የተሟላ ኑሮ

89/201

የውድቀት ጎጂነት (አደገኛነት)

ለመሻሻል የሚመኙም ቢሆኑ የመውደቅ አደጋ ይጠብቃቸዋል፡፡ በብልሃትና በደግነት ሊታዩ ይገባል፡፡ ከጥፋት ለመውጣት የሚጥሩትን ማሞገስና ማሞካሸት ለጥፋታቸው ምክንያት የሚሆንበትም ጊዜ አለ፡፡ የኃጢአት ተግባራቸውን በሕዝብ ፊት ቆመው እንዲዘረዝሩ ማድረግ ለተናጋሪዎቹም ለአድማጮቹም አደገኛ ነው፡፡ የክፋትን ትርዒት በዓይነ ሕሊና መመልከት ለአእምሮም ለመንፈስም አይበጅም፡፡ CLAmh 91.2

ለዳኑት ራሳቸውን ከሁሉ የበለጡ አድርጎ ማስገመት አጉል ነው፡፡ እንዲህ ከሆነ የኃጢአት ዘመናቸው ከሌሎች የተለዩ አድርጎ የለቀቃቸው መሆኑን የሚገምቱ ጥቂቶች አይሆኑም፡፡ ራስን የማስመካትና በራስ ላይ የመተማመን ስሜት ያድርባቸዋል፡፡ ጸንተው ሊቆሙ የሚችሉ ራሳቸውን ንቀው በክርስቶስ ላይ ሲመኩ ብቻ ነው፡፡ CLAmh 91.3

ራሳቸው በዕውነት የተመለሱ ሰዎች ለሌሎች መሥራት አለባቸው፡፡ ለሠይጣን መገዛትን ትቶ ክርስቶስን ሊያገለግል የሚሞክረውን ሰው ማንም ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ምክንያት እንዳይሆን ይጠንቀቅ፡፡ ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር የሚታገለውን ሰው የክርስቶስ አገልጋይ እንዲሆን አደፋፍሩት፡፡ CLAmh 91.4

የክርስቶስን ጥበብ የተቀበሉ ሰዎች ርዳታ የሚፈልጉትንና ከልባቸው ተመልሰው ካልተረዱ ግን እንደገና ሊወድቁ የሚችሉትን ነፍሳት ይመለከታሉ፡፡ CLAmh 91.5

ገና ያልበረቱትን ነፍሳት ወዳጆቻቸው እንዲያደርጓቸው እግዚአብሔር ልጆቹን በልባቸው ዕውቀትንና ማስተዋልን ያሳድራል፡፡ ያለፈው ኃጢአታቸው ምንም ቢከፋ ምንም ያህል በኃጢአት ቢጨማለቁ ለመመለስ ከፈለጉ ክርስቶስ በደስታ ይቀበላቸዋል፡፡ ከዚያ በኋላ ለክርስቶስ የሚያበረክቱት አገልግሎት እንዲኖራቸው ሥራ ስጧቸው፡፡ እነርሱ ከነበሩበት ማጥ (ረግረግ) ያሉትን ለማዳን ከፈለጉ ፍላጎታቸውን ማሟላት የሚችሉበትን ምቹ ጊዜ ስጧቸው፡፡ መንፈሳዊ ብርታት እንዲያገኙ ከቀድሞ ክርስቲያናት ጋር አዛምዷቸው፡፡ ጌታን በማገልገል ሁልጊዜ ተግተው እንዲሠሩ ሥራ ስጧቸው፡፡ CLAmh 91.6