የተሟላ ኑሮ
ለሕፃናት የተሻለው ምግብ
ለሕፃን የተሻለው ምግብ በሥነ ፍጥረት የተዘጋጀለቱ ነው፡፡ ይህን ምግብ ሊነሳ አይገባውም፡፡ ለራስዋ ምቾት ወይም ከህብረተሰብ ለምታገኘው ደስታ ብላ የተከበረውን ሕፃንን የማጥባት ኃላፊነት ችላ የምትል እናት በጣም ጨካኝ ናት፡፡ CLAmh 29.3
ልጆች ትክክለኛ ያመጋገብ ልምድ እዲኖራቸው ማድረግ በጣም ዋና ነገር ነው፡፡ ልጆች የሚበሉት ለመኖር እንጂ የሚኖሩት ለመብላት አለመሆኑን መማር አለባቸው፡፡ ይህ ዓይነት ትምህርት ሊጀመር የሚገባው ሕፃኑ ገና ከእናቱ እቅፍ ሳይወጣ ነው፡፡ ሕፃን ምግብ ሊሰጠው የሚገባ በተወሰነ ጊዜ ነው፤ እንዳደገም መጠን የሚመገብበት ጊዜ መራራቅ አለበት፡፡ በሆዱ ውስጥ ሊፈጭ የማይችለውን ጣፋጭ ነገር ወይም ያዋቂዎች ምግብ ሊሰጠው አይገባም፡፡ ሕፃናትን ስለመመገብ የሚደረገው ጥንቃቄና ጊዜ መጠበቅ ጤነኛና የማይበሳጩ ከማድረጉም በላይ ለወደፊቱ ሕይወታቸው የጥሩ ልምድ መሠረት ይሆናል፡፡ CLAmh 29.4
ልጆች ከሕፃንነት ደረጃ ሲያልፉ ስለምግብ ልምዳቸውና አምሮታቸው በጥንቃቄ ማስተማር ይገባል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ስለ ጤናቸው ባለማሰብ የፈለጉትን ነገር በፈለጉት ሰዓት እንዲመገቡ ይፈቀድላቸዋል፡፡ ለጤና ተስማሚ ላልሆነ የምግብ ዓይነት የሚጠፋውን ጉልበትና ገንዘብ በማየት ለልጆች የበለጠ ደስታ የሚያስገኝና የሕይወት ዋና ዓላማ የምግብን አምሮት ማርካት ነው ብለው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል፡፡ የዚህ ዓይነት ትምህርት ውጤቱ በቃኝ ማለትን አለማወቅ ነው፤ ከዚያ በኋላ መታመም ይመጣል፤ በኋላም ጐጂ የሆኑ መድኃኒቶችን መውሰድ ይቀጥላል፡፡ CLAmh 29.5