ቀደምት ጽሑፎች
32—መንፈሳዊ ስጦታዎች- የሰይጣን ውድቀት
ሰይጣን በአንድ ወቅት በሰማይ ከክርስቶስ ቀጥሉ ስፍራ የነበረው የተከበረ መልአክ ነበር፡፡ እንደ ሌሎች መላእክት ሁሉ በእርሱም ገጽታ ላይ ግሩም ደስታ ይነበብ ነበር፡፡ የግንባሩ ወጣ ማለትና ስፋት የአእምሮውን ምጥቀት ያሳይ ነበር፡፡ ፍጹም የሆነው ተክለ ሰውነቱ ግርማ ሞገስ የተላበሰ ነበር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር «ሰውን በመልካችን በአምሳላችን እንሥራ» ብሎ ልጁን በተናገረው ጊዜ ሰይጣን የሱስን ተመቀኘው:: ሰው በተፈጠረ ጊዜ እርሱ ከመማክርቱ መሃል አንዱ ለመሆን በመፈለጉና ይህ ደግሞ ሊሆን ባለመቻሉ በቅናት፣ በምቀኝነትና በጥላቻ ተሞላ፡፡ እርሱ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ በሰማይ ከፍ ያለውን ክብር ለመቀበል ተመኝቶ ነበር EWAmh 97.1
እስከዚህ ጊዜ ድረስ መላው ስማይ ለእግዚአብሔር መንግሥት በሥርዓት፣ በውህደትና በፍጽምና የሚገዛ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ሥርዓትና ፈቃድ ላይ ማመጽ ከፍተኛው ኃጢአት ነበር፡፡ መላው ሰማይ በከፍተኛ ብጥብጥና አለመረጋጋት ላይ የወደቀ መሰለ፡፡ መላእክት በቡድን፣ በቡድን የተከፋፈሉ በመሆናቸው እያንዳንዱ ቡድን ተጠሪና አዛዥ አለው፡፡ ለየሱስ የበላይ ሥልጣን ለመታዘዝ ፈቃደኛ ያልሆነውና እራሱን ከፍ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ምኞት ያደረበት ሰይጣን በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ በአግቦ መናገር ጀመረ፡፡ ከመላእክቶቹ አንዳንዶች የሰይጣንን አመጻ ሲደግፉ ሌሎቹ ግን ለልጁ ሥልጣን በመቆም ለእግዚአብሔር ክብርና ጥበብ አጥብቀው ታገሉ፡፡ ሰይጣንና ደጋፊዎቹ በእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ተሃድሶ ለማ ያደርጉ በነበረው ትግል በመላእክቱ ሃል ውዝግብ ነበር፡፡ እነርሱ ወደ ማይመረመረው አምላካዊ ጥበብ በመመልከት እግዚአብሔር የሱስን ከፍ ከፍ ያደረገበትን፣ ወሰን የሌለውን ገናናነትና ሥልጣን የሰጠበትን ምክንያት ለማወቅ ተመኙ፡፡ በዚህም በወልድ ሥልጣን ላይ አመጻ አደረጉ፡፡ እያንዳንዱ ጉዳይ ውሳኔ ያገኝ ዘንድ መላው የሰማይ ሰራዊት በአብ ፊት ይቅርቡ ዘንድ ጥሪ ተደረገላቸው፡፡ ሰይጣንና በዐመጻው EWAmh 97.2
የተቀላቀሉት መላእክ ከሰማይ እንዲባረሩ ውሳኔ ላይ የተደረሰው በዚህ ወቅት ነበር፡፡ ከዚያም በሰማይ ጦርነት ሆነ፡፡ መላእክት በጦርነቱ ተካፋይ በመሆን ሰይጣን የእግዚአብሔርን ልጅና ለእርሱ ታማኝ የሆኑትን ለመቆጣጠር ተመኘ፡፡ ነገር ግን መልካምና እውነተኞቹ መላእክት ድል በማድረጋቸው ሰይጣን ከተhታዮቹ ከሰማይ ተጠራርጎ ተባረረ EWAmh 98.1
ስይጣን ከአባሪዎቹ ጋር ሰማይ ከተዘጋበት በኋላ የነበረውን ንጽህናና ክብር ለዘላለም እንዳጣው በመ7ንዘብ ዳግመኛ ሰማይ ይመለስ ዘንድ በመመኘት ንስሐ ገባ፡፡ አግባብ የነበረውን የቀድሞውን ስፍራ ወይም ማንኛ ውንም ዓይነት ሊመደብበት የሚችል ኃላፊነትን ለመውሰድ ፈቃደኛ ነበር፡፡ ይህ ግን ሊሆን አይችልም፡፡ ሰማይ አደጋ ላይ መውደቅ የለበትም፡፡ ኃጢአት ከእርሱ በመመንጨቱና የአመጻ ዘር በእርሱ ዘንድ በመሆኑ እርሱ ቀድሞ በነበረበት ስፍራ ላይ ዳግመኛ እንዲቀመጥ ቢደረግ መላውን ሰማይ ሊያጠፋ ይችል ነበር፡፡ እርሱም ሆነ ተከታዮቹ ክፉኛ በማንባት ዳግመኛ በእግዚአብሔር በኩል ይቆሙ ዘንድ ልመናቸውን አቀረቡ፡፡ ነገር ግን ኃጢአታቸው፣ በጥላቻ መሞላታቸው፣ ክፋታቸውና ምቀኝነታቸው እግዚአብሔር ሊደመስሰው የሚችለው አልነበረም፡፡ በመሆኑም የመጨረሻውን ቅጣት ለመቀበል በዚያው ሁኔታቸው መቆየት ነበረባቸው፡፡ EWAmh 98.2
ሰይጣን ከዚህ በኋላ ዳግመኛ በእግዚአብሔር በኩል መቆም የሚችልበት አንዳችም መንገድ አለመኖሩን ሙሉ ለሙሉ ሲገነዘብ ለመጉዳት የማሰቡ ነገርና ጥላቻው መታየት ጀመረ፡፡ ሰይጣን ከራሱ መላእክት ጋር ምክክር በማድረግ ከእግዚአብሔር መንግሥት በተቃራኒ ለመሥራት እቅድ አወጣ፡፡ አዳምና ሔዋን ውብ በሆነው ኤደን ገነት እንዲኖሩ ሲደረጉ ሰይጣን እነርሱን የማጥፋት ሴራ ጠነሰሰ፡፡ እነዚህ ጥንዶች እግዚአብሔርን ቢታዘዙ ኖሮ ደስታቸውን ፈጽሞ ሊነፈጉ አይችሉም ነበር፡፡ እነርሱ እግዚአብሔርን ከመታዘዝ እስካላፈነገጡና ከእርሱ ጥበቃ እስካልወጡ ድረስ ሰይጣን ኃይሉን በእነርሱ ላይ መለማመድ አይችልም፡፡ በመሆኑም እነርሱን ወደ ኣለመታዘዝ በመምራት በሰይጣንና መላእክቶቹ ቀጥተኛ ተጽእኖ ስር አብልጠው እንዲወድቁ በማድረግ እግዚአብሔር ፊቱን በእነርሱ ላይ የሚያጠቁርበትን እቅድ መውጣት ነበረበት፡፡ ይህን እቅድ ገቢራዊ ማድረግ ይቻል ዘንድ ሰይጣን የሰዎች ተቆርቋሪ መስሎ ስውር ካባ ደርቦ ብቅ እንዲል ተወሰነ፡፡ በእግዚአብሔር እውነተኝነት ዙሪያ የራሱን ፈጠራ በማስቀመጥ ይህ አምላክ በተናገረው የሚኖር አይደለም የሚል ጥርጣሬ የሚፈጥር ነገር መናገር ነበ ረበት፡፡ በመቀጠል ይህ እንዴት መሆን ቻለ የተሰኘው አስተሳሰብ በአእምሮአቸው እንዲነሳሳ በማድረግ ሰይጣን እራሱ ጥፋተኛ ሆነ ወደተገኘ በት የማይመረመረው አምላካዊ እቅድ ውስጥ ጣልቃ እንዲገቡ መራቸው፡፡ EWAmh 98.3