የተሟላ ኑሮ

140/201

“ብቻ ተናገር”

አሁንም ጌታ መንገዱን ቀጠለ፤ ግን መቶ አለቃው ራሱ መጥቶ ለየሱስ “ስለዚህ ወዳንተ ልመጣ እንዲገባኝ ሰውነቴን አልቈጠርሁትም፤ ነገር ግን ቃል ብቻ ተናገር፤ ብላቴናዬም ይድናል፡፡ እኔ ደግሞ ለሌሎች ተገዥ ነኝና ከእኔ በታች ጭፍራ አለኝ፤ አንዱንም ሂድ ብለው ይሄዳል፤ ሌላውንም ና ብለው ይመጣል፡፡ ባሪያዬንም ይህን አድርግ ብለው ያደርጋል” በማለት መልእክቱን አረጋገጠ፡፡ (ማቴዎስ 8፡8-9) ፡፡ CLAmh 148.3

ይህ አባባል የሚከተለውን አሳብ የያዘ ነው፡፡ “እኔ የሮማን ኃይል የምወክል ነኝ፡፡ ወታደሮቼም የእኔን የበላይነት አምነው ይቀበላሉ፡፡ አንተም የኃያሉን እግዚአብሔርን ኃይል ትወክላለህ፤ ፍጡር ሁሉ አንተን ይታዘዛል፡፡ በሽታን ራቅ ብትለው “እንዳልኸው ይሆንልሃል፡፡ አንድ ቃል ብቻ ተናገር ባርያዬም ይፈወሳል፡፡” CLAmh 148.4

ክርስቶስም “ሂድና እንዳመንኸው ይሁንልህ” አለው ብላቴናውም በዚች ሰዓት ተፈወሰ” (ማቴዎስ 8፡13) ፡፡ CLAmh 148.5

የአይሁድ ሽማግሌዎች ለወገናቸው ደግ በመሆኑ አሽከሩን ይፈውስለት ብለው ነበር፡፡ “ምኩራብ ሠርቶልናልና ይገባዋል” ብለው ነበር፡፡ መቶ አለቃው ግን “አይገባኝም” አለ፡፡ (ሉቃስ 7፡4-6) ፡፡ ቢሆንም የሱስ እንዲረዳው መጠየቅ አልፈራም፡፡ ዕምነቱ በራሱ ደግነት ሳይሆን በመድኃኒታችን መሐሪነት ነበር፡፤ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን ተረድቶ ነበር፡፡ በዚህ መንገድ ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ ወደ ክርስቶስ ሊቀርብ ይችላል፡፡ “እንደ ምሕረቱ አዳነን እንጅ እኛ ስላደረግነው ጽድቅ ሥራ አይደለም” (ቲቶእ 3፡5) ፡፡ CLAmh 148.6

ኃጢአተኛ በመሆናችሁ ከእግዚአብሔር ዘንድ በረከት የማትቀበሉ መስሎ ይሰማችኋል? ክርስቶስ ወደ ዓለም የመጣ ኃጢአተኞን ሊያድን መሆኑን አትርሱ፡፡ ለእግዚአብሔር የምናቀርበው ምንም ደግነት የለንም፡፡ ልናቀርበው የሚገባን ተማኅጽኖ ኃጢአተኛ መሆናችንና የመድኃኒታችን ርዳታ እንደሚያስፈልገን ነው፡፡ በራሳችን መመካትን ትተን፤ CLAmh 149.1