መልዕክት ለወጣቶች

158/511

ፈቃድን በማስገዛት ብርታት

የፈቃድን እውነተኛ ኃይል እስክትገነዘብ ድረስ ሁልጊዜ በአደጋ ውስጥ ነህ:: ልታምንና ሁሉንም ነገሮች ቃል ልትገባ ትችላለህ። ነገር ግን ቃል ኪዳኖችህም ሆኑ እምነትህ ፈቃድህን በእምነትና በተግባር አጠገብ ካላስቀመጥክ በስተቀር ዋጋ የላቸውም። በፈቃድ ኃይልህ ሁሉ የእምነትን ጦርነት ብትዋጋ አሸናፊ ትሆናለህ። ስሜቶችህ፣ ፍላጎቶችህና የምታሳርፋቸው አሻራዎችህ፣ በተለይ የተዛቡ ሐሰቦችህ እምነት የሚጣልባቸው ስላልሆኑ ልትተማመንባቸው አትችልም። የተጣሱ ቃል ኪዳኖችህንና የተተው መሃላዎችህን ማወቅህ በራስህ ላይ ያለህን መታመን ከማዳከሙም በላይ ሌሎች ባንተ ላይ ያላቸውን እምነትም ያዳክማል። MYPAmh 100.4

ነገር ግን ተስፋ መቁረጥ የለብህም። ምንም እንኳን ማንኛውም ነገር እውነትና እርግጥ ባይመስልህም ለማመን መወሰን አለብህ። ወደዚህ ወደማይታመን ደረጃ ራስህን ያመጣህ አንተ ራስህ ነህ ብዬ መንገር አያስፈልገኝም:: በእግዚአብሔርና በወንድሞችህ የነበረህን መታመን መልሰህ ማግኘት አለብህ። የራስህን ፈቃድ ለኢየሱስ ክርስቶስ ፈቃድ ማስገዛት ያንተው ኃላፊነት ነው። ይህንን ስታደርግ እግዚአብሔር ወዲያውኑ ቁጥጥሩን ይወስድና ይሰራል። ተፈጥሮህ በሞላ በክርስቶስ መንፈስ ቁጥጥር ሥር ይሆናል። አስተሳሰቦችህም ለእርሱ ይገዛሉ። MYPAmh 100.5

ውስጣዊ ስሜቶችህንና ግፊቶችህን እንደፈለግከው መቆጣጠር አትችልም። ነገር ግን ፈቃድህን መቆጣጠርና በሕይወትህ አጠቃላይ ለውጥ ማምጣት ትችላለህ። ፈቃድህን ለክርስቶስ በማስገዛት ሕይወትህ ከክርስቶስ ጋር በእግዚአብሔር ውስጥ ይደበቅና ከኃይላትና ከሥልጣናት በላይ ከሆነው ኃይል ጋር ህብረት ትፈጥራለህ። ከእርሱ ብርታት ጋር የሚያያይዝ ከእግዚአብሔር የሆነ ጥንካሬ ይኖርሃል፡፡እንደዚሁም አዲስ ብርሐን ያውም የሕያው እምነት ብርሐን ላንተ የሚቻል ይሆናል። ነገር ግን ፈቃድህ ሰይጣን ሊያጠምድህና ሊያጠፋህ ያለማቋረጥ ከሚሰራባቸው ወዳጆችህ ፈቃድ ጋር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር መተባበር አለበት። MYPAmh 100.6

ሳትዘገይ ከእግዚአብሔር ጋር ትክክለኛ ግንኙነት አትፈጥርምን? “ፈቃዴን ለኢየሱስ አሁኑኑ እሰጠዋለሁ» በማለት ከዚህች ሰዓት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ከኢየሱስ ወገን አትሆንም”? ባህልንና በውስጥህ የሚያስቸግረውን ጠንካራ የምግብ ፍላጎትና ፍትወትን ቸል በል:: ሰይጣን “አንተ ጎስቋላ የሆንክ ግብዝ ነህ” እንዲልህ እድል አትስጠው። ሰይጣን እንዳይከስህና ተስፋ እንዳያስቆርጥህ በሩን ዝጋ። “አምናለሁ! እግዚአብሔር ረዳቴ እንደሆነ አምናለሁ” በለው። ያኔ በእግዚአብሔር አሸናፊ መሆንህን ታያለህ። ፈቃድን አጽንተህ በእግዚአብሔር ወገን በመጠበቅ ስሜቶችህ እንኳን የኢየሱስ ፈቃድ ምርኮኞች ይሆናሉ። ያኔ እግርህ በፅኑ ዓለት ላይ ቆሞ ታገኛለህ። ይህንን ማድረግ አንዳንድ ጊዜ ያለህን ጥቃቅኑን የፈቃድ ኃይልህን በሙሉ ይጠይቃል። ነገር ግን ላንተ እየሠራ ያለው እግዚአብሔር ስለሆነ ከዚያ ከምትቀረጽበት ሂደት ውስጥ የክብር ዕቃ ሆነህ ትወጣለህ። MYPAmh 101.1