የተሟላ ኑሮ
“የለኝም እኔ የማቀርብልህ እተማመናለሁ ብቻ በመስቀልህ፡፡”
እያልን ወደ ቀራንዮ መስቀል መመልከት ነው፡፡ እመን ብቻ ለሚያምን ሁሉ ቀላል ነውና” (ማርቆስ 9፡23) ፡፡ ከአምላካችን ጋር ልንገናኝ የምንችልና ከጨለማ ኃይላት ጋር መታገል የምንችል በሃይማት ብቻ ነው፡፡ አብ በወልድ አማካይነት ክፉን የምንቋቋምበትና የከፋ ቢከፋ ፈተናን የምናሸንፍበት ኃይል ሰጥቶናል፡፡ CLAmh 149.2
ብዙዎች ግን ሃይማኖት ስለሚጎድላቸው ከክርስቶስ ይርቃሉ፡፡ እነዚህ ነፍሳት የራሳቸውን ጉድለት አምነው ራሳቸውን ለርኅሩኁ አዳኛቸው ያስረክቡ፡፡ በራሳችሁ አትመኩ፤ በክርስቶስ ዕመኑ፡፡ በሰዎች መካከል ሳለ ድውያንን ይፈውስ፤ አጋንንትን ያወጣ የነበረው መድኅን አሁንም ኃይሉ ያው ነው፡፡ ስለዚህ ተስፋውን እንደ ሕይወት ዛፍ ቅጠል ጨብጡት፡፡ “ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ወደ ደጅ አልሰደውም፡፡” (ዮሐንስ 6፡37) ፡፡ CLAmh 149.3