ቀደምት ጽሑፎች
36—የክርስቶስ አገልግሎት
ሰይጣን ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ከእርሱ ተለይቶ ሄደ፡፡ መላእክት በምድረበዳ ምግብ በማዘጋጀት አገለገሉት፣ አበረታቱት-የአባቱም በረከት በላዩ ነበር፡፡ ጸንፈኛ ፈተናዎቹን ይዞ የመጣው ሰይጣን ባይሳካለትም ነገር ግን ወደ ፊት በተለያዩ ጊዜያት ያንኑ ብልጣ ብልጥ አሳችነቱን ይዞ ወደ የሱስ የአገልግሎት ጊዜያት የሚመጣባቸውን አጋጣሚዎች አሻግሮ ይመለከት ነበር ሰይጣን የሱስን የማይቀበሉትን ሰዎች በማነሳሳት እርሱን አብልጠው እንዲጠሉትና እንዲያጠፉት በማድረግ በእርሱ ላይ ድልን ለመቀዳጀት አሁንም ተስፋ አድርጎአል፡፡ ሰይጣን ከመላእክቶቹ ጋር ልዩ ጉባዔ ጠራ፡፡ በስብሰባቸው አንዳችም ድል መቀዳጀት አለመቻላቸው ተስፋ እንዲነድዱ አድርጓቸው ነበር፡፡ በመሆኑም ከዚህ በኋላ ባለ ኃይላቸው ተነሳስተው ከቀድሞው የከፉ ማሳቻ መንገዶችን የግዴታ ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለባቸው ውሳኔ ላይ ደረሱ፡፡ በእርሱ የዓለም አዳኝነት ዙሪያ በራሱ ሕዝብ አእምሮ ውስጥ አለማመን በመዝራት የሱስ በተልዕኮው ተስፋ እንዲቆርጥ ማድረግ ከውሳኔያቸው አንዱ ነበር፡፡ አይሁዳውያኑ የቱንም ያህል ለሥርዓቶቻቸውና ለመስዋዕቶቻቸው የጸና አቋም ቢኖራቸውም ነገር ግን የተሰጧቸውን ትንቢቶች ለመመልከት ዓይኖቻቸው ከታወሩና መሲህን እንደ ብርቱ ዓለማዊ ንጉሥ አድርገው ካመኑ የሱስን ወደ መናቅና መቃወም ሊያመሩ ይችላሉ፡፡ EWAmh 108.1
በክርስቶስ አገልግሎት ወቅት ሰይጣንና መላእክቱ ሰዎችን በአለማመን፣ በጥላቻና በፌዝ በማነሳሳት በእጅጉ ተጠምደው እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ ብዙውን ጊዜ የሱስ የሰላ እውነትን በመናገር ኃጢአታቸውን ሲገስጽ ሰዎች በቁጣ ይገነፍሉ ነበር እነዚሀ ሰዎች የእግዚአብሔርን ልጅ ህይወት ይቀጥፉ ዘንድ ሰይጣንና መላእክቱ አጥብቀው ይገፋፏቸው ነበር ከአንድ ጊዜ በላይ ድንጋይ አንስተው ሊወግሩት የነበረ ቢሆንም ነገር ግን መላእክት ጥበቃ በማድረግ በቁጣ ከገነፈለው ሕዝብ ወደ ሰላማዊ ስፍራ ገሽ አድርገውት ነበር፡፡ አሁንም ግልጽ የሆነው እውነት ቅዱስ ከሆኑት ከናፍሩ ሲወጣ የሰማው ሕብብ በንዴት ተሞልተው እየገፉት ወደ ከኮረብታ አፋፍ በመውሰድ ቁልቁል ሊጥሉት ቢያስቡም ነገር ግን አሁንም መላእክት ከሕዝቡ ዓይን ስለሰወሩት በመካከላቸው ሰንጥቆ ሄደ፡፡ EWAmh 108.2
አሁንም ታላቁ የደኅንነት እቅድ ይከሽፋል ብሎ ተስፋ ያደርግ የነበረው ሰይጣን የሕዝቡን ልብ ለማደንደንና ለየሱስ ያላቸውን ስሜት መራራ ለማድ ረግ ያለ ኃይሉን አስተባብሮ መሥራቱን ቀጠለ፡፡ የሱስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ የሚቀበሉት በጣም ጥቂቶች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተስፋ በማድረግ የአግዚአብሔር ልጅ ለዚህ ጥቂት ሕዝብ የሚከፍለው ሥቃይና መስዋዕትነት ታላቅና መነጻጸር የማይችል እንዲሆን ለማድረግ አሰበ፡፡ ነገር ግን የሱስን እንደ እግዚአብሔር ልጅ አድርገው የሚቀበሉትና እንደሚያድናቸው የሚያምኑት ሰዎች ቁጥር ሁለት እንኳ ቢሆን የእግዚአብሔር ልጅ እቅዱን ገቢራዊ ያደረግ እንደነበር ተመልክቻለሁ:: EWAmh 109.1
የሱስ ሥራውን የጀመረው በሰይጣን የሥቃይ ግዞት ሥር የነበሩትን ነጻ በማውጣትና ኃይሉን በመበጣጠስ ነበር፡፡ እርሱ ለታመመው ጤንነቱን በመመለስ፣ ለታወረው የዓይን ብርሃኑን በመስጠትና አንካሳውን በመፈወስ በደስታ እንዲፈነጥዙና ለእግዚአብሔር ክብር እንዲሰጡ አድርጎአል፡፡ ለብዙ ዓመታት ጭካኔ በተሞላው የሰይጣን ኃይል ጥብቅ ግዞት ስር ይማቅቁ ለነበሩ ጤንነታቸውን መልሶላቸዋል፡፡ ደካማውን፣ ሲርበተበት የነበረውንና ያዘነውን ጸጋ በተሞሉ ቃላት አጽናንቶአል፡፡ የሞተውን ህይወት ሰጥቶ በማስነሳቱ ይህ አስደናቂ ኃይል እንዲገለጥ ላደረገው እግዚአብሔር ክብር ሰጥተዋል፡፡ እርሱ ላመiበት ሁሉ አስደናቂ ነገሮች አድርጎአል፡፡ EWAmh 109.2
የክርስቶስ ህይወት በርኅራኄ፣ በማጽናናት እንዲሁም በፍቅር ቃላትና ድርጊቶች የተሞላ ነበር፡፡ እርሱ ምን ጊዜም ከጠፉበት ሊፈልጋቸው የመጣውን ሰዎች በአትኩሮት በማድመጥ ሥቃያቸውን ያስታግስ ነበር፡፡ የእርሱን መለኮታዊ ኃይል ማረጋገጫ የነበሩ አያሌ ሕዝቦች በራሳቸው ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡ ሆኖም ሥራው በተሳካ ሁኔታ ከተጠናቀቀ በኋላ ብዙዎች ትሁትና ኃያል በሆነው መምህር ሐፍረት ተሰምቶአቸው ነበር፡፡ ገዢ ዎችና ባለሥልጣናት በርሱ ባለማመናቸው ሕዝቡ የሱስን ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ እርሱ የሐዘን ሰው ነበር በመሆኑም በዚህ አራስን የመካድ ህይወት ውስጥ ጸንቶ መት ሊሆንላቸው አልቻለም: ሆኖም ብዙዎች የእግዚአብሔርን ልጅ በመከል ይሰጣቸው የነበሩ መመሪያዎችን ያምጡ ነበር እንዲሁም ጸጋ በተሞላው አኳኋን ከከናፍሩ ይወጡ በነበሩ ቃላት ሐሴት ያደርጉ ነበር። ቃላቶቹትርጉም ያላቸውና ግልጽ በመናቸው ደካማው እንኳ የሚያስተውላቸው ነበሩ: EWAmh 109.3
የኃይማኖት መሪዎችና ገዢዎች የአዳኙን ህይወት እንዲቀጥፉ በማመስ ሰይጣንና መላእክቱ የአይሁዳውያኑን ዓይኖች አሳወሩ፧ ማስተዋላቸው እንዲጨልም አደረጉ:: የሱስን ይዘው እንዲያመጡ የተላኩ ሰዎች ወደ እርሱ በቀረቡ ጊዜ ሰብዓዊውን መከራና ሥቃይ በአጽናኝ ቃላትና ርኅራኄ ሲታደግ በመመልከታቸው በእጅጉ ተደንቀው ነበር: እነዚህ ሰዎች ከአንደበቱ ይወጡ በነበሩ በፍቅር በተሞሉና በለሰለሱ ቃላት ደካማውንና በሥቃይ ያለውን ሲያበረታ ሰሙ። በሥልጣን ሲናገር፣ የሰይጣንን ኃይል ሲገስጽና ምርኮውን ነጻ ሲሉቅ ተመለከቱ: ከየሱስ አንደበት ይወጡ የነበሩ በጥበብ የተሞሉ ቃት በመደመማቸው እጆቻቸውን ሊሰነዝሩበት አልቻሉም:: በመሆኑም የሱስን ሳይዙ ባዶ እጃቸውን ወደ ላኳቸው ቀሳውስትና ሽማግሌዎች ተመለሱ «ለምን አላመጣችሁተም? ተብለው በተጠየቁ ጊዜ ምስክር ለሆባቸው ተአምራት፣ በቅድስና ስለተሞሉት የጥበብ ቃላት፣ ስለ ፍቅርና ስለ ሰሙት የዕውቀት ቃል ከተናገሩ በኋላ ‹እንደዚህ ሰው ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም, በማለት ንግግራቸውን ቋጩ። የተናገሩትን ያደመጡት የኃይማኖት መሪዎቹ በእርሱ ተታላችኋል በማለት ሲከሷቸው ሌሎች ኃላፊዎች ደግሞ ሳይዙት ባዶ እጃቸውን በመምጣታቸው ሃፍረት እንደተሰማቸው ገለጹ: ቀሳውስቱ ንቀት በተሞላው አነጋገር ከፊዎች መካከል በእርሱ ያመነ እንዳለ ጠየቁ:: ብዛት ያላቸው የሕግ ሰዎችና ሽማግሌዎች በእርሱ አምነው እንደነበር ተመልክቻለሁ ሆኖም ሰይጣን እነዚህ ሰዎች ምላሽ ከመስጠት እንዲቆጠቡ አድርጓቸዋል:: የዝምታቸው መንስዔ ከእግዚአብሔር ይልቅ በሕዝቡ ሊደርስባቸው የሚችለው ነቀፋ ስላስፈራቸው ነበር እስከዚህ ጊዜ ድረስ የሰይጣን ማሳቻ ዘዴና ጥላቻ የደኅንነት እቅድ እንዲሰናከል ማድረግ አልቻለም ነበር:: EWAmh 110.1
የሱስ ወደዚህ ምድር የመጣበት ተጨባጭ ዓላማ ፍጻሜ ወደሚያገኝበት ጊዜ ተቃርቦ ነበር ሰይጣንና መላእክቱ በአንድ ላይ በመሰባሰብ የራሱ ሕዝብ ይገደል እያለ እንዲጮኽ፣ እንዲዘብቱበትና ጭካኔ በተሞላው አኋን እንዲገድሉት ለማሳሳት መሩ: ይህን ያቀዱት የሱስ በእንዲህ ያለው የሕዝቡ ምላሽ ቅር በመሰኘትና በጥላቻ በመሞላት ከሚደርስበት ውርደት ያፈገፍጋል ከሚል አስተሳሰብ በመነሳት ነበር:: EWAmh 110.2
ሰይጣን ዕቅዶቹን እያወጣ በነበረበት ወቀት የሱስ የግድ ማለፍ ስለነበረበት አስቸጋሪ ጎዳና ተሰቅሎ ስለ መሞቱና በሦስተኛው ቀን እንድገና ስለመነሳቱ እየነገራቸው ነበር: ሆኖም ደቀ መርቱ የነበራቸው ማስተዋል በእጅጉ ደካማ ስለ ነበር ምን እንደነገራቸው እንኳ ማስተዋል አልቻሉም:: EWAmh 110.3