መልዕክት ለወጣቶች

182/511

ሁለንተናዊ ትምህርት

ትምህርትን የሚፈልጉ ወጣቶች የፈለጉትን ትምህርት ለማግኘት በጽናት ይስሩ፡፡ ክፍተት እስኪገኝ አትጠብቁ፡፡ ለራሳችሁ ክፍተቱን ፍጠሩ፡፡ በፊታችሁ የተከፈተውን ማንኛውንም ትንሽ መንገድ አጥብቃችሁ ያዙ፡፡ ቁጠባን ተለማመዱ፡፡ የምታገኙትን ገቢ የምግብ ፍላጎታችሁን ለማሟላትና ደስታን ለመፈለግ አታባክኑ፡፡ እግዚአብሔር ጠቃሚና ብቁ እንድትሆኑ እንደጠራችሁ ሆናችሁ ለመገኘት ቁርጥ ውሳኔ ይኑራችሁ፡፡ በማንኛውም በምታደርጉአቸው ነገሮች ፍፁምና ታማኝ ሁኑ፡፡ የአእምሮ ችሎታችሁን ለማጠንከር ልትደርሱበት የምትችሉትን እያንዳንዱን መልካም አጋጣሚ መጠቀም አለባችሁ፡፡ የመጽሐፍት ጥናት ጠቀሜታ ካለው የእጅ ሥራ ጋር ይጣመር፡፡ ታማኝነት ባለበት ጥረት፣ ነቅቶ መጠበቅና ፀሎት ከላይ የሆነውን ጥበብ አግኙ፡፡ ይህ ሁለንተናዊ ትምህርትን ይሰጣችኋል፡፡ በመሆኑም በባሕርያችሁ ወደ ላይ ከፍ ትሉና በሌሎች አእምሮ ተጽእኖ ይኖራችኋል፡፡ ይህም እነርሱን በእውነተኛነትና በቅድስና መንገድ እንድትመሩ ያስችላችኋል፡፡ MYPAmh 114.4

ላሉን እድሎችና መልካም አጋጣሚዎች ንቁ ብንሆን ኖር ራስን በማስተማር ስራ ብዙ ማድረግ ይቻል ነበር፡፡ እውነተኛ ትምህርት ኮሌጅ ከሚሰጠው ትምህርት የበለጠ ነው፡፡ የሳይንሶች ትምህርት ችላሊባል የማይገባ ቢሆንም ከእግዚአብሔር ጋር ባለ አስፈላጊ ግንኙነት የሚገኝ ከፍተኛ ስልጠና አለ፡፡ እያንዳንዱ ተማሪ መጽሐፍ ቅዱሱን ይውሰድና ከታላቁ መምህር ጋር ግንኙነት ይፍጠር፡፡ የመለኮታዊ እውነትን በመፈለግ ሂደት ከሚገጥሙ ጠንካራ ችግሮች ጋር ለመታገል አእምሮ መሰልጠንና መገራት አለበት፡፡ MYPAmh 114.5