ቀደምት ጽሑፎች
30—ሐሰተኛ እረኞች
ሐሰተኛ እረኞች ሰክረው ሲንገዳገዱ ተመልክቼ ነበር፡፡ ነገር ግን እረኞቹ የሰከሩት ወይን ጠጅ ጠጥተው አልነበረም፡፡ የእግዚአብሔር እውነት በእነርሱ ላይ ቢታተምም ሊያነቡት ግን አይችሉም፡፡: ሰባተኛው ቀን እውነተኛው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሰንበት ነው ወይስ አይደለም? ተብለው ሲጠየቁ አእምሮ ወደ ተረት እንዲያፈነግጥ ያደርጋሉ፡፡ እነዚህ ነቢያት የነበሩትን ክፍተቶች ለመሙላት አልተንቀሳቀሱም---የእግዚአብሔር ሕዝቦች ለጌታ ቀን በውጊያ ይቆሙ ዘንድ አላዘጋጅዋቸውም: ሰዎች አእምሮአቸው ተነሳስቶ እነዚህን የሐሰት አረኞች ስለ እውነት መጠየቅ ሲጀምሩ የጠያቂዎቻቸውን አእምሮ ጸጥ ለማድረግ ቀለል ያሉና ወደር የማይገኝላቸውን ዘዴዎች ተጠቅመው አቋማቸውን እንኳ እስከ መለወጥ ይደርሳሉ፡፡ በአብዛኞቹ በእነዚህ እረኞች ላይ ብርሃን ፈንጥቆ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን አይቀበሉትም፡፡ እረኞቹ በቀድሞው አቋማቸው ድምዳሜ ሊደርሱ ይችሉ ቢቀጥሉ ይህን እውነት ሊቀበሉ ወደሚችሉበት ነበር: ሆኖም ይህ እንዳይሆን አቋማቸውን ብዙ ጊዜ ቀያይረዋል፡፡ የእውነት ኃይል የቆሙበትን መሰረት ቢገለባብጠውም እነርሱ ግን ልባቸውን በማለሳለስ ፋንታ ሌላ መድረክ ይሻሉ፡፡ EWAmh 92.2
ከእነዚህ እረኞች ውስጥ አብዛኞቹ የቀድሞዎቹን አምላካዊ አስተምህሮ ዎች መካዳቸውን ተመልክቻለሁ፡፡ በአንድ ወቅት በጋለ ስሜት ተነሳስተው ድጋፋቸውን ሲሰጡ የነበሩ--የከበሩትን እውነቶች በመካድ በሁሉም ዓይነት የተሳሳቱ ትምህርቶች ውስጥ ገብተዋል፡፡ እረኞቹ በተሳሳተአስተምህሮ ስክ ረው እንደነበርና መንጋዎቻቸውን ወደ ሞት እየመሩ እንደነበር ተመለክቻ ለሁ:፡፡ አብዛኞቹ የእግዚአብሔር እውነት ተቃዋሚዎች በመኝታቸው ላይ ሆነው ጉዳትና ጥፋት ሲያውጠነጥኑ ካደሩ በኋላ ሲነጋ ይህንኑ እኩይ እቅዳቸውን ተግባራዊ ማድረግ ይችሉ ዘንድ የሕዝቡን አትኩሮት ከhበረውና አስፈላጊ ከሆነው እውነት ላይ ለማስቀየስ የሚረዳቸውን አዲስ ነገር ይዘው ይመጣሉ፡፡ EWAmh 93.1
መንጋዎቻቸውን ወደ ሞት እየመሩ ያሉ ቀሳውስት በቅርቡ በራሳቸው አስፈሪ ሙያ እንደሚታሰሩ ተመልክቼ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር መቅሰፍቶች እየመጡ ቢሆንም ነገር ግን የሐሰት እረኞች በእነዚህ አንድ ወይም ሁለት መቅሰፍቶች መሰቃየታቸው በቂ አይሆንም፡፡ በዚያን ጊዜ በቁጣና በፍትሕ የሚዘረጋው የእግዚአብሔር እጅ የታለመውን ተግባር ሙሉ ለሙሉ ሳያከናውን ዳግመኛ ወደራሱ አይመለስም፡፡ እነዚያ በደሞዝ የሚያገለግሉ ቀሳውስት በቅዱሳኑ እግር ስር በመውደቅ ቅዱሳኑ እውነትን አጥብቀው በመያዛቸውና የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጠበቃቸው እግዚአብሔር የወደዳቸው መሆኑን አምነው ይቀበላሉ፡፡ EWAmh 93.2
በተለያዩ ቡድኖች የተከፋፈሉት አድቬንቲስት አማኞች እያንዳንዳቸው አነስተኛ መጠን ያላቸውን እውነቶች የያዙ ሲሆን ነገር ግን እግዚአብሔር እነዚህን ሁሉ እውነቶች የሰጠው ለጌታ ቀን እየተዘጋጁ ላሉት ልጆቹ ነው፡፡ ከእነዚህ ቡድኖች ውስጥ አንዳቸውም የማያውቁትን ወይም ሊያስተውሉት የማይችሉትን እውነትዝግጅት እያደረጉ ላሉት ልጆቹ ሰጥቶአል ለእነርሱ የታተሙ የሆኑባቸውን ነገሮች---ጌታ ግን እርሱን ለሚያዩና ሊያስተውሏቸው ዝግጁ ለሆኑት አበርክቶአል፡፡ እግዚአብሔር ሊነገግራቸው የሚፈልገው አንዳች አዲስ ብርሃን ቢኖረው እነዚያ በእርሱ የተመረጡትና የተወደዱት ያስተውሏቸው ዘንድ ይፈቅዳል፡፡ EWAmh 93.3
በየቀኑ አዳዲስ ስህተቶችን ከሚጎነጩት በተለየ የመጨረሻው የምህረት መልእክት እንዳለን የሚያምኑትን እንድመለከት ተደርጌ ነበር፡፡ ወጣቱም ሆነ አዛውንቱ የእነርሱን ስብሰባ መካፈል እንደሌለበት ተመልክቻለሁ፡፡: ምክንያቱም በጉባዔዎቻቸው መኘት ማለት ነፍስ ገዳይ የሆነውን መርዛቸውንና የሰ ዎችን ትእዛዝ ጠብቁ የማለውን አስተምህሮአቸውን ማበረታታት ነው:፡፡ የእንደነዚህ ዓይነቶቹ ስብሰባዎች ተጽእኖ መልካም አይደለም፡፡ እግዚአብሔር hእንዲህ ዓይነቱ ጽልመትና ስህተት ካዳነን እርሱ በተቀዳጀነው ነጻነትና እውነት ሐሴት እያደረግን በጽናት ልንቆም ይገባል፡፡ እግዚአብሔር እራሱ ካልላከን በቀር በፈቃዳችን የተሳሳተውን ትምህርት ለመስማት ስንሄድ አይደሰትብንም፡፡ መላእክት በእኛ ላይ ጥበቃ ማድረጋቸውን በማቆም ለጠላት እንግልት እንተዋለን፡፡ በሰይጣንና በክፉ መላእክቱ አማካኝነት ብርሃናችን እንዲደበዝዝና ደካሞች እንድንሆን እንደረጋለን፡፡ EWAmh 93.4
ተረት የምንሰማበት ጊዜ እንደሌለን ተመልክቻለሁ፡፡ አእምሮዎቻችን ተጨባጭ ካልሆኑት ነገሮች በመራቅ በወቅታዊው እውነት ሊሞሉና ጥበብን ሊሹ ይገባል፡፡ ትህትና በተሞላው ማንነት ተስፋ ስላደረግነው ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ማስረዳት እንችል ዘንድ ስለ አቋማችን ጥንቃቄ የተሞላው ዕውቀት ማግኘታችን አስፈላጊ ነው፡፡ የተሳሳቱ አስተምህሮዎችና አደገኛ ስህተቶች ተጽእኖአቸውን በአእምሮ ላይ ሊያሳርፉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የእስራኤልን ቤት ለጌታ ቀን ብቁ ከሚያደርገውና ከሚያዘጋጀው እውነት ጋር አብረው መኖር ግን አይችሉም:: EWAmh 94.1