የተሟላ ኑሮ
የሰማይ በር ተከፈተ
የድውዩን መፈወስ በዚያ ለነበሩት ሰዎች የሰማይን በር ከፍቶ ሙሉ በረከትን አንዳሳያቸው ይቆጠራል፡፡ የተፈወሰው ሰው እግዚአብሄርን እያመሰገነ ፤ሸክሙ እንደ ላባ ቀልሎት በመካከላቸው ሲያልፍ ሰዎቹ “ዛሬስ ድንቅ ነገር አየን” ይባባሉ ነበር፡፡ (ሉቃስ 5፡26)፡፡ CLAmh 156.5
ከጥቂት ጊዜ በፊት ተጋድሞ የነበረበትን አልጋ ተሸክሞ በደስታ እየዘለለ ወደቤቱ ሲመለስ በሰውየው ቤት ውስጥ ታላቀ የደስታ ልቅሶ እያለቀሱ በዙርያው ቆመው ነበር፡፡ በሙሉ ብርታት ጸንቶ ቆሞ አገኙት፡፡ ሰለው የነበሩት ክንዶቹ ብርታት አገኙ ፡፡ በስብሶና ተበላሽቶ የነበረው አካሉ ንጹህ ሆኖ ነበር፡፡ ቀጥ ብሎ ያለችግር ይራመድ ነበር፡፡ በፊቱ ላይ ደስታና ፈገግታ ይታይበት ነበር፤ በሃጥያትና በስቃይ ምክንያት አድሮበት የነበረው ትካዜ በሰላምና በደስታ ተተክቶ ነበር፡፡ CLAmh 156.6
የደስታ ምስጋና ከዚያ ቤተሰብ ዘንድ በወልድ አዳኝነት ለተከበረው ለአብ ቀረበለት፡፡ ሰውየውና ቤተሰቡ በሙሉ ህይወታቸውን ለክርስቶስ ሊስረክቡ ተዘጋጁ፡፡ በእምነታቸው ጥርጥር አልተቀላቀለበትም፤ ተስፋ ለቆረጠው ቤተሰብ ደስታን ላበሰረው መድኅን ታማኝነታቸውን አረጋገጡ፡፡ CLAmh 157.1