መልዕክት ለወጣቶች
ለወደፊት አደጋዎች መዘጋጀት
ዓለም ማስጠንቀቂያ ሊሰጠው ይገባል፤ ማንኛውም ነፍስ ጥልቀት በሌለው የእውነት እውቀት ረክቶ መቀመጥ የለበትም፡፡ ለምን ኃላፊነት እንደምትጠሩ አታውቁም፡፡ የእውነት ምስክርነታችሁን እንድትሰጡ ወዴት እንደምትጠሩም አታውቁም፡፡ ብዙዎች በፍርድ ቤቶች በፈራጆች ፊት ይቆማሉ፤ አንዳንዶች ለእምነታቸው ምላሽ ለመስጠት በነገሥታትና የምድር ምሁራን ፊት ይቆማሉ፡፡ MYPAmh 121.5
ጥልቀት የሌለው የእውነት ማስተዋል ያላቸው ጥቅሶችን ማብራራትና ለእምነታቸው ግልጽ ምክንያት መስጠት አይችሉም፡፡ ጥያቄው ሲቀርብላቸው ግራ ይጋባሉ፤ የማያሳፍሩ ሠራተኞች መሆን አይችሉም፡፡ ማንም ሰው በተቀደሰው መድረክ ስለማይሰብክ ማጥናት እንደማያስፈልገው አያስብ፡፡ እግዚአብሔር ምን እንድታደርጉ እንደሚጠይቃችሁ አታውቁም፡፡ MYPAmh 121.6
መታመንን ለሚጠይቅ ኃላፊነት ራሳቸውን ገጣሚ አድርገው በሾሙ ምሁር ሠራተኞች ምክንያት የእግዚአብሔር ሥራ ወደፊት እንዳይቀጥል መታገዱ የሚያስለቅስ እውነታ ነው፡፡ እግዚአብሔር በታላቁ የመከር መስክ እንዲሰሩ በሺሆች የሚቆጠሩትን ይቀበላቸዋል፤ ነገር ግን ብዙዎች ራሳቸውን ለሥራው ገጣሚ ሳያደርጉ ቀርተዋል፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ለክርስቶስ ሥራ ራሱን ያጨ ሰው፣ በጌታ ሠራዊት ውስጥ እንደ ወታደር ራሱን የሰጠ ሰው፣ የታማኝነት ሥራን መስራት በሚችልበት ቦታ ራሱን ማስቀመጥ አለበት፡፡ አስመሳይ ለሆኑ የክርስቶስ ተከታዮች ኃይማኖት ምንም ማለት አይደለም፡፡ ጥበብና እውቀት ሊደረስ በሚችል ቦታ ተቀምጦ እያለ ማንም ሰው መሀይም ሆኖ እንዲቀር የእግዚአብሔር ፈቃድ አይደለም፡፡ Fundamantals of Christian Education, p. 216-217. MYPAmh 121.7