ቀደምት ጽሑፎች
33—የሰው ውድቀት
ቅዱሳን መላእክት ኤደን ገነትን በመጎብኘት ስለ ኤደን ገነት ህይወታቸውና ስለ ሰይጣን አመጻ በተደጋጋሚ ነግረዋቸው ነበር፡፡ መላእክቱ ስለ ሰይጣን በመንገር ሁለቱ እንዳይለያዩ ነገር ግን ከተለያዩ ከወደቀው ጠላት ጋር ሊገናኙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋቸው ነበር፡፡ የአዳምና ሔዋን ደኅንነት የተረጋገጠ መሆን የሚችለው ፍጹም በሆነ መታዘዝ መሆኑን በመግለጽ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ትእዛዝ ፍጹም አድርገው ይጠብቁ ዘንድ እነዚሁ መላእክት ነግረዋቸዋል፡፡ ይህን ማድረግ ሲችሉ የወደቀው ጠላት በእነርሱ ላይ ሥልጣን አይኖረውም፡፡: EWAmh 99.1
ሰይጣን ሔዋን እንዳትታዘዝ በማድረግ ሥራውን ጀመረ፡፡ የእርሷ የመጀመሪያው ስህተት ከባሏ ተለይታ መቅበዝበዟ ነው፡፡ ሁለተኛው ስህተት በተከለከለው ዛፍ አካባቢ ቆይታ ማድረጓ ሲሆን በመቀጠል የፈታኙን ድምጽ መስማቷና «ከእርሱ በበላህ ቀን በእርግጥ ትሞታለህ” በማለት እግዚአብሔር የተናገረውን ለመጠራጠር መድፈሯ በዋነኝነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ሔዋን ጌታ የተናገረው ነገር በእርግጥም እርሱ እንዳለው አደጋ የለውም ብላ በማሰብ እጇን ወደ ፍሬው ሰድዳ በላች፡፡ ፍሬው ለዓይንም ሆነ ለመቅመስ የሚያስደስት ነበር ከዚያም በእርግጥም ለእነርሱ መልካም የሆነውን ነገር እግዚአብሔር መከልከሉ የቅናት መንፈስ ፈጠረባትና ባሏን በመፈተን ከፍሬው ሰጠችው፡፡ እባቡ ያላትን ነገሮች በሙሉ ለባሏ በመንገር በመናገር ችሎታው ምን ያህል እንደተደመመች ገለጸችለት፡፡ EWAmh 99.2
በአዳም ገጽታ ላይ ኃዘን ሲያጠላ ተመለከትኩ፡፡ የፍርሃትና የአግራሞት ሁናቴ ይታይበታል፡፡ በአእምሮው ውስጥ ትግል የሚካሄድ ይመስላል፡፡ ይህ በማንነቱ ዙሪያ ግንዛቤው ይኖራቸው ዘንድ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው የነበ ረው ጠላት ለመሆኑ የእርግጠኝነት ስሜት ተሰማው:፡፡ አሁን ሚስቱ መሞት ይኖርባታል፡፡ የሁለቱ መለያየት የግድ ነው፡፡ ነገር ግን አዳም ለሔዋን የነበ ረው ፍቅር ብርቱ ነበር፡፡ እናም ፍጹም በሆነ ተስፋ መቁረጥ የእርሷን ዕጣ ፈንታ ለመካፈል ቁርጥ ሃሳቡ አደረገ፡፡ ፍሬውን በእጁ ያዝ አደረገና በፍጥነት በላው፡፡ ከዚያም ሰይጣን ከበረ፡፡ በሰማይ አመጻ አድርጎ የነበረው ሰይጣን እርሱን የሚወዱትና በአመጻው የሚከተሉት ደጋፊዎች አገኘ:: እርሱ ውድቀት ከደረሰበት በኋላ ሌሎችም የእርሱን ውድቀት እንዲጋሩ መንስዔ የሆነው ሰይጣን አሁን ደግሞ ሲቲቱ የእግዚአብሔርን ጥበብ እንድትፈታተንና አምላካዊውን እቅድ እንድትመራመር በማድረግ ፈተናት፡፡ ሴቲቱ ብቻዋን እንደማትወድቅ ሰይጣን ያውቅ ነበር በመሆኑም አዳም ለሔ ዋን በነበረው ፍቅር የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጣስ ከእርሷ ጋር አብሮ ወደቀ፡፡ የሰው መውደቅ በሰማይ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ ተሰራጨእያንዳንዱ የበገና ድምጽ እረጭ አለ፡፡ መላእክት በሐዘን ዘውዳቸውን ከአናቶቻቸው ላይ እያነሱ ጣሉ፡፡ ሰማይ በተመሰቃቀለ ሁናቴ ውስጥ ወደቀ:: ጥፋተኞች ሆነው በተገኙት ጥንዶች ላይ ለመወሰን ጉባዔ ተጠራ፡፡ አዳምና ሔዋን በድጋሚ እጃቸውን ሰድደው ከህይወት ዛፍ ፍሬ በመብላት የማይሞቱ ኃጢአተኞች እንዳይሆኑ መላእክት ፍርሃት አደረባቸው:: ሆኖም እግዚአብሔር ሕግ ተላላፊዎችን ከኤደን ገነት እንደሚያባርራቸው ተናገረ፡፡ ወዲያውኑ መላእክት ወደ ህይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ እንዲዘጉ ታዘዙ፡፡ አዳምና ሔዋን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ የቁጣ ፊቱን እንዲቀበሉ በማድረግ ዳግመኛ ከህይወት ዛፍ በልተው ኃጢአትና አለመታዘዝ ለዘላለም እንዲኖር እነርሱም የማይሞቱ ኃጢአተኞች ሆነው በህያውነት እንዲቀጥሉ ማድረግ የሰይጣን የተጠና ዕቅድ ነበር: ነገር ግን ቅዱሳን መላእክት ከገነት እንዲያስወጧቸውና ወደ ህይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ እንዲዘጉ ተላኩ፡፡ እነዚህ ኃያላን መላእክት እያንዳንዳቸው በቀኝ እጃቸው ነበልባላዊ ሠይፍ ይዘው ነበር፡፡ ከዚያም ሰይጣን ድል ሆነ፡፡ በእርሱ ውድቀት ሌሎች ሥቃይ እንዲቀበሉ አደረገ፡፡ በዚህም እነርሱ ከገነት እርሱ ደግሞ ከሰማይ ተባረረ፡፡ EWAmh 99.3