የተሟላ ኑሮ
3—ያስደሳች ትዳር ምስጢር
ረዳት እንድትሆነው ሔዋንን ለአዳም የሰጠው አምላክ የመጀመሪያውን ታምሩን በሠርግ ግብዣ ላይ ፈጸመ፡፡ ክርስቶስ ወዳጆችና ቤተ ዘመዶች በሚደሰቱበት የግብዣ አዳራሽ ውስጥ የሕዝብ አገልግሎቱን ጀመረ፡፡ እሱ ራሱ ያቋቋመው ሥርዓት መሆኑን በማስታወስ ጋብቻን ቀደሰ፡፡ ወንድና ሴት በተቀደሰ ጋብቻ እንዲዋሃዱና ቤተሰብ እንዲያቋቁሙ፤ የቤተሰቡም አባሎች የላይኛው (የሰማይ) ቤተሰብ አባሎች እንዲሆኑ ወሰነ፡፡ CLAmh 12.3
ክርስቶስ ሠርግን በእርሱና በጻድቃን መካከል ላለው ግንኙነት ምሳሌ በማድረግ አክብሮታል፡፡ እርሱ ሙሽራው ሲሆን ቤተክርስቲያንዋ ሙሽራይቱ ናት፤ ስለ ሙሽራይቱም “ወዳጄ ሆይ ሁለንተናሽ ውብ ነው፤ ነውርም የለብሽም” ይላል፡፡ መኃልይ 4፡7 CLAmh 12.4
“ክርስቶስ ዳግም ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት… ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ ወይም እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለነውር ትሆን ዘንድ… እንዲሁም ባሎች ደግሞ እንደገዛ ሥጋቸው አድርገው የገዛ ሚስቶቻቸውን ሊወዱአቸው ይገባቸዋል፡፡” ኤፌ 5፡25-28 CLAmh 12.5
የቤተሰብ ኅብረት በዓለም ከሚገኘው ከማንኛውም ዓይነት ኅብረት የበለጠ የጠበቀና የተቀደሰ ነው፡፡ ለሰብአዊ ፍጥረት ሁሉ በረከት ይሆን ዘንድ ተቋቋመ፡፡ የሚያስከትለውን ኃላፊነት በመገንዘብ፤ በፈሪሃ እግዚአብሔር አስተውሎ ከገቡበት እውነትም ትዳር ትልቅ በረከት ነው፡፡ CLAmh 13.1
ለመጋባት የሚመኙ ሁሉ የሚያቋቁሙት ትዳር ምን ዓይነት እንደሚሆን አጥብቀው ማሰብ ይገባቸዋል፡፡ ልጅ በሚወልዱበት ጊዜ የተቀደሰ ኃላፊነት ይጣልባቸዋል፡፡ የልጆቻቸው በዚህ ዓለም ክንውን ማግኘትና በሚመጣውም ዓለም መደሰት አብዛኛውን ጊዜ የሚወሰነው በነሱ ነው፡፡ የኅብረተሰብ ሁናቴ የሚወሰነው በቤተሰብ ስለሆነ እያንዳንዱም ቤተሰብ የኅብረተሰቡን ክንውንነት ወይም ውድቀት የሚወስነውን ሚዛን ወደ አንድ በኩል እንዲያጋድል ያደርጋል፡፡ CLAmh 13.2