የተሟላ ኑሮ
በመድኅን ቃል ዕመን
በኃጢያት ምክንያት ከእግዚአብሄር ተለይተናል፡፡ መንፈሳችን ሽባ ሆኗል፡፡ ያ ሽባ ሊራመድ እንዳልቻለ ሁሉ በራሳችን ሃይል ቅዱስ ህይወት ልንኖር አንችልም፡፡ CLAmh 159.1
ብዙዎቹ አቅመ ቢስ መሆናቸውን ያውቃሉ፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሄር ጋር የሚያስማማቸውን ሃይል ለማግኘት ይሞክራሉ፡፡ ሙከራ ብቻ ሳይሆን ብርቱ ጥረትም ያደርጋሉ፡፡ ግን አይሳካላቸውም፡፡ ተስፋ በመቁረጥ “እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?” ይላሉ፡፡ (ሮሜ 7፡24) ፡፡ እነዚህ በራሳቸው ጥረት የሚፍጨረጨሩና የሚታገሉ ወደ ላይ ይመልከቱ፡፡ የሱስ በደሙ የገዛቸውን ወደ ታች እየተመለከተ “ልትድን ትወዳለህን?” ይላቸዋል፡፡ ጤናማና ሰላማዊ ሆነህ እንድትነሳ ያዝሃል፡፡ በጌታ ቃል እመን፡፡ ፈቃድህን ለክርስቶስ አስገዛ፡፡ ልታገለግለው ፈቃደኛ ከሆንክና እንደ ትእዛዙ ከሠራህ ብርታት ትቀበላለህ፡፡ CLAmh 159.2
ማንኛውም የሃጥያት ልምድ ቢኖርብህ፤ አካልህና መንፈስህ ባልሆነ መጥፎ ልምድ ቢያዝም ክርስቶስ ከዚያ ክፉ ልምድ ሊያላቅቅህ ፈቃዱ ነው፤ ችሎታም አለው፡፡ “በኃጢአት ለሞተው” ሰው ህይወት (ነፍስ) ይዘራበታል፡፡ (ኤፌሶን 2፡1) በኃጢአት ሰንሰለት የታሰረውን ነጻ ያወጣዋል፡፡ CLAmh 159.3