የተሟላ ኑሮ
የሚጠጡ ወላጆች አርኣያነት
የዚህ የመጠጥ ቤት ክፋቱ የቤቱን ምሰሶ ያናጋዋል፡፡ ብዙ ሴቶች የመጠጥ ሱሰኞች ሆነዋል፡፡ በብዙ ቤቶች ውስጥ እርዳታና መከባከብ የሚያስፈልጋቸውን ሕፃናት በመጠጥ ምክንያት እናቶቻቸው ችላ ይሏቸዋል፡፡ ልጆች በዚህ መጥፎ ጥላ ስር ያድጋሉ፡፡ ለወደፊቱ ከወላጆቻቸው የከፋ ኑሮ ቢኖሩ እንጂ ምን ተስፋ አላቸው? CLAmh 82.5
የክርስትና አማካይ ቦታ ከተባሉት ቦታዎች ይህ መጥፎ ልምድ ወደ አረመኔዎች መኖሪያ ይዛመታል፡፡ CLAmh 82.6
ምስኪኖቹ መሃይማን የተናገሩትን በማመን የአልኮሆ ተገዥዎች ይሆናሉ፡፡ ከአረመኔዎች መካከል እንኳን የአልኮሆልን መርዝነት የሚረዱ አስተዋዮች አሉ፡፡ ግን የአገራቸውን ሰዎች ከመጣባቸው ጠንቅ ማዳን ሳይሳካላቸው ይቀራሉ፡፡ ሠለጠንን የሚሉት ሰዎች ትንባሆን፣ አልኮሆልንና ሌሎች ሱስ የሚያስዙትን ነገሮች ለአረማውያን ያዛምታሉ፡፡ CLAmh 82.7
በትምህርት ያልተገራው መሃይም በመጠጥ ኃይል ሲገፋፋ ከአውሬ የማይሻል ይሆንና ወደ ቦታው ወንጌላውያንን መላክ ከማይቻልበት ደረጃ ይደረሳል፡፡ ሰዎችን ከእግዚአብሄር ጋር በማስተዋወቅ ፋንታ ከክፋት ጋር ስለሚያዛምዷቸው ለአገራቸው ውድቀት፣ ለጎሣቸው ጥፋት የሚሆን ጠንቅ ይሸምታሉ፡፡ CLAmh 83.1
ስለዚህ የሠለጠኑት አገሮች ዜጎች በማደግ ላይ ባሉት አገሮች ሕዝብ ዘንድ ይጠላሉ፡፡ CLAmh 83.2