የተሟላ ኑሮ

151/201

በቤተሳይዳ መተመቂያ

“በእየሩሳሌም በበጎች በር አጠገብ በእብራይስጥ ቤተሳይዳ የምትባል አንዲት መጥመቂያ ነበረች፤ አምስትም መመላሻ ነበረባት፡፡ በእነዚህ ውስጥ የውኃውን መንቀሳቀስ አየጠበቁ በሽተኞችና እውሮች፤ አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ህዝብ ይተኙ ነበር፡፡” (ዮሃንስ 5፡2-3) ፡፡ CLAmh 157.2

በተለየ ጊዜ ውኃው ይናወጥ ነበር፤ ውሃውን ያንቀሳቀሰው ልዩ ሃይል ነው ተብሎ ስለሚታመን መጀመሪያ ቀድሞ የገባ በሽተኛ የበሽታው አይነት ምንም ቢሆን ይድን ነበር፡፡ ብዙ በሽተኞች በቦታው ይገኙ ነበር፤ ግን ከሰው ብዛት የተነሳ በርታ ያሉት ደካሞችን ገፍትረው ማለፍ ነበረባቸው፡፡ CLAmh 157.3

ብዙዎች ወደ መጥመቂያው ሊገቡ አይችሉም ነበር፡፡ ከመጥመቂያው አፋፍ ደርሰው ለመግባት ባለመላቸውም የሞቱት ጥቂቶች አልነበሩም፡፡ CLAmh 157.4

በሽተኞች ከቀን ሃሩር፤ ከለሊት ቁር የሚጠለሉበት መጠለያ ተሰርቶላቸው ነበር፡፡ በየቀኑ እንድናለን በሚል ከንቱ ተስፋ ተጽናንተው ከዚያ ቦታ ብዙ ጊዜ የኖሩ ነበሩ፡፡ ለሊትም አዳራቸው ከዚያ ነበር፡፡ CLAmh 157.5

የሱስ በኢየሩሳሌም ይገኝ ነበር፡፡ ሊጸልይ ብቻውን ወደ መጥመቂያው መጣ፡፡ ምስኪኖቹ በሽተኞች የመዳን እድላቸውን እየተጠባበቁ ተቀምጠው አያቸው፡፡ CLAmh 157.6

በፈዋሽነት ሃይሉ በሽተኞችን በሙሉ ሊያድናቸው ፈልጎ ነበር፤ ግን እለቱ ሰንበት ነበር፤ ህዝብ ወደ ጸሎት ቤት ይጎርፍ ነበር፡፡ እንዳሰበው ቢያደርግ የአይሁዶቹ አጉል መመጻደቅ ለስራው እንቅፋት እንደሚሆንበት አወቀ፡፡ CLAmh 157.7

ግን የአንዱን በሽተኛ ይዞታ ፋታ የማይሰጥ ሆኖ አገኘው፡፡ ለ 38 አመታት ሽባ ሆኖ የኖረ አንድ ሰው ነበር፡፡ CLAmh 158.1

ውሃው ሲንቀሳቀስ ለነፍሴ ያለ ወደ ውሃው ሊወስደው ይችል ነበር ፤ ክፋቱ ውሃው ሲንቀሳቀስ በአጠገቡ የሚረዳው ሰው አይገኝም ነበር ፡፡ የውሃውን መንቀሳቀስ በአይኑ እያየ ሊገባ ባለመቻሉ ሳይድን ይቀራል፡፡ ከእርሱ ይልቅ የበረቱት ቀድመውት ይገባሉ፡፡ ያ ምስኪኑ ረዳት የሌለው ሽባ ለራሳቸው ብቻ በሚያስቡት ሰዎች መካከል የመዳን እድል አልነበረውም፡፡ የነበረው ተስፋ እየመነመነ ፤ ብርታቱ አያለቀ ሄደ፡፡ ሰውየው እንተደለመደው በአልጋው ላይ ተጋድሞ የውሃውን መንቀሳቀስ ከአንገቱ ቀናብሎ ሲመለከት አንድ ርኀሩህ ሰው ቀረብ ብሎ “ልትድን ትወዳለህን?” ሲለው ሰማ፡፡ CLAmh 158.2

እንደገና ተስፋ በልቡ ውስጥ አንሰራራ፤ አሁን እንደምንም እርዳታ የሚያገኝ መስሎ ተሰማው፡፡ ተስፋው ግን ብዙ ሳይቆይ መነመነ፡፡ ባለፈው ጊዜ ውኃው ሲናወጥ ስንት ጊዜ እድል እንዳመለጠው አስታወሰና እንደገና እስኪንቀሳቀስ ድረስ መኖሩ አጠራጠረው ፡፡ ቅሬታ እየተሰማው ዘወር ብሎ “ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጥመቂያይቱ ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም፡፡ ነገር ግን እኔ ስመጣ ሳለው ሌላው ቀድሞኝ ይወርዳል” አለ፡፡ CLAmh 158.3

የሱስ “ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሂድ” አለው (ዮሐንስ 5፡6-8) ፡፡ በአዲስ ተስፋ በሽተኛው የሱስን ቀና ብሎ ተመለከተው፡፡ የፊቱ ፈገግታ፤ የድምጹ ለዛ እንደማንኛውም ተራ ሰው አልነበረም፡፡ ፍቅርና ሃይል በእርሱ ላይ ይታይ ነበር፡፡ ሽባው በየሱስ ንግግር አመነ፡፡ CLAmh 158.4

ያለ ጥያቄ ትእዛዙን ተቀብሎ እንደተባለው ለማድረግ ሲሞክር አካሉ በሙሉ ታዘዘው፡፡ ህዋሳቱና ጡንቻዎቹ በሙሉ አዲስ ህይወት ተቀበሉ፤ ሽባ ሆነው የኖሩት እግሮቹ አገልግሎት መስጠት ጀመሩ፡፡ ቀጥ ብሎ ቆሞ እግዚአብሄርን እያመሰገነ አዲስ ባገኘው ሃይል በቀላሉ ተራመደ፡፡ CLAmh 158.5

የሱስ ለሽባው መለኮታዊ እርዳታ ሊሰጠው ቃል አልገባለትም ነበር፡፡ ሰውየውም ጌታ ሆይ፤ ሙሉ ባለ ጤና እንድሆን ከረዳኸኝ ያልኸኝን እታዘዛለሁ ሊል ይችል ነበር፡፡ ቢጠራጠር ኖሮ የመዳን እድሉ አለፈችው ማለት ነበር፡፡ ግን የክርስቶስን ቃል ሳያመነታ ታዘዘ፡፡ወዲያው ስለሞከረ እግዚአብሄር ረዳው ለመራመድ ፈቃደኛ በመሆኑ ሊራመድ ቻለ፡፡ እንደ ክርስቶስ ትእዛዝ ስላደርገ ጤናማ ሆነ፡፡ CLAmh 158.6