ቀደምት ጽሑፎች

29/73

28—እራስን መካድ

ቅዱሳን ጉባዔዎችን ለማካሄድ ከመጠን ያለፈ ዝግጅት ማድረጋቸውን ተከትሎ ያለውን አደጋ ተመልክቼ ነበር፡፡ አንዳንዶች ከመጠን ባለፈ መስተንግዶ ተሰናክለው ነበር፡፡ . . . ሰዎች ለዳቦና ዓሣ ብለው በስብሰባ ዎች መገኘታቸው አደጋ አለው፡፡ በትንባሆ ሱስ የተጠመዱ ሁሉ ከእንዲህ ያለው ተግባራቸው በመታቀብ ለዚህ ተግባር ያባክኑ የነበረውን ወጪ በተሻለ ነገር ላይ ሊያውሉት እንደሚገባ ተመልክቻለሁ፡፡ እራሳቸውን ከአምላካዊው ደስታና እርካታ ገድበው የነበሩ አሁን ግን አምላካዊን ደስታና እርካታ ለማግኘት በማዋል ለአጉል ልምድ ያወጡት የነበረውን ወጪ ወደ ጌታ ግምጃ ቤት ሊያስቀምጡ ይገባል፡፡ ይህ ሲሆን ስጦታው እንደዚያች መበለት ሁለት ሣንቲም በእግዚኣብሔር ዘንድ ትኩረት ያገኛል፡፡ ለስጦታ የሚቀርበው ይህ ገንዘብ አነስተኛ ሊሆን ቢችልም ነገር ግን ሁሉም ይህን ቢያደርጉ የተሻለ መጠን ያለው ገንዘብ ለእግዚአብሔር ሥራ ይውላል፡፡ ሁሉም በአለባበሳቸው ዙሪያ ያልተንዛዛ ወጪ ማድረግ እንዳለባቸውቢገነዘቡ፣ ጎጂነት ላላቸው እንደ ሻይና ቡና ለመሳሰሉት የሚወጡ ወጪዎችን ለሥራው ማስኬጃ ቢያውሉት በምድር አብልጠው በረከትን ይቀበላሉ በሰማይ የተዘጋጀላቸውንም ሽልማት ይወስዳሉ፡፡ ብዙዎች እግዚአብሔር ሁናቴዎችን ስላመቻቸላቸው ብቻ መኖር ካለባቸው በላይ ይኖራሉ፣ እጅግ ውድ ምግቦችን ይመገባሉ እንዲሁም ለተቀናጣ አለባበስ አላስፈላጊ ወጪ ያወጣሉ፡፡ በእንዲህ ያለው አኗኗራቸው እራስን የመካድ ምግባር ሊኖራቸው አይችልም፡፡ በመሆኑም ምንም ዓይነት መስዋዕት አይከፍሉም፡፡ ነገር ግን ኑሮአቸውን አሁን ካሉበት መለስተኛ በማድረግ አላስፈላጊ ወጪያቸውን እውነትን ወደ ፊት ለማራመድ ቢያውሉት ኖሮ መስዋዕት እንደከፈሉ ይቆጠርላቸው ነበር፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሁሉም እንደየ ሥራው በሚከፍልበት በያን ጊዜ በእርሱ ዘንድ የሚታወሱ ይሆናሉ፡፡: EWAmh 91.1