ቀደምት ጽሑፎች

30/73

29— የእግዚአብሔርን ስም አለማክበር

ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔር ስም ፍርሃት አዘል በሆነ አብሮት ልንጠቀመው እንደሚገባ ተመልክቻለሁ:: እግዚአብሔር ኃያል የተሰኙት ብርቱ ቃላት በአንድ ላይ ተጣምረው በጸሎት ወቅት በግዴለሽነትና በዘፈቀደ ሲጠሩ እርሱን ያሳዝነዋል፡፡: እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ስለ እግዚአብሔር ማንነትም ሆነ ስለ እውነት ባለማስተዋላቸው እንጂ አስፈሪ የሆነውንና በመጨረሻው ቀን የሚዳኛቸውን አምላክ እንዲህ አላግባብ አያነሱትም ነገር፡፡ መልአኩ እንዲህ አለ «ስሙ አስፈሪ እንደመሆኑ ቃላቱን በአንድ ላይ አታጣምሯቸው:፡፡» የእግዚአብሔርን ታላቅነትና ባለግርማነት የሚገነዘቡ ስሙን የሚጠሩት ፍርሃት አዘል በሆነ አክብሮት ነው፡፡ ማንም ሊደርስበት በማይችለው ብርሃን ውስጥ የሚኖረውን ይህን አምላክ አይቶ በህይወት የሚኖር የለም:፡፡ ቤተክርስቲያን ከመበልጸጓ አስቀድሞ እነዚህ ነገሮች ሊስተዋሉና ሊታሙ እንደሚገባ ተመልክቻለሁ:: EWAmh 92.1