የተሟላ ኑሮ

138/201

በሃይማኖት መንካት

በአካባቢው ይጋፉ ለነበሩት ሕዝብ ከክርስቶስ ዘንድ ልዩ በረከት አልተሰጣቸውም፡፡ ግን በዕምነት የነካቸው በሽተኛ ሴት ፈውስ አገኘች፡፡ በመንፈሳዊ በኩልም በአጋጣሚ የሚደረገው መነካካት በዕምነት ከሚደረገው ግንኙነት የተለየ ነው፡፡ ክርስቶስ የዓለም አዳኝ መሆኑን ማወቅ ብቻ ለነፍስ መዳንን አያስገኝም፡፡ CLAmh 147.1

ደኅንነት የሚያስገኝ ዕምነት የወንጌልን እውነተኛነት ማወቅ ብቻ አይደለም፡፡ እውነተኛ ዕምነት ማለት ክርስቶስን የግል አዳኝ አድርጎ መቀበል ነው፡፡ ካመንሁ “እንዳልጠፋ እንድድን እንጅ” እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪለውጥ ድረስ ወዶኛል፡፡ (ዮሐንስ 3፡16) ፡፡ CLAmh 147.2

በቃሉ መሠረት ወደ ክርስቶስ ስቀርብ የማዳኑን ጸጋ እቀበላለሁ፡፡ አሁን የምኖረው ሕይወት “በዕምነት በሚወደኝ በአብ ፍቅር ተቀብያለሁ፡፡” (ገላትያ 2፡20) ፡፡ CLAmh 147.3

ብዙዎች ዕምነትን እንደ አስተያየት ይቈጥሩታል፡፡ የሚያድን ዕምነት ክርስቶስን የተቀበሉ ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋዋሉበት ቃል ኪዳን ነው፡፡ ሕያው ዕምነት ማለት ኃይልን የሚሰጥ ሃይማኖትን የሚያጸና፤ በክርስቶስ ጸጋ አማካይነት አማኙን ድል አድራጊ የሚያደርግ ነው፡፡ CLAmh 147.4

ከሞት ይልቅ ዕምነት ኃያል አሸናፊ ነው፡፡ በሽተኞች የሃይማኖት ዓይናቸውን በታላቁ ፈዋሽ ላይ ቢጥሉ አስገራሚ ውጤት በተገኘ ነበር፡፡ መንፈስና አካል በታደሰ ነበር፡፡ CLAmh 147.5

በመጥፎ ልማድ የተጠመዱ ሰዎችን ወደሚገሠግሡበት አደገኛ መዳረሻ በማመልከት ፈንታ ወደ ክርስቶስ ፊታቸውን እንዲመልሱ መርዳት ይበጃል፡፡ ወደ ሰማይ ክብር አሳዩአቸው፡፡ ተስፋ የቈረጡትን የሚደርስባቸውን ጥፋት እያወሱ ከማስፈራራት ይልቅ የተጠቀሰው ዘዴ ለመንፈስ ዕረፍትን፤ ለአካል ብርታትን ይሰጣል፡፡ CLAmh 147.6