የተሟላ ኑሮ
በመጋረጃው ውስጥ
የፍቅር ድርሰቶች፣ መናኛና ልብ የሚመስጡ ልብወለድ ታሪኮች አንባቢውን መጉዳታቸው አይቀርም፡፡ ደራሲው ዓላማዬ የሞራል ትምህርት ለመስጠት ነው ይል ይሆናል፡፡ በድርሰቱም ውስጥ የሃይማናት ስሜት ተሰባጥሮ ይገኝበት ይሆናል፤ ይሁን እንጂ እንደዚህ ያሉት አሳቦች ለማይጠቅምና ዋጋ ለሌለው ነገር መሸፈኛ ናቸው፡፡ CLAmh 45.4
“ዓለም አስጎምጂ በሆነ ስህተት በተሞሉ መጻህፍት ተሞልቷል፡፡ ወጣቶች መጽሐፍ ቅዱስ ሐሰት ነው ብሎ የሚንቀውን ነገር እውነት ነው ብለው ይቀበላሉ፤ የነፍሳቸው አጥፊ የሆነውንም ስህተት ይወዳሉ፤ የሙጥኝ ይይዛሉ፡፡ CLAmh 46.1
እውነትን ለማስተማር ወይም መጥፎን ነገር ለመግለጽ የተጻፉ ልብወለድ ድርሰቶች አሉ፡፡ አንዳንዶቹ ጥሩ ውጤት አስገኝተዋል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ነው የማይባል ጉዳትም አስከትለዋል፡፡ በተለይም ወጣቶችን ጎጂ የሆኑ ሐሳቦች የሚያነሳሱ አንዳንድ አረፍተ ነገሮችና የሐሳብ ሥዕሎች ይገኝባቸዋል፡፡ በድርሰቱ ውስጥ የሚገልጹትን አንጐልን የማይጠቅምና ለመንፈሳዊውም ልምድ የማይገጥም ያደርገዋል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን ያስጠላል፡፡ መንፈሳዊ ነገሮች በሐሳብ ውስጥ ቦታ የላቸውም፡፡ አንጐል ንጹህ ያልሆነውን ነገር አዘውትሮ እንደተመለከተ መጠን ስሜት ይነሳሳል፤ ፍጻሜውም ኃጢአት ነው፡፡ CLAmh 46.2