ በጥልቅ ሃሳብ ውስጥ የተዘፈቀ ይመስል ነበር፡፡ በፊቱ ላይ ይነበብ የነበረው ክፋትና ሰይጣናዊ አታላይ ፈገግታ በፍርሃት አንድንቀጠቀጥ አደረገኝ፡፡ ሰይጣን ሰለባው ሊያደርገው ያስበውን እጁ ውስጥ እስኪያስገባው ይህን ፈገግታውን ብልጭ ያደርግና ነገር ግን በወጥመዱ ከከተተው በኋላ ይህ ፈገግታ አስፈሪ ገጽታ እየተላበሰ መሄድ ይጀምራል:: EWAmh 103.3