የተሟላ ኑሮ
በውሸት የተሞሉ መጻሕፍት
ለልጆች የሚሰጠው ትምህርት ብዙ ተረትና ልብ ወለድ ታሪክ ሞልቶበታል፡፡ የዚህ ዓይነት መጻሕፍት በትምህርት ቤቶች ይሠራባቸዋል፤ በብዙ ቤቶችም ውስጥ ይገኛሉ፡፡ ክርስቲያን የሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው በሐሰት በተሞሉ መጻሕፍት እንዲጠቀሙ እንዴት ይፈቅዳሉ? ልጆ ወላጆቻቸው ካስተማሯቸው ጋር የማይስማማውን የታሪኮች ትርጉም በጠየቁ ጊዜ ታሪኮቹ እውነተኛ አይደሉም የሚል መልስ ይሰጣቸዋል፤ ይሁን እንጂ ይህን በማለት በታሪኮቹ ምክንያት የሚመጣውን ጉዳት ሊያስወግዱ አይችሉም፡፡ በነዚህ መጻሕፍት ውስጥ የሚሰጠው ሐሳብ ልጆችን ወደ ስህተት መንገድ ይመራል፡፡ ስለ ሕይወት የተሳሳተ አስተያየት ይኖራቸዋል፤ ለሌላውም ነገር ምኞት ያድርባቸዋል፡፡ CLAmh 46.3
እነዚህ መጻሕፍት በሰፊው እንዲሰራባቸው የሚያደርገው ሰይጣን ነው፡፡ የወጣቶችንና ያዋቆችን አሳብ ከጠባይ መገንባት ሥራ ለመመለስ ይመኛል፡፡ ልጆቻችንን በማታለል በሥራው ሊያጠፋቸው ምኞቱ ነው፡፡ ስለዚህ አእምሯቸውን ከእግዚአብሔር ቃል በማራቅ ሊጠብቋቸው የሚችሉትን እውነተኛ ነገሮች እንዳያውቁ ያደርጋል፡፡ CLAmh 46.4
እውነት ያልሆነ ነገር የያዙ መጻሕፍት ለልጆች ሊሰጡ አይገባም፡፡ ልጆች ትምህርትን በሚገበዩበት ጊዜ የኃጢአት ዘር እንዳይገዙ መጠንቀቅ ያሻል፡፡ አእምሯቸው ጠና ያለ ሰዎች ከነዚህ መጻሕፍት ቢወገዱ ራሳቸውን ከመጠበቃቸው በላይ በምሳሌነታቸው ወጣቶችን ወደ ጥሩ ነገር ለመመለስ ይረዳል፡፡ መለኮታዊና እውነተኛ የሆነ ብዙ ነገር ሞልቷል፡፡ ለዕውቀት የጠጠሙ ሰዎች ወደ ድፍረርስ ምንጭ መሔድ የለባቸውም፡፡ አምላካችን እንዲህ ይላል፤ CLAmh 46.5
“ጆሮህን አዘንብለህ የጠቢባንን ቃላት ስማ፤
ልብህንም ወደ ዕውቀቴ አድርግ፤
እነሱን በውስጥህ ብትጠብቅ፤
እምነትህ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፤
ለአንተ ዛሬ እነሆ አስታወቅሁህ፤
የእውነትን ቃል እርግጠኝነት አስታውቅህ ዘንድ፤
ለሚጠይቅህም እውነትን ቃል ለመመለስ ይቻልህ ዘንድ፡፡”
CLAmh 47.1
ምሳሌ 22፡17-21