የተሟላ ኑሮ

90/201

በክርስቶስ ማመን

ብርሃን በሕይወታቸው ላይ ከበራ የጥንት ኃጢአን እነርሱ በነበሩበት ችግር ያሉትን ሰዎች ታጥቀው ያገለግላሉ፡፡ CLAmh 92.1

በየሱስ በማመን ከፍ ያለ አግልግሎት ስለሚያበረክቱ ነፍሳትን ለማዳን ለከፍተኛ ኃላፊነት ይታጫሉ፡፡ ጉድለታቸውን በመገንዘብ የተፈጥሮ ድካማቸውን ያውቃሉ፡፡ የኃጢአትን ብርታትና የመጥፎ ልማድን አደገኛነት በደንብ ይረዳሉ፡፡ ክርስቶስ ካልረዳቸው ድል ነሺነትንም እንደማያገኙ በማወቅ “ጌታ ሆይ ነፍሴን ላንተ እሰጣሁ” የሚል የዘወትር ጸሎት ያቀርባሉ፡፡ CLAmh 92.2

“ሌሎችን ሊረዱ የሚችሉ እደነዚህ ያሉት ናቸው፡፡ ተፈትኖና ተቸግሮ የነበረ፤ ተስፋው ጨልሞበት የነበረ፤ ግን የፍቅርን መልዕክት በመስማት የዳነ ሰው ነፍሳትን የመመለስን ጥበብ ያስተውላል፡፡ CLAmh 92.3

ጌታ ፈልጎ ስላዳነው በልቡ ጌታን ያፈቀረ ሰው እርሱ የጠፉትን መፈለግ ይቀናዋል፡፤ ኃጢአተኞችን ወደ እግዚአብሔር በግ ያመላክታቸዋል፡፡ ራሱን ምን ሳይቆጥብ ለክርስቶስ ያስረክባል፡፡ በጌታ ዘንድም ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ CLAmh 92.4

ርዱኝ በማለት ያወጣውን እጁን ረዳቱ ደርሶ ጨብጦታል፡፤ በዚህ ዓይነት አገልግሎት ብዙ የጠፉ ወደ አባታቸው ይመለሳሉ፡፡ CLAmh 92.5