መልዕክት ለወጣቶች
እውነተኛ ትምህርት
እውነተኛ ትምህርት አእምሮንና ልብን በፈጣሪ አምላክ በአዳኙ በኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት የሚሞሉ ሃሳቦችን ማስረጽ ነው፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ትምህርት አእምሮን ያድስና ባሕርይን ይለውጣል፡፡ አእምሮ የነፍሳት ጠላትን የማታለያ ሹክሹክታዎች እንዳይቀበል ያጠነክራል፤ ያነፃልም፡፡ የእግዚአብሔርን ድምፅ እንድናስተውልም ይረዳናል፡፡ የተማረውን ግለሰብ ከእግዚአብሔር ጋር አብሮ ለመስራት ገጣሚ ያደርገዋል፡፡ MYPAmh 113.1
ወጣቶቻችን ይህንን እውቀት ቢያገኙ ኖር ሌላውን አስፈላጊ የሆነ ነገር ሁሉ ማግኘት ይችሉ ነበር፡፡ ይህ ካልሆነ ግን ከዓለም የሚገኘው እውቀት በሙሉ ከእግዚአብሔር ወገን ሊያቆማቸው አይችልም፡፡ መጽሐፍት ሊሰጡአቸው የሚችሉአቸውን እውቀቶች በሙሉ መሰብሰብ ቢችሉ እንኳን በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ያለው ባሕርይ ሊሰጣቸው ለሚችለው የመጀመሪያ የጽድቅ መርህ መሀይም ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ MYPAmh 113.2
በምድራዊ ትምህርት ቤቶች እውቀት ለማግኘት የሚሹ ሁሉ ሌላም ትምህርት ቤት (የክርስቶስ ትምህርት ቤት) ተማሪዎቹ እንዲሆኑ እንደሚፈልግባቸው ማስታወስ አለባቸው፡፡ ከዚህ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በፍፁም አይመረቁም፡፡ ከተማሪዎቹ መካከል ሽማግሌዎችም ወጣቶችም ይገኙበታል፡፡ MYPAmh 113.3
ለመለኮታዊው መምህር ትምህርት ጆሮአቸውን የሚሰጡ ሁሉ ያለማቋረጥ የበለጠ የነፍስን ጥበብና ክብረት ያገኙና እድገት ለዘላለም ወደሚቀጥልበት ከፍተኛ ትምህርት ቤት ለመግባት የተዘጋጁ ይሆናሉ፡፡ ወሰን የለሽ ጥበብ ከፊታችን የህይወትን ታላቅ የሥራና የደስታ ትምህርቶችን አስቀምጦልናል፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ብዙ ጊዜ ለመማር ከባድ የሆኑ ሲሆን ግን ያለእነርሱ ምንም ዓይነት እርግጠኛ እድገት ማሳየት አንችልም፡፡ ጥረትን፤ እንባንና መቃተትን ሊጠይቁብን ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ተስፋ መቁረጥም ሆነ መዛል የለብንም፡፡ ከንፁሐንና ቅዱሳን መልእክት ጋር ማህበርተኛ ለመሆን ገጣሚ መሆን የምንችለው በዚህ ዓለም ውስጥ በፈተናዎቹ መካከል ነው፡፡ ጠቀሜታቸው አነስተኛ በሆኑ ትምህርቶች በመመሰጥ በክርስቶስ ትምህርት ቤት መማርን የሚያቆሙ ዘላለማዊ ኪሳራ እየገጠማቸው ነው፡፡ MYPAmh 113.4
ፈጣሪ ለሰው ልጆች የሰጠው እያንዳንዱ የአካልና የአእምሮ ችሎታ፣ እያንዳንዱ ብቃት ለእርሱ ክብር መዋል አለበት፡፡ እነዚህን ለእግዚአብሔር ክብር ስናውል እጅግ ንፁህ፣ የከበረና ደስታ የሞላበት ልምምድ ይገኝበታል፡፡ በህይወታችን የሰማይ መርሆዎች ከፍተኛ ቦታ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህንን እውቀት በማግኘት ወይም የአእምሮ ችሎታን በማሳደግ የሚወሰድ እያንዳንዱ እርምጃ ሰብአዊውን ከመለኮታዊው ጋር ለማዋሀድ የሚወሰድ እርምጃ መሆን አለበት፡፡ Fundamentals of Christian Education, p.543-544. MYPAmh 113.5