መልዕክት ለወጣቶች
ተግባራዊ ስልጠና
ጠቃሚ የእጅ ሥራ የወንጌል እቅድ ክፍል ነው፡፡ ታላቁ መምህር በደመና አምድ ተከቦ እያንዳንዱ ወጣት አንድ ጠቃሚ የሆነ የሥራ ዘርፍ መማር እንዳለበት ለእስራኤል ልጆች መመሪያዎችን ሰጠ፡፡ ስለዚህ ሃብታሞችም ሆኑ ደሃዎች፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን አንድ ዓይነት ጠቃሚ ሥራ ማስተማር የአይሁድ ባህል ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢገጥሙአቸው እንኳን በሌሎች ሰዎች ላይ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ ለራሳቸው ሰርተው የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟለት እንዲችሉ ለማድረግ ነው፡፡ በስነ-ጽሁፍ ዘርፍ ይሰለጥኑ ይሆናል፤ ነገር ግን በተጨማሪ የእጅ ሙያ ስልጠናም ግዴታ ነው፡፡ ይህ ከትምህርታቸው አንዱና የማይቀር ክፍል ነበር፡፡ MYPAmh 117.1