የአድቬንቲስት ቤት

77/88

ምዕራፍ ሰባ ስድስት—የዕረፍት ጊዜያትና ክብረ-በዓላት

የመምራት አስፈላጊነት በበዓል አጠባበቅ ጊዜ፡- በዓሎቻችን ዓለም እንደሚያደርገው እያደረግን ልናሳልፋቸው እንደማይገባ አይቻለሁ። ሆኖም ሳናስታውሳቸው ማለፍ የለባቸውም፤ ምክንያቱም ይህ ድርጊት ልጆቻችንን ላያስደስት ይችላልና። በእነዚህ ቀናት ልጆቻቸው ለክፉ ተጽዕኖ የመጋለጥ አደጋ የሚገጥማቸው ከሆነና የዓለም ደስታና ፌሽታ የሚያበላሻቸው ከሆነ፣ ወላጆች በማጥናት አደገኛ መዝናኛዎችን የሚተኩ ነገሮች ለልጆቻቸው ሊያዘጋጁ ይገባቸዋል። የእነርሱ ፍላጎትና ደስታ በዕይታችሁ ውስጥ እንዳለ እንዲገነዘቡ አድርጓቸው።1 AHAmh 346.1

በበዓላት አከባበር ረገድ በቤተ-ክርስቲያንም ሆነ በዓለም ያሉ ሰዎች የተማሩት እነዚህ የስንፍና ቀናት ለጤንነትና ለደስታ አስፈላጊ እንደሆኑ ነው፤ ነገር ግን ውጤታቸው የሚያሳየው በክፋት የተሞሉ መሆናቸውን ነው።2 AHAmh 346.2

ይህ አስተሳሰብ እንዲቀየር እየጣርን ሳለ ለልጆችና ለወጣቶች እነዚህ በዓላት በተቻለ መጠን አስደሳች እንዲሆኑላቸው ጥረት እያደረግን መሆን አለበት። ዓላማችን ከማያምኑ ሰዎች የመዝናኛ ትዕይንቶች እነርሱን ማራቅ ነው።3 AHAmh 346.3

“የባከነ ቀን” ብሎ መልአክ ይመዝግበው?፡- ደስታን ለማግኘት ሲባክን ቀኑ ካለቀ በኋላ የደስታ ፈላጊው እርካታ የት አለ? እንደ ክርስቲያን ሠራተኝነታቸው ወደ ተሻለ ከፍ ከፍ ወዳለና ወደ ነፃ ሕይወት ይመጡ ዘንድ ማንን ረዱ? መልአኩ የጻፈውን ማየት ቢችሉ ምን ያነብባሉ? የባከነ ቀን! ለራሳቸው ነፍስ የባከነ ቀን፤ ለክርስቶስ አገልግሎት ሳይውል የጠፋ ቀን! ምክንያቱም ምንም መልካም ነገር አልተከናወነበትም። ሌሎች ቀናት ይኖሯቸው ይሆናል፤ ልጃገረዶች ከወጣት ወንዶች፣ ወጣት ወንዶች ደግሞ ከልጃገረዶች ጋር በስንፍና፣ በርካሽና በሞኝነት ወሬ ያሳለፉትን ያን ቀን ግን ፈጽሞ እንደገና አያገኙትም። AHAmh 346.4

እነዚህ ዕድሎች እንደገና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈጽመው አይገኙም። በዚያ የዕረፍት ቀን ከሁሉም ጊዜ የከበደውን ሥራ ቢሠሩ ይሻላቸው ነበር። የዕረፍታቸውን ቀን በትክክል ሳይጠቀሙበት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለዘለዓለም አለፈ፤ በፍርድ ቀንም ያለአግባብ የባከነ ቀን ተብሎ ተመዝግቦ በፊታቸው ያገኙታል።4 AHAmh 346.5

የልደት ቀናት- እግዚአብሔርን የማመስገኛ ጊዜያት፡- ጌታ እራሱ ባዘዘው መሠረት በአይሁድ ሥርዓተ-አስተዳደር ልጆች ሲወለዱ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ይቀርብ ነበር። በዛሬው ጊዜ ወላጆች በልጆቻቸው የልደት ቀን ሥጦታ ለማበርከት የተለየ ጭንቀት ውስጥ ይገባሉ። ለፍጡር ሰው ክብር የሚገባው ይመስል ለልጆቻቸው ክብር የሚሠጡበት እድል አድርገው ይቆጥሩታል። ሰይጣን እነዚህን ነገሮች እንደፈለገው ማድረግ ተሳክቶለታል። ሐሳብና ሥጦታ ለፍጡራን ብቻ ይሆን ዘንድ ነገሮችን በማጣመም የተለየ ሞገስ የሚገባቸው በማስመሰል የልጆች ሀሳብ በዚያ ቀን ሥለራሳቸው ብቻ እንዲሆን ያደርጋል…. AHAmh 346.6

በልደት በዓላቸው ቀን ከአፍቃሪ ቸርነቱ የተነሣ ሕይወታቸውን ለሌላ ዓመት ጠብቆታልና እግዚአብሔርን ለማመሥገን ምክንያት እንደሚሆንላቸው ልጆች መማር ይገባቸዋል። ይህ ድርጊት ወርቃማ ትምህርት የሚለግሳቸው ነው። ለሕይወታችን፣ ለጤናችን፣ ለምግባችን፣ ለልብሳችን እንዲሁም ባልተናነሰ መልኩ ለዘለዓለማዊ ሕይወት ተስፋችን ሁሉንም ምህረት ለሚያደርግልን ለጋሽ አምላክ ባለዕዳዎች ነን። ወደር ለሌለው መጋቢያችን የምሥጋና መሥዋዕት እናቀርብ ዘንድ፣ ለሥጦታዎቹ ሁሉ እውቅና እንሰጥ ዘንድ እግዚአብሔር በእውነት የተገባው ነው። እነዚህ የልደት ቀን ሥጦታዎች በሰማይ እውቅና የሚሰጣቸው ናቸው።5 AHAmh 347.1

የዓመቱን መዝገብ የመከለሻ ጊዜ፡- ሕይወታቸውን እንዲመረመሩና በሰማይ ያለውን ያለፈውን ዓመት መዝገባቸውን ምንም ሳይቀየር ባለበት ቢያነብቡት ደስ ሊሰኙበት የሚችሉበት መሆን ለመሆኑን እንዲያስቡበት ምከሯቸው። ጠቃሚ አስተሳሰቦችን በውስጣቸው አበራቱ፤ ጠባያቸው፣ ንግግራቸው ወይም ሥራቸው እግዚአብሔርን የማስደሰት ባሕርይ ያለው እንደሆነ እንዲያጤኑ እርዷቸው። ሕይወታቸው የበለጠ ክርስቶስን መሰል ይሆን ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ያማረ ይሆን ዘንድ እያስተካከሉት ነው? የጌታን መንገድ ዕውቀትና መመ ሪያዎች አስተምሯቸው።6 AHAmh 347.2

የእግዚአብሔርን ሥራ ማስቀደም፦ ለቤተሰቦቼና ለጓደኞቼ፡- #ሚስዮናዊ አገልግሎቶችን ለማቋቋም ይውል ዘንድ ወደ ጌታዬ ጎተራ እንዳስገባው ፈቃዳቸውን ካልጨመሩበት በስተቀር በማናቸውም የልደት ቀን ወይም በገና ሰሞን ሥጦታ እንዳያበረክቱልኝ ነግሬአቸዋለሁ።;7 AHAmh 347.3

የምሥጋና ማቅረቢያ ጊዜን (Thanks Giving) እንዴት እናክብረው፦ ምሥጋና የማቅረቢያ ጊዜያችን እየተቃረበ ነው። ሁልጊዜ አንደሚሆነው ለራሳችን የሚደረግ ምሥጋና ይሆን? ወይስ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ምሥጋና ነው? ምሥጋና የምናቀርብባቸው ጊዜያት በመካከላችን ያሉትን ድኆች ለማሰብ የተሰጠን ዕድል እንደሆነ ብናስብና ካለፈው ጊዜ በተሻለ ብናስተውላቸው ለራሳችንና ለሌሎች ነፍሳት የታላቅ ትርፍ ወቅት ሊሆኑልን ይችላሉ…. AHAmh 347.4

ርኅራኄአችንንና ሥጦታዎቻችንን እሺ ብለው በመቀበላቸው ለእኛ መልካም እያደረጉልን እንደሆነ እንዲሰማቸው በሚያደርግ በለሰለሰ አቀራረብ ድኆችን የምንረዳባቸው መቶ የተለያዩ መንገዶችን መቀየስ እንችላለን። መስጠት ከመቀበል ይልቅ መባረክ እንደሆነ አንርሳ። ሊያከብሩአቸው የሚፈልጉአቸውን በአፀፋውም እራሳቸውን እንዲያከብሩአቸው ለሚወድዱ ነገር ግን እርዳታቸው በፍጹም ለማያስፈልጋቸው ሰዎች ወንድሞቻችን ትኩረት በገፍ ይሰጣሉ። ፋሽንና ባህል ‘ለሚሰጡአችሁ ስጡ’ ይላል ነገር ግን ይህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የአሰጣጥ ደንብ አይደለም። ለራሳችን ጥቅምና እርካታ ሲባል የሚለገስን ሥጦታ የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ይቃወማል “ለባለጠጋም የሚሰጥ ብቻ ያጎድልበታል [ወደ ድህነት ይወድቃል]።” AHAmh 347.5

መመሪያዎቻችን የሚፈተኑበት ወቅት አሁን እየመጣ ነው። ለእግዚአብሔር ምስኪኖች ማድረግ የምንችለውን ብናስብ መልካም ነው። በእኛ ምክንያት የእግዚአብሔር በረከት ተቀባዮች ልናደርጋቸው እንችላለን። የትኛዋን መበለት፣ የትኛውን ወላጅ-አልባ፣ የትኛውን ድኃ ቤተሰብ እንደምትረዱ አስቡ። የምትረዷቸው በጉዳዩ ላይ አጀብ በመፍጠር ወይም የምታደርጉትን ሰዎች እንዲያዩላችሁ በማሰብ አይሁን፤ #የጌታ በረከት ወደ እራሱ ድኆች የሚፈስበት ቱቦ; በመሆን እንጂ…. AHAmh 348.1

ሆኖም ይህን መሥራታችሁ ያለባችሁን ኃላፊነት ሁሉ አይጠቀልለውም። ወደር ለሌለው ጓደኛችሁ [ለጌታ] ገፀ-በረከት አቅርቡ፤ ለልግስናዎቹ ሁሉ ዕውቅና ስጡ፤ በፊቱ ላገኛችሁት ሞገስ አመስግኑት…. ወንድሞችና እህቶች ሆይ በምሥጋና ቀን ቀለል ያለ እራት ብሉ፤ የሆዳችሁን ፍላጎት ለመሙላት ለተለያየ ምግቦች የምታወጡትን ተጨማሪ ገንዘብ ለእግዚአብሔር የም ሥጋና በረከት አድርጉት። 8 AHAmh 348.2

ለመደሰት ሆዳችንን ለመሙላትና ራሳችንን ለማስከበር የሚደረጉ ከሆነ ከአሁን በኋላ የምሥጋና ቀናት መከበራቸው ይቅር። እግዚአብሔር ሕይወታችን ለሌላ ዓመት ጠብቆ አቆይቶታልና ወደ ጌታ ዙፋን ለመቅረብ ምክንያት አለን… ግብዣ የሚደረግም ከሆነ ለተቸገሩት ይሁን።9 AHAmh 348.3

ምሥጋና ሊሰጥበት የሚገባ ቀን*፡- ልናመሠግንበት የሚገባን አንድ ነገር እንዳለን አስባለሁ። ብዙ ምህረቶችን ስላደረገልን ልንደሰትና ሐሴት ልናደርግ ይገባናል… ይህ የምሥጋና ቀን የሚወክለውን ሁሉ እንዲሆን ፍላጎታችን ነው። ከቆሻሻ ጋር ቀላቅላችሁ የተበላሸ አታድርጉት። ስሙ የሚለው ይሁን - ምሥጋና መስጠት። ድምፆቻችን በምሥጋና ወደ ላይ ይውጡ። 10 AHAmh 348.4

እነዚህ የበዓል ቀናት ለእግዚአብሔር ለምን አይሆኑም?፦ እንክብካቤውን ሁሉ እያስታወስን አዕምሮአችንን ብናነቃቃ በዓላትን ለእግዚአብሔር ብናደርጋቸውና ብናከብራቸው ለእኛ መልካም አይሆንልንም? ያለፉትን በረከቶቹን ብናሰላስል እግዚአብሔርን እንዳንረሳም ወደ ነፍሳችን የመጡትን ግሩም ማስጠንቀቂያዎች ብናስታውስ መልካም አይደለምን? AHAmh 348.5

*ማስታወሻ፡- ይህ በBattle Creek Tabernacle በሕዳር 27, 1884 ከተሰጠው ስብከት በከፊል የተወሰደ ነው፡፡ ዓለም ብዙ በዓላት አሉት፤ ሰዎች በግጥሚያ በፈረስ ግልቢያ፣ በቁማር፣ ሲጋራ በማጨስና በስካር ተይዘው ያሳልፏቸዋል…. AHAmh 348.6

ለለጋስ በረከቶቹ እግዚአብሔርን ያመሠግኑት ዘንድ የአምላክ ሕዝቦች በየጊዜው ቅዱስ ስብስባ አያስፈልጋቸውም?11 AHAmh 349.1

በዓላት ሚሊዮናዊ አገልግሎት ለመስጠት ዕድል ይከፍታሉ፦ ወጣት ሴቶችንና ወንዶችን በማስተባበር የሰው ዘርን ችግር በማቃለልና የወንዶች የሴቶች የወጣቶችና የልጆች ነፍስ ይድን ዘንድ እንዲሠሩ ተግባራዊ ሥልጠና የሚሰጡ ሰዎች በቤተ-ክርስቲያን ያስፈልጉናል። ለዕለት ጉርሳቸው መሥራት ስላለባቸው ሙሉ ጊዜያቸውን ለዚህ ሥራ ማዋል ለሁሉም ሰው የሚቻል አይደለም። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ለጌታ ሥራ የሚውል ብዙ ገንዘብ መስጠት ባይችሉም የበዓል ቀናት አሏቸው። መልካምና ክርስቲያናዊ ተግባር ላይ በመሳተፍ ያሳልፏቸው።12 AHAmh 349.2

የበዓል ቀን ሲኖራችሁ ለልጆቻችሁ አስደሳችና ማራኪ አድርጉት። ለተጎዱና ለተቸገሩትም እንዲሁ የሚያስደስት ቀን አድርጉት። ምስጋናና የምስጋና ሥጦታ ለየሱስ ሳታመጡ ቀኑ አይለፍ።13 AHAmh 349.3