የተሟላ ኑሮ
ንጹሕ የእውቀት ምንጭ
እንደዚሁም ክርስቶስ የእውነትን ደንብ በወንጌል ሰጥቷል፡፡ የሱን ትምህርት በመቀበል ከአእግዚአብሔር ዙፋን ከሚፈልቀው ንጹሕ ምንጭ ልንጠጣ እንችላለን፡፡ ከሱ ጊዜ በፊት ከታወቀው ሁሉ የበለጠ ዕውቀትና ከማንኛውም ፍልስፍና የበለጠ ፍልስፍና ለሰው ሊሰጥ በቻለ ነበር፡፡ ብዙ ምሥጥሮችን ለመግለጽና እስከ ጊዜ ፍጻሜ ድረስ ሰው ይህን ዕውቀት በንቃት እንዲከታተል ለማድረግ ይችል ነበር፡፡ ነገር ግን የመዳን ሳይንስ ከማስተማር አንድ አፍታም ተግ አላለ፡፡ ጊዜው፣ ችሎታውና ሕይወቱ የተወደዱ ነበሩ፤ የተጠቀመባቸውም የሰውን ነፍስ ለማዳን ብቻ ነበር፡፤ የመጣው የጠፋውን ለመፈለግና ለማዳን ነበር፤ ከዚህም ዓላማ ምን የሚመልሰው ነገር አልነበረም፡፡ ምን ነገር ዓላማውን እንዲያስተወው አልፈቀደም፡፡ CLAmh 47.2
ክርስቶስ የሚጠቅም ዓይነት ዕውቀት ብቻ አካፈለ፡፡ ለሕዝቡም የሰጣቸው ትምህርት የዕለት ኑሯቸውን የሚያሻሽል ነበር፡፡ ለማወቅ በመጓጓት ጥያቀዎችን ይዘው በመጡበት ጊዜ ጥያቄዎቻቸውን በሚፈልጉት አኳኋን አልመለሰላቸውም፡፡ እንደዚህ ያሉትን ጥያቄዎች ሁሉ ጠለቅ ያሉ ሐሳቦች ለመስጠት ተጠቀመባቸው፡፡ ከዕውቀት ዛፍ ለመጠቀም ለፈለጉ ሁሉ የሕይወት ፍሬ ሰጣቸው፡፡ ከዘላለም ሕይወት ምንጭ በስተቀር ሌላው ሁሉ ምንጭ ታሸገ፡፡ CLAmh 47.3
የሰውን ልምድ በመከተል እንዳይረክሱ በማለት መድኃኒታችን ማንም በረቢዎች ትምህርት ቤት እንዲማር አላደፋፈረም፡፡ የተሻለ ጥበብ ከኛ ጋር እያለ የሰዎችን ንግግር እንደዕውቀት የምንቀበለው ለምን ይሆን? CLAmh 48.1
ስለዘላለማዊ ነገሮችና ስለ ሰብአዊ ድካም ያየሁት ነገር ልቤን ነክቶታል፤ ሕይወቴንም ለውጦታል፡፡ ሰው የሚመሰገንበት ወይም የሚከበርበት ነገር አይታየኝም፡፡ የዓለማዊ ጠቢባንና ትልቅ የሚባሉ ሰዎች አስተያየት መከበር የሚገባበት ምክንያት አይታየኝም፡፡ መለኮታዊ ብርሃን የሌላቸው ሰዎች ስለ እግዚአብሔር እቅድና መንገድ እንዴት ትክክለኛ አስተያየት ሊኖራቸው ይችላሉ? በሙሉው ይክዱታል፤ መኖሩን ችላ ይላሉ ወይም በራሳቸው አስተያየት ኃይሉን ይወስናሉ፡፡ CLAmh 48.2
ሰማይንና ምድርን የፈጠረው፤ ከዋክብትን በሰማይ በሥርዓት ያስቀመጠውና የፀሐይንና የጨረቃን ሥራ የወሰነው አስተማሪያችን ይሁን፡፡ CLAmh 48.3