የተሟላ ኑሮ
የሕጻን አለባበስ
የሕፃኑ ልብስ ሙቀትና ምቾት የሚሰጥ የሆነ እንደሆን ብስጭትና መቁነጥነጥ ከሚያመጡት ዋና ምክንያቶች አንዱ ተወገደ ማለት ነው፡፡ የሕፃኑ ጤና ይሻሻላል፤ እናቲቱም ለሕፃኑ መጠንቀቅ ጉልበትዋንና ጊዜዋን የሚያጠፋ ሆኑ አታገኘውም፡፡ CLAmh 28.3
ጥብቅ ልብስ የልብንና የሳንባን ሥራ ስለሚያውክ ሊወገድ ይገባል፡፡ ማንኛውም የሰውነት ብልት እንደ ልቡ እንዳይቀሳቀስ አድርጎ በሚያጠብቅ ልብስ ምክንያት ማንኛውም የሰውነት ክፍል ምቾት ማጣት አይገባውም፡፡ ሕፃናት እንደልባቸው ለመተንፈስ እንዲችሉ ልብሳቸው የማያጠብቅ ወይም ልል መሆን ሲገባው ትከሻቸው የልብሱን ክብደት እንዲሸከመው መሆን አለበት፡፡ CLAmh 28.4
በአንዳንድ አገሮች የሕፃናትን ትከሻ፣ እጅና እግር ያለመሸፈን ልምድ አለ፡፡ ይህ ዓይነት ባሕል በጣም ሊነቀፍ ይገባዋል፡፡ እጅና እግር ከዋናዎቹ የደም መዘዋወሪያ ሥሮች ራቅ ያሉ እንደመሆናቸው መጠን ከከሌላው አካል የበለጠ መሸፈን አለባቸው፡፡ ወደ አካል ጫፎች ምግብና ሙቀት የሚወስዱት የደም ሥሮች ትልልቅ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የአካል ጫፎች (እጅና እግር) እንደሚገባ ያልተሸፈኑ እንደሆነ የደም ስሮቹ ይጠባሉ፤ ከአካላችንም በቀላሉ ሊጐዱ የሚችሉት ክፍሎች ብርድ ይሰማቸዋል፤ ጠቅላላው የደም መዘዋወርም ይደናቀፋል፡፡ CLAmh 28.5
የሥነ ፍጥረት ኃይል የልጆችን አካል በትክክል ለመገንባት እንዲችል ማንኛውም ዓይነት ርዳታ ሊደረግለት ይገባል፡፡ እጅና እግራቸውን በደንብ ያልለበሱ እንደሆነ ልጆች በተለይም ልጃገረዶች የአየሩ ሁናቴ ጥሩ ካልሆነ በስተቀር ከቤት ሊወጡ አይችሉም፡፡ እንዳይበርዳቸው በማለት ከቤት ውስጥ ተዘግተው ይውላሉ፡፡ ልጆች በደንብ የለበሱ እንደሆን ግን በጋም ሆነ ክረምት ውጭ እንደልባቸው ለመጫወት ይችላሉ፡፡ CLAmh 28.6
ልጆቻቸው ጤነኛ እንዲሆኑ የሚመኙ እናቶች ሁሉ እንደሚገባ ሊያለብሷቸውና የአየሩ ሁናቴ ተስማሚ በሆነበት ጊዜ ሁሉ ውጭ እንዲጫወቱ ሊያደፋፍሯቸው ይገባል፡፡፤ CLAmh 29.1
ባሕል በማይፈቅደው አኳኋን ልጆችን ለጤና እንደሚስማማ አድርጎ ለማልበስና ለማስተማር አድካሚ ይሆን ይሆናል፤ ይሁን እንጂ የድካሙ ዋጋ ብዙ ነው፡፡ CLAmh 29.2