ቀደምት ጽሑፎች

32/73

31—እግዚአብሔር ለሰዎች የሰጠው ስጦታ

የሰው ልጆች ይቀርታ አግኝተው በህይወት ይኖሩ ዘንድ እግዚአብሔር ልጁን በመስጠት ያሳየውን ታላቅ ፍቅርና እራስን ዝቅ ማድረግ እንድመለከት ተደርጌ ነበር፡፡ የኤደን ገነትን ውበት በቅርበት የመመልከት ዕድል የነበራቸውንና ከአንዷ በቀር በዚያ ከነበሩት ፍሬዎች ሁሉ እንዲበሉ የተፈቀደላቸውን አዳምና ሔዋንን ተመለከትኩ፡፡ ነገር ግን እባቢቱ ሔዋንን በመፈተኗና እርሷ ደግሞ ባሏን በመፈተኗ ሁለቱም ከተhለከለው ፍሬ በሉ፡፡ በዚህም የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጣሳቸው ኃጢአተኞች ሆኑ፡፡ ወሬው በመላው ሰማይ ተሰራጨ፧ እያንዳንዱም የበገና ድምፅ ጸጥ ኣለ፡፡ መላእክት ኣዘኑ--አዳምና ሔዋን ዳግመኛ እጃቸውን ሰድደው ከተከለከለው ፍሬ እንዳይበሉና የማይሞቱ ኃጢአተኞች እንዳይሆኑም ፈሩ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ሕግ ተላላፊዎችን ከኤደን ገነት እንደሚያስወጣቸው በመናገ ወደ ህይወት ዛፍ የሚወስደውን መንገድ ለመጠበቅና ዘላለማዊ ወደ ምታደርገው ወደ ፍሬዋ እንዳይደርሱ ለማድረግ ኪሩቤልንና በየአቅጣጫው የምትገለባበጥ ነበልባላዊ ሠይፍ በኤደን አኖረ:: EWAmh 94.2

ሰው መጥፋቱና እግዚአብሔር ፈጥሯት የነበረችው ዓለም በተኮነኑና ሟች በሆኑ ፍጡራን ልትሞላ መሆኗ፤ እንዲሁም ከሥቃይ፣ ከህመም እና ከሞት ማምለጫ መንገድ አለመኖሩን የተገነዘበውን ሰማይ በሃዘን ድባብ ሞላው፡፡ ሁሉም የአዳም ቤተሰቦች መሞት ነበረባቸው ከዚያም ተወዳጁን የሱስ ስመለከተው የርኅራኄና የሐዘንና ገጽታ አስተዋልከብት: ወዲያውኑ እየጨመረ ይሄድ ወደ ነበረው አብን ወደ ሸፈነው ብርሃን ሲቀርብ ተመለከትኩት፡፡ ከዚያም መልአኩ «ከአባቱ ጋር በቅርበት እየተነጋገረ ነው» አለኝ፡፡ የሱስ ከአባቱ ጋር እየተገናኘ በነበረበት ሰዓት የመላእክቱ ጭንቀት እየበረታ የሄደ ይመስል ነበር፡፡ ሦስት ጊዜ ያህል በአብ ባለ ግርማ ብርሃን ውስጥ ተዘግቶበት የነበረ ሲሆን በሦስተኛው የየሱስን አምሳል ማየት ችለን ነበር፡፡ በፊቱ ላይ ይታይ የነበረው ገጽታ በእጅጉ የተረጋጋና ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት ዓይነት ፍቅር የሚንጸባረቅበት ነበር፡፡ ከዚያም ለጠፋው ሰብዓዊ ፍጡር ማምለጫ መንገድ መዘጋጀቱን ለመላእክታዊው የመዘምራን ቡድን ይፋ አደረገ፡፡ እርሱ ኃጢአታቸውን ተሸክሞ የእነርሱን የሞትን ቅጣት በመቀበል ለመተላለፋቸው በደሙ ይቅርታን እንዲቀበሉና ዳግመኛ በመታዘዝ ከተባረሩበት ኤደን እንዲመለሱ ለማድረግ የገዛ ራሱን ህይወት ለጠፋው ዘር መስዋዕት አድርጎ ለመስጠት አብን ሲማጸን እንደነበርና ይህንኑ ያደርግ ዘንድ ፈቃድ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡ ይህ ሲሆን አሁን ወደ ህይወት ዛፍ ለመድረስ ያጡትን መብት ሙሉ ለሙሉ ዳግመኛ ያገኙታል፡፡ EWAmh 95.1

እግዚኣብሔር ለአመጸኛው ዘር ላደረገው ታላቅ ምኅረት ሰማይ ሊገለጽ በማይችል ደስታ ተሞላ፤ የሰማይ መዘምራን በገናዎቻቸውን በመንካት ከዚያ ቀደም ተሰምቶ የማያውቅ የምስጋናና የውዳሴ መዝሙር አሰሙ የሱስ ከአባቱ እቅፍ ወጥቶ ሥቃይና መከራ የበዛበትን ህይወት ለመኖር፣ የውርደት ሞት ለመሞትና እራሱን ክዶ መስዋዕት በመሆን ህይወቱን ለሌ ሎች ይሰጥ ዘንድ በመፍቀዱ ምስጋናና ውዳሴ ቀረበለት፡፡ EWAmh 95.2

መልአኩ እንዲህ አለ «አብ የተወደደውን ልጁን ያለ ምንም ትግል የሰጠ ይመስልሻል? በጭራሽ! ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘው ሰብዓዊ ፍጡር ይጥፋ ወይስ ለመተላለፋቸው ይሞትላቸው ዘንድ አብ የሚወደውን ልጁን ይስጥ? በሚለው ዙሪያ ብርቱ ትግል ነበር መላእክት ለሰው ልጅ ደኀንነት ከፍተኛ ፍላጎት በማሳየት የእነርሱ ክበርና ህይወት ለሚጠፋው የሰው ልጅ ደኅንነት ማምጣት የሚችል ከሆነ ከመካከላቸው ይህን ለማድረግ ፈቃደኞች የሆኑ ነበሩ: ሆኖም የእነርሱ መስዋዕትን የሚፈይደው አንዳችም ነገር አይኖርም:፡፡» የሰብዓዊው ፍጡር መተላለፍ እጅግ ግዙፍ ስለነበር የመላእክ ህይወት ዕዳውን መክፈል አይችልም ከእግዚአብሔር ልጅ ሞትና ምልጃ በቀር የጠፋውን ሰው ተስፋ ከመቁረጥ፣ ከንና ሥቃይ በማዳን ዕዳውን መክፈል የሚል የለም:: EWAmh 95.3

ነገር ግን ለመላእክት የተመደበላቸው የሥራ ድርሻ የነበረ ሲሆን ይኸውም የእግዚአብሔር ልጅ በምድር ላይ ለሚኖረው ሥቃይ የተሞላው ህይወት እርሱን ማበረታታትና ማጽናት እንዲሁም ከማንኛውም የክፉ መላእክትና ያለማቋረጥ በሰይጣን ከሚሰነዘር ጽልመት መጠበቅ ነበር፡፡ የጠፉትን ለማዳን ሐጉን መለወጥ ለእግዚአብሔር የማይቻል መሆኑን ተመለከትኩ፡፡ በዚህ የተነሳ ለሰብዓዊው ፍጡር መተላለፍ ተወዳጁ ልጁ ይስቃይ ዘንድ ፈቀደ:: EWAmh 96.1