የተሟላ ኑሮ

79/201

የምግብ ፍላጎታችሁን ተቆጣጠሩ

የምግብ ፍላጎታችሁን አሠልጥኑ፤ ልጆቻችሁንም አካልን ከሚበዘብዝ ምግብ እንዲርቁ አስተምሩ፡፡ በአካባቢያቸው ያለውን ክፋት መቋቋም እንዲችሉ አእምሯቸውን ማጠንከር ያስፈልጋል፡፡ CLAmh 80.3

በሌሎች በቀላሉ እንዳይመሩ ጽኑ አሳብ እንዲኖራቸው አስተምሩአቸው፡፡ በሌሎች መሪነት ከመሸንገል ይልቅ ሌሎችን ወደ መልካም ነገር የሚስቡ ይሁኑ፡፡ መልካም ልምድና የተሟላ የምግብ አመራረጥ እንዲኖራቸው አድርጎ ልጆን ማሳደግ የእናቶች መብትና ግዴታ ነው፡፡ CLAmh 80.4

መሻትን አለመግዛትን ለማዳከም ብዙ ጥረት ይደረጋል፡፡ አብዛኛው ጥረት ግን ዓላማውን የሳተ ነው፡፡ የመሻትን መግዛት ሠራተኞችና ደጋፊዎች በሻይ፣ በቡና፣ በቅመማቅመምና ባልተስተካከለ አመጋገብ የሚደርሰውን ጉዳት መገንዘብ አለባቸው፡፡ CLAmh 80.5

የተስተካከለ አስተሳሰብና የጸና መንፈስ የሚገኘው በተሟላ የአካል ይዞታ አማካይነት መሆኑን ሰዎች ይገንዘቡ፡፡ ናርኮቲክስና አካልን የሚበዘብዙ የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች አካልን አዳክመው አእምሮን ያቀጨጫሉ፤ መንፈሳዊ ዕድገትን ያደኩራሉ፡፡ የዓለምን ሞራል የሚያበላሸው ዋና ጠንቅ መሻትን አለመግዛት ነው፡፡ ዓይኑ ያየውን ሁሉ የሚያግበሰብስ ሰው ፈተናን ለመቋቋም ኃይል ያንሰዋል፡፡ በሻይ፣ በቡና፣ በትንባሆ፣ ለሚመጣው ጠንቅ ዋስትናው አለመንካት፣ አለመቅመስ፣ አለመያዝ ነው፡፡ የቡናና የሻይ አደገኛነት ከትንባሆና ከአልኮሆል ነክ መጠጥ አያንስም፡፡ ለመተው ያለው አስቸጋሪነትም ከሰካራምነት አይሻልም፡፡ የዚህን ሱስ መተው የሚሞክሩ ሰዎች ለጊዜው ብዥ ይልባቸዋል፤ ሲያጡም ይሰቃያሉ፡፡ ግን ከበረቱ ሱሱን ሊያሸንፉ ይችላሉ፤ ሲያጡም አይቸገሩም፡፡ ተፈጥሮ ከደረሰባት ጉዳት ለማገገም ጊዜ ያስፈልጋታል፡፡ ግን ጊዜ ከተሰጣት እንደገና ተጠራቅማ ሥራዋን በሚያኮራ ይዞታና በጨዋነት ታከናውናለች፡፡ CLAmh 80.6