መልዕክት ለወጣቶች
ለዘላለም የሚሆን ትምህርት
ዮሐንስ «ወጣቶች ሆይ ብርቱ ስለሆናችሁ፣ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ስለሚኖርና ክፉውን ስላሸነፋችሁ እጽፍላችኋለሁ» ይላል፡፡ ጳውሎስም ጢሞቲዎስን ወጣቶች «የረጋ አእምሮ» እንዲኖራቸው እንዲጠይቃቸው ያደፋፍራል፡፡ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ታማኝና ጽኑ አገልጋይ እንደነበረው እንደ ዳንኤል ለመሆን ነፍሳችሁን ከፍ አድርጉ፡፡ የቆማችሁበት ቦታ ቅዱስ ስለሆነና የእግዚአብሔር መላእክት በዙሪያችሁ ስለሆኑ እግሮቻችሁ የሚሄዱበትን መንገድ በደንብ አሰላስሉ፡፡ MYPAmh 116.1
በትምህርት መሰላል ላይ ወደ ጫፍ መድረስ እንዳለባችሁ ቢሰማችሁ ትክክል ነው፡፡ ፍልስፍናና ታሪክ አስፈላጊ ትምህርቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን እነዚህን ትምህርቶች ለመማር የከፈልከው የጊዜ መስዋዕትነት፣ ያወጣኸው ገንዘብና ያገኘኸው ስኬት ለእግዚአብሔር ክብርና ለሰዎች ጥቅም ካልተጠቀምክበት ምንም ጥቅም የለውም፡፡ MYPAmh 116.2
የሳይንስ እውቀት ከፍ ያሉ ግቦችን ለመድረስ መወጣጫ ድልድይ ካልሆነ በስተቀር ዋጋ የለውም፡፡ ለዘላለም የማይሆንን እውቀት የሚሰጥ ትምህርት ጥቅም የለውም፡፡ ሰማይንና የወደፊቱን ዘላለማዊ ህይወት በፊታችሁ ካላኖራችሁ በስተቀር ስኬቶቻችሁ ዘለቄታ ያለው ዋጋ የላቸውም፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ በሳምንት አንድ ቀን ብቻ ሳይሆን በየእለቱ መምህራችሁ ከሆነ የስነ-ጽሁፍ እውቀትን ለማግኘት በምታደርጉት ጥረት የእርሱ ፈገግታ ይከተላችኋል፡፡ Fundamentals of Christian Education., P. 191-192. MYPAmh 116.3