የተሟላ ኑሮ

82/201

በደም የተለወሰ ገንዘብ

የአስካሪ መጠጦች ይዞታ በዓለም ላይ አንሰራርቷል፡፡ በገንዘብና በልምድ፤ በሱስ የተደገፈ ነው፡፡ ኃይለኛነቱ ቤተክርስቲያንንም ያሰጋታል፡፡ ሀብታቸውን በመጠጥ ንግድ ያዳበሩ ሰዎች የቤተክርስቲያን “ቀዋሚና ታማኝ” አባሎች ናቸው ተብለው ተመዝግበዋል፡፡ ብዙዎቹ በበጎ አድራጎት ስም ከፍተኛ የገንዘብ ችሮታ ለቤተክርስቲያን ይለግሳሉ፡፡ የሰጡት ገንዘብ ለቤተክርስቲያን ማስፋፊያና ለቀሳውስቱ አበል ይውላል፡፡ የዚህን ዓይነት ገንዘብ አሜን ብለው የሚቀበሉ አብያተ ክርስቲያናት በአድራጎታቸው የአልኮሆልን መጠጥነት መደገፋቸው ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ወንጌላዊው ለእውነት በእውነት መቆም ያስፈራዋል፡፡ ስለአልኮሆል መጠጥ ነጋዴዎች እግዚአብሔር ያለውን አስተያየት በሚገባ አያስረዳም፡፡ ይህን አድራጎት በግልጥ የነቀፈ እንደሆነ ቄሱ ጉባዔውን ቅር እንደሚሰኝ፤ ተወዳጅነቱ እንደሚቀንስ፤ ደሞዙንም እንደሚያጣ ያውቃል፡፡ CLAmh 83.3

የእግዚአብሔር ሥልጣን ከቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ይበልጣል፡፡ ለመጀመሪያው ነፍሰ ገዳይ “የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮሃል” ያለው አምላክ የአልኮሆል መጠጡን ነጋዴ መሥዋዕት አይቀበልም፡፡ (ዘፍ 4፡10) ገንዘቡ በደም የተለወሰ (የተበከለ) ነው፡፡ መርገም አለበት፡፡ (ኢሳይያስ 1፡11-15 CLAmh 83.4

ሰካራሙ ከዚያ የተሻለ ሥራ ሊያሠራ የሚያስችል ችሎታ አለው፡፡ ለዓለም በረከትና ለእግዚአብሔር ክብር ሊሆን የሚችል ተሰጦ ታድሎ ነበር፡፤ ታድያ ምን ይሆናል! ሰዎች ሕይወቱን በወጥመድ ያዙበት፡፡ በርሱ መዋረድና መጎሳቆል የራሳቸውን ሲያይ አዳበሩ፡፡ እነርሱ የገፈፉት ምስኪኑ ሰው በድኅነት ሲንገላታ ራሳቸው ደልቷቸውና ተንደላቅቀው ይኖራሉ፡፡ ግን እግዚአብሔር የሰካራሙን ደም ሕይወትን እንዲበላሽ ካደረጉት ሰዎች እጅ ይፈልጋል፡፡ ወንጀላቸውን በስጦታና በገንዘብ ሊሸፋፍኑ የሚሞክሩትን በዋዛ አይለቃቸውም፡፡ CLAmh 83.5

የሰማይ ገዥ የስካርን መነሾና ውጤት ለይቶ ማወቅ አይሳነውም፡፡ ለድንቢጥ የሚጠነቀቅ፣ የሜዳው ሳር የሚያስጌጥ አምላክ በአርኣያው የፈጠራቸውን፣ በደሙ የገዛቸውን ችላ አይላቸውም፤ ከጩኸታቸውም ጆሮውን አይመልስም፡፡ ለችግርና ለወንጀል መብዛት ምክንያት የሚሆነውን ድርጊት ሁሉ እግዚአብሔር በቀላል አይመለከተውም፡፡ CLAmh 84.1