መልዕክት ለወጣቶች
ክርስቶስ ታላቁ መምህር
ክርስቶስ የዓለም ብርሃን ነበር፡፡ እርሱ የእውቀት ሁሉ መሠረት ነው፡፡ እርሱ ያልተማሩትን ዓሣ አጥማጆችን ሊሰጣቸው የሚችለውን ታላቅ ተልዕኮ እንዲቀበሉ ብቁ ሊያደርጋቸው ችሏል፡፡ ለእነዚህ ዝቅተኛ ሰዎች የተሰጠው የእውነት ትምህርት ታላቅ ጠቀሜታ ነበረው፡፡ ዓለምን ሊያንቀሳቅሱት ነበር፡፡ ኢየሱስ እነዚህን የዋህ ሰዎች ከራሱ ጋር ማገናኘቱ ቀላል ይመስል ነበር፡፡ ነገር ግን አስደናቂ ውጤት የሚያስከትል ክስተት ነበር፡፡ የተጠሩት ቃላቶቻቸውና ሥራዎቻቸው ዓለምን እንዲለውጡ ነበር፡፡ MYPAmh 112.3
ኢየሱስ ትምህርትን አልጠላም (አልናቀም)፡፡ የተማረ አእምሮ በፍቅርና በፈርሃ-እግዚአብሔር ከተቀደሰ የእርሱን ሙሉ ተቀባይነት ያገኛል፡፡ በክርስቶስ የተመረጡት ያልተማሩ ሰዎች በሰማይ ንጉስ የማሰልጠን ተጽዕኖ ስር በመሆን ከእርሱ ጋር ሶስት አመታት አሳልፈዋል፡፡ ክርስቶስ ዓለም ከሚያውቃቸው መምህራን ሁሉ ታላቅ መምህር ነው፡፡ MYPAmh 112.4
ወጣቶች ራሳቸውን ለእርሱ ቀድሰው የሚሰጡ ከሆነ እግዚአብሔር ከነመክሊታቸውና ፍቅራቸው ጋር ይቀበላቸዋል፡፡ እጅግ ከፍ ወዳለው የእውቀት ከፍታ ላይ ሊደርሱ ይችላሉ፡፡ ይህ እውቀታቸው በመንፈሳዊ መርህ ሚዛኑን የሚጠብቅ ከሆነ ክርስቶስ ሊሰራ ከሰማይ የመጣበትን ሥራ ወደ ፊት በመቀጠል ከጌታ ጋር አብሮ ሰራተኞች ይሆናሉ፡፡ MYPAmh 112.5
በእኛ ኮሌጅ ያሉ ተማሪዎች የሳይንስን እውቀት የማግኘት ብቻ ሳይሆን የተስተካከለ ባሕርይ እንዲኖራቸው የሚረዱአቸውን መልካም ጠባያት እንዲያሳድጉና እንዲለማመዱ የሚረዳቸውን ትምህርት የማግኘት ጠቃሚ እድሎችም አሏቸው፡፡ እነርሱ ኃላፊነት የሚሰማቸው የእግዚአብሔር የግብረገብ ወኪሎች ናቸው፡፡ የሐብት፣ የስልጣንና የእውቀት መክሊቶች ሰው በጥበብ እንዲገለገልባቸው ከእግዚአብሔር በአደራ የተሰጡ ናቸው፡፡ እነዚህን የተለያዩ መክሊቶች አመጣጥኖ አከፋፍሎአል፤ ለእያንዳንዱ ሥራ ሰጥቷል፡፡ Review and Herald, June, 21,1877. MYPAmh 112.6