መልዕክት ለወጣቶች
በትክክለኛ መርሆዎች ሚዛንን መጠበቅ
ብሩህ አእምሮ ያላቸው ወጣቶች ሁል ጊዜ ታላቅ ስኬትን ያመጣሉ ማለት ስህተት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ተሰጥኦና ትምህርት ያላቸው ሰዎች ታማኝነትን በሚጠይቁ ቦታዎች ላይ ተቀምጠው ስኬታማ አለመሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ማብለጭለጫቸው ወርቅ አስመስሎአቸው ነበር፣ ነገር ግን በተፈተኑ ጊዜ የሚያብረቀርቅ ተራ ብረትና ሰም ሆነው ተገኝተዋል፡፡ ታማኞች ስላልሆኑ በስራቸው ያልተሳካላቸው መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ጠንካራና ሳይታክቱ የሚሰሩ ሠራተኞች ባለመሆናቸው መሰራት ወደሚገባቸው ነገሮች ዝግ ብለው አልሄዱም፡፡ ከመሳሰሉ ሥር ጀምረው ጫፍ እስኪደርሱ ድረስ እያንዳንዱን መወጣጫ ደረጃ በደረጃ ለመውጣት ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ እራሳቸው በጫሩት የአእምሮአቸው ብልጭታ ተራምደዋል፡፡ ከእግዚአብሔር ብቻ ሊሰጥ በሚችለው ጥበብ አልተደገፉም፡፡ ለውድቀታቸው ምክንያቱ እድሉን ስላላገኙ ሳይሆን በኃጢአት የሚያዝን አእምሮ ስለሌላቸው ነው፡፡ከትምህርት የሚገኝ ጥቅም ለእነርሱ ዋጋ ያለው መሆኑ ስላልተሰማቸው በሃይማኖትና በሳይንስ እውቀት ወደፊት መሄድ የሚገባቸውን ያህል አልሄዱም፡፡ አእምሮአቸውና ባሕርያቸው በትክክለኛነት ከፍ ያለ መርህ ሚዛኑን አልጠበቀም፡፡ Fundamentals of Chiristian Education, p. 193. MYPAmh 122.1