መልዕክት ለወጣቶች
አለመረጋጋትና ጥርጣሬ
አንተ እውቀት ያለህ ወጣት ነህ። ሕይወትህን በመጨረሻ ለሰማይ ገጣሚ እንዲሆን ለማድረግ ትሻለህ። ብዙ ጊዜ ራስህን በግብረገብ ኃይል ደካማ፣ የጥርጣሬ ባሪያና በአሮጌው የኃጢአት ሕይወት ልምዶችና ባህሎች ተገዥ ሆነህ በመገኘትህ ተስፋ ትቆርጣለህ። ፍላጎቶችህን የምትገልጽበት ተፈጥሮህ ለራስህ ልባዊ መሃላዎችና ምርጥ ውሳኔዎች የማይገዛ ሆኖ ታገኛለህ። ምንም ነገር እርግጠኛ መስሎ አይታይህም። የራስህ አለመረጋጋት ሊጠቅሙህ የሚችሉ ሰዎችን እውነተኛነት እንድትጠራጠር ያደርግሃል። MYPAmh 100.2
በጥርጣሬ ውስጥ አብዝተህ በታገልክ ቁጥር የትም ቦታ ፀንተህ መቆም የምትችልበት የፀና መሬት የሌለ እስኪመስልህ ድረስ ሁሉም ነገር እርግጠኛ ያልሆነ ይመስልሃል። ተስፋዎችህ እንደ አሸዋ ገመድ ይሆኑብህና ልትተማመንባቸው የሚገቡህን ሰዎች ተግባራት በተመሳሳይ እርግጠኛ ባልሆነ ብርሃን ታያቸዋለህ። MYPAmh 100.3