የተሟላ ኑሮ
16—አልኮሆል ነክ መጠጦችና ዘመናዊ ኑሮ
“ቤቱን በግፍ ሰገነቱን በዓመፃ ለሚሠራ ለራሴ ሰፊ ቤት ትልቅም ሰገነት እሠራለሁ ለሚል፤ መስኮትንም ለሚያወጣ በዝግባም ሥራ ለሚያስጌጥ፤ በቀይ ቀለምም ለሚቀባው ወዮለት፡፡ … በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን … ዓይንህና ልብህ ግን ለስስት፣ ንጹህ ደምንም ለማፍሰስ ዓመፅንና ግፍንም ለመሥራት ነው፡፡” (ኤርምያስ 22፡13-17) CLAmh 81.1
ይህ ጥቅስ የሚያብራራው አስካሪ መጠጥ የሚሠሩትንና የሚነግዱትን ተግባር ነው፡፤ ተግባራቸው ገፈፋ ነው፡፡ ለሚከፈላቸው ገንዘብ ተመጣጣኝ አገልግሎት አያበረክቱም፡፡ በኪሳቸው የሚሰበስቧት እያንዳንዷ ብር በከፋዩ ላይ መርገምን ትጨምራለች፡፡ CLAmh 81.2
እግዚአብሔር በለጋሥ እጅ ለሰው ሁሉ በረከቱን አድሎታል፡፡ ስጦታው በብልሃት ቢሠራበት ኖሮ ዓለም ከድህነት በተገላገለ ነበር፡፡ የሰዎች ክፋት የእግዚአብሔርን በረከት ወደ መርገም ይለውጠዋል፡፡ በሰዎች መስገብገብና ፍትወት ምክንያት ለበረከት የተሰጠን እህል ሥቃይንና ችግርን የሚያስከትል መርዝ ይሆናል፡፡ CLAmh 81.3
በየዓመቱ በብዙ ሚሊዮን ጋሎን የሚሰፈር አልኮሆል ነክ መጠጥ ሰዎች ይጠጣሉ፡፡ መንገላታትን፣ ድህነትን፣ በሽታን፣ ውርደትን፣ ሴሰኝነትን፣ ወንጀልንና ሞትንም ለመሸመት በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ብር ወጭ ይሆናል፡፡ ለትርፉ ሲል የመጠጥ ነጋዴው የሰዎችን አካልና አእምሮ የሚያበላሽ መጠጥ ለደንበኞቹ ይሸጣል፡፡ ለጠጩ ቤተሰብ መንገላታትና ድህነት ጠንቅ ይሆናል፡፤ CLAmh 82.1
ያመንዝራዎች ቤቶች፣ የዓመፅ ዋሻዎች፣ የወንጀል ችሎቶች፣ እሥር ቤቶች፣ የአእምሮ በሽተኞች ቦታ ሆስፒታሎች ሁሉ የተሞሉት ከመጠጥ ቤት በተመረዙ እድለ ቢሶች ነው፡፡ CLAmh 82.2
“እንደ ጥንቷ ባቢሎን” በሰዎች ነፍስ ይጫወታል፡፡ ከመጠጥ ሻጩ ጋር ዋናው የነፍስ ፀር ተሰልፏል፡፡ ክፉ የተባውን ሁሉ ሰዎችን ለማጥመድ ወጥቶና ወርዶ ያዘጋጃል፡፤ በከተማና በገጠር፣ በባቡር ውስጥ፣ በመሥሪያ ቤት፣ በመደሰቻ አዳራሾች፣ በቤተ ክርስቲያን የጌታ ራት ሥነ ሥርዓት ሲካሄድ ሳይቀር ሰይጣን አሽከላውን (ወጥመዱን) ይዘረጋል፡፡ CLAmh 82.3
የስካርን መንገድ ለመደልደል ያልሞከረው ዘዴ የለውም፡፡ ሥራው ከቀን ወደ ቀን፣ ከወር ወደ ወር፣ ከዓመት ወደ ዓመት ይቀጥላል፡፡ ለአገር ኩራትና መመከያ ይሆናሉ ተብለው ተስፋ የተጣለባቸው አባቶች፣ ባሎች፣ ወንድሞች በመጠጥ መርዝ ተነድፈው ተንገላተውና ተጐሳቁለው ወደየቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ CLAmh 82.4