መልዕክት ለወጣቶች

183/511

እውቀትና ራስን መግራት

መሰሎቻቸውን ለመባረክ ለእውቀት የሚጠሙ ራሳቸው ከእግዚአብሔር በረከትን ይቀበላሉ፡፡ ቃሉን በማጥናት የአእምሮ ኃይሎቻቸው ለልባዊ ሥራ ይነሳሳሉ፡፡ የተለያዩ የአካልና አእምሮ ኃይሎች በመስፋታቸውና በማደጋቸው አእምሮ ኃይልና ብቃት ያገኛል፡፡ MYPAmh 115.1

ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኛ መሆን የሚፈልግ እያንዳንዱ ግለሰብ ራስን መግራትን መለማመድ አለበት፡፡ ይህ ከአንደበተ ርቱዕነት ወይም እጅግ አስደናቂ ከሆኑ መክሊቶች የበለጠ ይሠራል፡፡ Christ’s Object Lessons, P. 334-335. MYPAmh 115.2