የተሟላ ኑሮ

139/201

የመቶ አለቃውን አሽከር ፈወሰው

የአንድ መቶ አለቃ አሽከር በጠና ታሞ ነበር፡፡ በሮማውያን ዘንድ አሽከሮች በገበያ የሚሸጡ፤ የሚለወጡ ባሪያዎች ነበሩ፡፡ አብዛኛውን ጊዜም የጭካኔ ተግባርና መንገላታት ይደርስባቸው ነበር፡፡ ያ መቶ አለቃ ግን አሽከሩን ይወደው ስለነበር ቢድንለት ይወድ ነበር፡፡ የሱስ ሊፈውሰው እንደሚችል አመነ፡፡ CLAmh 147.7

መድኅንን ባያየውም በዝና አመነበት፡፡ አይሁዳውያን ወግና ሥርዓት ቢያበዙም የእነርሱ ሃይማኖት ከእርሱ ሃይማኖት መብለጡን ሊክድ አልቻለም፡፡ CLAmh 147.8

በገዥዎችና በተገዥዎቹ መካከል ገደብ የሆነውን የዘር ልዩነትና የጥላቻ አጉል ስሜት ጥሶ ለማለፍ በቅቶ ነበር፡፡ እግዚአብሔርን ማገልገል የተቀደሰ ተግባር መሆኑን ተረድቶ እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን አይሁዶችን በበጎ ዓይን ይመለከታቸው ነበር፡፡ የክርስቶስን ትምህርት በወሬ ሰምቶ መንፈስን የሚያረካ መሆኑን አመነበት፡፡ መንፈሳዊ ስሜቱ የመድኃኒታችንን መምህርነት አሜን ብሎ ተቀበለው፡፡ ግን ጌታን ራሱ ለመቅረብ ብቁነት ስላልተሰማው አሽከሩን እንዲፈውስለት በአይሁድ ሽማግሌዎች አማካይነት አስጠየቀው፡፡ CLAmh 148.1

ሽማግሌዎቹ “ሕዝባችንን ይወዳል፤ ምኩራብም ራሱ ሠርቶልናል፤” በማለት ነገሩን ለየሱስ አቃንተው ነገሩለት፡፡ ግን የሱስ ወደ መቶ አለቃው ቤት ሲጓዝ መኰንኑ ራሱ ለየሱስ “ጌታ ሆይ በቤተ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝምና አትድከም” የሚል መልእክት ላከበት፡፡ CLAmh 148.2