የተሟላ ኑሮ

9/201

የሕይወት ጓደኛ አመራረጥ

የሕይወት ጓደኛ በሚመረጥበት ጊዜ ለወላጆችም ሆነ ለልጆች የአካል፣ የአዕምሮና የመንፈስ ጥንካሬን የሚያመጣ መሆኑ ወይም አለመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል፤ ይህም ማለት ወላጆችንና ልጆችን ለሰው ዘር ሁሉ በረከት ለእግዚአብሄርም ክብር እንዲሆኑ የሚያስችል መሆን አለበት፡፡ CLAmh 13.3

የጋብቻን ኃላፊነት ከመጋፈጣቸው በፊት ወጣቶች ለትዳር ተግባሮችና ችግሮች የሚያዘጋጃቸው የሕይወት ልምድ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በዕድሜ ያልበሰሉ ወጣቶች እንዲጋቡ ሊደፋፈሩ አይገባም፡፡ በሚገባ ሳይዘጋጁ፣ የአካልና የአዕምሮም ኃይል ሳይዳብር፣ ውጤቱም ዘላቂ የሆነ ጋብቻን የመሰለ ዋና ግንኙነት እንዲህ በችኮላ ሊጀመር አይገባም፡፡ CLAmh 13.4

የሚጋቡትም ባለጸጋ ባይሆኑም ጤነኛ መሆን አለባቸው፡፡ በዕድሜም በጣም መራራቅ የለባቸውም፡፡ ይህን ሕግ አለመከተል በዕድሜ አነስተኛ የሆነውን (የሆነችውን) ጤና ያጓድላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜም የሚወለዱት ልጆች የአካልና የአዕምሮ ጥንካሬ ያንሳቸዋል፡፡ በዕድሜ ከገፋ ሰው ወጣትነታቸው የሚያስፈልገውን ዓይነት ጓደኝነት ለማግኘት አይችሉም፤ ከዚህም በላይ ፍቅርና ተመሪነት በበለጠ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ አባትየው ወይም እናቲቱ በሞት ይለዩዋቸው ይሆናል፡፡ CLAmh 13.5